የወልድያውን ጅምላ ግድያ የተባበሩት መንግስታት አወገዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2010) በወልዲያ በቃና ዘገሊላ በአል ላይ በወጡ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጅምላ ግድያ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አወገዘ። ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በመንግስት ታጣቂዎች የተፈጸመው ጅምላ ግድያ ገለልተኛ በሆነ አካል በአስቸኳይ ተጣርቶ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ተጠያቂ መሆን ይኖርባቸዋል። ጥቃቱን የሚፈጽሙ ያልሰለጠኑ የጸጥታ አካላትም ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል ብሏል። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የወልዲያው ...

Read More »

በወልዲያ ህዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 15/2010) በወልዲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ታወቀ።   በዕለቱ ይውል የነበረው የማክሰኞ ገበያም እንዳይቆም ተደርጓል። የተገደሉት ሰዎች ቁጥ እያሻቀበ ነው። በአልሞ ተኳሽ ከተመቱት ሌላ በስልት ተወግተው ሆስፒታል የገቡ በርካታ ሰዎችም እንዳሉ ይነገራል። የግጭቱ መንስዔ በበዓሉ ላይ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት የሚያንጸባርቁ ወጣቶች እንደሆኑ በህወሃት አገዛዝ በኩል ተገልጿል። ለኢሳት ዛሬ በደረሰው መረጃ ግን ከ13 ሰዎች በላይ በግፍ ለተገደሉበት ...

Read More »

ጆርጅ ዊሃ የላይቤሪያን የመሪነት መንበር ተረከበ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2010) ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃ ዛሬ የላይቤሪያን የመሪነት መንበር ተረከበ። በሞኖሮቪያ ሳሙኤል ዶ ስታዲየም በተካሄደው ደማቅ ስነስርዓት የላይቤሪያን የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የተረከበው ጆርጅ ዊሃ ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደርገው ንግግር ብቻዬን የማደርገው ነገር የለምና አግዙኝ አብራችሁኝ ሁኑ ሲል ጥሪ አቅርቧል። ላለፉት 12 አመታት በላይቤሪያ የመሪነት ስልጣን ላይ የቆዩትን ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍን ተክቶ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን ዛሬ ቃለ መሃላ በመፈጸም ...

Read More »

ሁለት ድጋፍ ሰጪ አካላት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2010) የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት /መኢሕድ/ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ የድጋፍ ትብብር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። የሁለቱ ድጋፍ ሰጭ የስራ አመራር አባላት በቨርጂኒያ ሒልተን ሆቴል ባደረጉት የስምምነት ስነ ስርአት ላይ እንደተገለጸው ፓርቲዎቹ የሕወሃትን ስርአት ለመለወጥ በጋራ ለመስራት ይተባበራሉ። በዚሁም የዲፕሎማሲ ጥረቶችን በጋራ ለማከናወን በአገዛዙ ላይ የሚካሄዱ ተቃውሞዎችን በትብብር ማካሄድና ጥቃት በአንደኛው ማህበረሰብ ...

Read More »

አቶ ስዬ አብርሃ ሀገር ቤት ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2010) በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ውስጥ የተፈጠረው ቀውስ መፍትሄ ባላገኘበት በአሁኑ ወቅት አቶ ስዬ አብርሃ ሀገር ቤት መግባታቸው ታወቀ። በአቶ ስብሃት ነጋ የሚደገፈው የዶክተር ደብረጺዮን ቡድን በአቶ አባይ ወልዱ ቡድን ላይ የጀመረውን ጥቃት በመቀጠልም ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ከኤፈርት ሃላፊነት ማንሳቱንም የሕወሃት ደጋፊ የመረጃ ማዕከላት ዘግበዋል። ከአንጋፋዎቹ የሕወሃት ታጋዮች አንዱ የነበሩትና የሕወሃት ጦር አዛዥ በኋላም የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ...

Read More »

በወልዲያ በአገዛዙ ታጣቂዎች የተፈጸመው ጅምላ ግድያ ተወገዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2010) በወልዲያ በጥምቀት በዓል ማግስት በቃና ዘገሊላ በዓል ላይ በአገዛዙ ታጣቂዎች የተፈጸመውን ጅምላ ግድያ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት በጽኑ አወገዙ። ፓርቲዎቹና የሲቪክ ማህበራቱ ግድያውን አስመልክቶ ባወጡት መግለጫ እንዳሉት በሕወሃት/ኢሕአዴግ የሚመራውን አገዛዝ ለማስወገድ ሕዝቡ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል። በመላው ኢትዮጵያ የሚካሄደው የጸረ ሕወሃት ትግልን ማቀናጀት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በአገዛዙ ...

Read More »

በወልዲያ ከ7 በላይ ሰዎች የተገደሉት ወጣቶች ባስነሱት ግጭት ምክንያት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 14/2010) በወልዲያ በቃና ዘገሊላ በዓል ላይ ከ7 በላይ ሰዎች የተገደሉት የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ወጣቶች ባስነሱት ግጭት ምክንያት ነው ሲሉ የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ገለጹ። መምሪያ ሃላፊው ኮማንደር አማረ ጎሹ የአካባቢው ታጣቂዎች ትዕግስታቸው በማለቁ ርምጃውን ለመውሰድ ተገደዋል ብለዋል። ወጣቶቹ ግን በጭፈራ ከመቃወም ውጪ የፈጸሙት ነገር አለመኖሩን የአይን እማኞች ተናግረዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ...

Read More »

በወልዲያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ –ጥር 14/2010) በወልዲያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለ3ኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። ትላንት ምሽቱን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከስርዓቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ንብረት ላይ ርምጃ ሲወሰድ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ጠዋት ነዋሪው በዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞ ማድረጉም ተመልክቷል። የአጋዚ ወታደሮችን ተኩሶ የገደለው ወጣት የቀብር ስነስርዓት በተቃውሞ ታጅቦ ተከናውኗል። ዛሬም በአጋዚ ወታደሮች ግድያ መፈጸሙ ታውቋል። ተጨማሪ ሃይል ወደ ከተማዋ ያስገባው ...

Read More »

የጥምቀት በዓል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2010) በየዓመቱ ጥር 11 የሚከበርው የጥምቀት በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ። በኢትዮጵያ በበዓሉ አከባበር ላይ ስርዓቱን የሚቃወሙ ድምጾች በብዛት መሰማታቸው ታውቋል። በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንደኛው የጥምቀት በዓል ነው። በዘንድሮው የጥምቀት በአልም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ በሚከበርባቸው ቦታዎች በመገኘት ሃይማኖታዊ ስነስርዓቱን ተካፍለዋል። በበዓሉ ዋዜማ በሚከበረው የከተራ በዓልም ታቦታቱ ከየደብራቸው ...

Read More »

በካሽሚር ግዛት አዲስ ውጥረት ነገሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 11/2010) ሕንድና ፓኪስታን በሚወዛገቡባት የካሽሚር ግዛት አዲስ ውጥረት ነገሰ። የህንድ ወታደሮችን ጨምሮ በትንሹ 5 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት ወታደሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱም ታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2003 የተካሄደውን የተኩስ ማቆም ስምምነትን ተከትሎ ጃሙና ካሽሚር በተባለ ስፍራ ላይ እንዲወሰኑ የተደረገውን ወታደራዊ የድንበር መስመር የተቀበሉ ቢሆንም በቀደሙት አመታት ህንድ ፓኪስታንን ስትወነጅል ቆይታለች። ሆኖም ከ15 አመታት ወዲህ የአሁኑ ከፍተኛና ...

Read More »