አዞላና ኢፓማ የተባሉ አረሞች ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) በጣና ሃይቅ ላይ አዞላና ኢፓማ የተባሉ አረሞች በተጨማሪ ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ። እምቦጭ አረም ሃይቁ ላይ እያደረሰ ያለው አደጋም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የውሃ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ የጣና ሃይቅ ባለፉት አመታት የተለያዩ የህልውና ፈተናዎች ገጥመውታል ሲሉ ለቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ተናግረዋል። ፈተናዎቹን የአፈር መከላት፣የደለል ክምችት፣ተገቢ ያልሆነ የስነ-ሕይወት አጠቃቀም፣ልቅ ግጦሽና የባህር ሸሽ ...

Read More »

በጉዲፈቻ የተወሰዱ ሰባት ሺ ህጻናት የት እንደደረሱ አይታወቅም ተባለ

  (ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2018) በጉዲፈቻ ከኢትዮጵያ ወደ ወጭ የተወሰዱ ሰባት ሺ ህጻናት የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ ወደ ውጭ በጉዲፈቻ የሚሰጡ ህጻናት በተገቢው ህጋዊ አሰራር እየተፈፀመ አለመሆኑን ለፓርላማ ገልፀዋል፡፡ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ያሉ ደላሎች ወላጆችን በማታለልና ከሌሎች አካላት ጋር በመመሳጠር በህገወጥ መንገድ ህፃናትን ወደ ተለያዩ ሀገራት ልከዋል፡፡ ...

Read More »

የአለም ባንክ ቋሚ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ ነዋሪዎች 200ሺ የሚሆኑት ራሳቸውን መመገብ ባለመቻላቸው የአለም ባንክ ቋሚ ድጋፍ ሊያደርግላቸው መሆኑ ተገለጸ። አቅመ ደካሞች ለሆኑት በየወሩ ቋሚ ክፍያ በመስጠት እንዲሁም ሌሎቹን ደግሞ በአካባቢ ጽዳትና መሰል ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ገንዘቡ እንደሚከፈላቸው ተመልክቷል። በፍጹም ድህነት ውስጥ ከሚገኙት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች 32ሺ የሚሆኑት አቅመ ደካሞች በመሆናቸው በነፍስ ወከፍ በወር 170 ብር በቤተሰብ ቁጥር ተባዝቶ ...

Read More »

የአጼ ቴድሮስ ሐውልት ተመረቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010) የአጼ ቴድሮስ ሐውልት በደብረታቦር ከተማ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ተመረቀ። በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በ2 ሚሊየን ብር ወጪ የተሰራው የአጼ ቴድሮስ ሃውልት 7 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ያለው ነው። በኢትዮጵያ የንግስና ታሪክ ከ1847 እስከ 1860 ኢትዮጵያን የመሩት አጼ ቴድሮስ የሀገር አንድነት ተምሳሌት ናቸው። በከፋፍለህ ግዛው ስልት በተነጣጠለ ሁኔታ በኢትዮጵያ የነበረውን የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ለማስወገድ ደፋ ቀና ያሉት አጼ ቴድሮስ በእንግሊዞች ...

Read More »

  የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ 17 እስረኞችን አስለቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010)   የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኚት ከተማ በሚገኘው እስር ቤት ላይ ባደረሰው ጥቃት 17 እስረኞችን ማስለቀቁን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ። አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ መገለጫ እንደሚያመልከተው ዘመቻ ነጻ ትውልድ በሚል መጠሪያ ማክሰኝት እስር ቤት ላይ በተፈጸመጥቃት ነው 17 እስረኞች ነጻ የወጡት። ትላንት ለሌት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 9 ሰአት ላይ ፈጸምኩት ባለው ...

Read More »

በፈረንሳዩ የሽብር ድርጊት ተሳታፊ የነበረው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ

 (ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) በፈረንሳይ ፓሪስ ለ130 ሰዎች ዕልቂት ምክንያት በሆነው የሽብር ድርጊት ተሳታፊ የነበረው ተጠርጣሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ። ለዳኞቹ ምንም የምላችሁ ነገር የለም ዝምታዬ ለኔ የመከላከያ ማስረጃዬ ነው ማለቱም ተመልክቷል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ህዳር 13/2015 በፈረንሳይ ፓሪስ የሙዚቃ ዝግጅት በሚካሄድበት አዳራሽ፣በስታዲየምና በሆቴል ላይ በተሰነዘረው ተከታታይ የሽብር ጥቃት ለ130 ሰዎች ማለቅና በመቶዎች ለሚቆጠሩ መቁሰል ተጠያቂ ከነበሩት ተጠርጣሪ አሸባሪዎች አንዱ ...

Read More »

የኦፌኮ አመራሮች ለ2ተኛ ጊዜ ተፈረደባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አመራሮች ለ2ተኛ ጊዜ ተፈረደባቸው። ተከሳሾቹ በድጋሚ የ6 ወራት እስራት የተፈረደባቸው በችሎት ውስጥ በዳኛው ከመቀመጫቸው እንዲነሱ ታዘው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ተብሏል። ጠበቆቻቸው ግን እኛ ከተነሳን ተከሳሾች እንዲነሱ አይገደዱም ነበር ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመውታል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ ያሉትን ተከሳሾች አቶ ...

Read More »

የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎትን ለማዳረስ የተመደበው 445 ሚሊየን ብር በሕወሃት ተዘረፈ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2018) በአማራ ክልል በዚህ ዓመት የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎትን ከ10 በላይ ለሚሆኑ ከተሞችና ቀበሌዎች ለማዳረስ በሚል የተመደበው 445 ሚሊየን ብር በሕወሃት በመዘረፉ አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችሉ ተገለፀ ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ከሕዝብ በተለያዩ መንገዶች ማለትም ከአገልግሎት ፥ ከአዲስ መስመር ዝርጋታ ጥያቄዎች ፥ ከቅጣትና ከልዩ ልዩ ገቢዎች የሰበሰበው 445 ሚሊዮን ብር ለትግራይ ክልል መሰጠቱ ታውቋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሰሜን ...

Read More »

በኢትዮ ሳት ሳተላይት የግልም ሆነ የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በግዳጅ እንዲሰራጩ የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት አጣ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) የኢትዮጵያው አገዛዝ በሚቆጣጠረው ኢትዮ ሳት ሳተላይት የግልም ሆነ የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በግዳጅ እንዲሰራጩ በብሮድካስት ባለስልጣን የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት ማጣቱ ተገለጸ። በተለይ የኦሮሚያና የአማራ መገናኛ ብዙሃን በዚህ ሳተላይት በኩል እንዲሰራጩ የተደረገው ሙከራ ክልሎቹ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካ አልቻለም። “ኢትዮ ሳት” በኢንሳ በኩል ቁጥጥር የሚደረግበትና ከፈረንሳይ ኩባንያ አገዛዙ በውድ ዋጋ የተከራየው ሳተላይት ነው። በሳተላይቱ ከ35 በላይ ቻናሎች ሊሰራጩበት እንደሚችልም ነው ...

Read More »

የተሰጠው ወታደራዊ ማዕረግ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ብሶትና ምሬት ለማዳፈን ያለመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) ለ61 ወታደራዊ መኮንኖች የተሰጠው ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ብሶትና ምሬት ለማዳፈን ያለመ ነው ተባለ። ኢሳት ያነጋገራቸው ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደገለጹት ያለዕውቀትና የውጊያ ልምድ በብሄር ኮታ የታደለው ወታደራዊ ማዕረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት አቅምን ከግምት ያላስገባ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው። ባለፈው ዓርብ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሃት የሚመራው መንግስት 4 የሙሉ ጄነራል፣ የ3ሌተናል ጄነራል፣ ...

Read More »