በአለም የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ የሼህ መሃመድ አላሙዲን ስም አልሰፈረም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በአለም የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ የሼህ መሃመድ አላሙዲን ስም አለመስፈሩ ታወቀ። ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል በአለም በሃብት ግንባር ቀደም የሆኑት ቢልጌትም በአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቢዞ ተበልጠው ወደ ሁለተኛ ደረጃ መውረዳቸው ተሰምቷል። በአለም የሚገኙት ቢሊየነሮች ቁጥር 2 ሺ 208 መድረሱም ተመልክቷል። የባለጸጎቹን የሃብት መጠን በተመለከተ አመታዊ ሪፖርቱን ያወጣው ፎርብስ መጽሔት ይፋ ባደረገው የ2018 የሃብታሞች ዝርዝር ዚምባቡዌና ሃንጋሪ ቢሊየነሮቻቸውን አስመዝግበዋል። ...

Read More »

የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱና በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው በደል እንዲቆም ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በወህኒ ቤት የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱና በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው በደል እንዲቆም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ጠየቀ። ሌሎች የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች እየተፈቱ ባሉበት ወቅት የዋልድባ መነኮሳትን በወህኒ ቤት ውስጥ ማገትና ማጎሳቆል የሕወሃት መንግስት ለቤተክርስቲያኒቱ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ ነው ሲልም ሕብረቱ አመልክቷል። “ወይባና አስኬማ የዋልድባ መነኮሳት ክብር” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ባወጣውና ለዋልድባ መነኮሳት አጋርነቱን በገለጸበት ...

Read More »

አምስት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት ታሰሩ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በኦሮሚያ ከተነሳው አድማ ጋር በተያያዘ አምስት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት መታሰራቸው ተነገረ። በኦሮሚያ የተጀመረው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል። ባለስልጣናቱ የታሰሩት የስራ ማቆም አድማው እንዲካሄድ ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ነው። በኦሮሚያ ክልል በአገዛዙ የኮማንድ ፖስት አባላት የታሰሩት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት የምስራቅ ሃረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪን የሚጨመር ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አድማ ቀስቅሳችኋል ተብለው ከታሰሩት ...

Read More »

የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ በሶሪያ ውስጥ መከስከሱ ተሰማ። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት 26 መንገደኞችና 6ቱ የአውሮፕላን ሰራተኞች በሙሉ ማለቃቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በሶሪያ የባህር ዳርቻ በምትገኘው ላታኪያ ከተማ ባለው የሩሲያ ወታደራዊ ጦር ሰፈር በማረፍ ላይ እያለ አውሮፕላኑ መከስከሱም ታውቋል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ሲሆን የቅድመ ምርመራ መረጃዎች አደጋው በቴክኒካል ችግር ሳይከሰስ እንዳልቀረ አመላክተዋል። ሆኖም እውነተኛውን የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል ...

Read More »

የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገና ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ገለጸ። ኦፌኮ በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና የጸደቀበት መንገድ ሕገወጥ በመሆኑ አንቀበለውም ብሏል። አዋጁ ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑም ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ኦፌኮ ገልጿል። የኦፌኮ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ...

Read More »

የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገና ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ገለጸ። ኦፌኮ በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና የጸደቀበት መንገድ ሕገወጥ በመሆኑ አንቀበለውም ብሏል። አዋጁ ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑም ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ኦፌኮ ገልጿል። የኦፌኮ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ...

Read More »

ሃገሪቱን በጦር ማስተዳደር የማይቻል ነገር ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) ሃገሪቱን በጦር ማስተዳደር ለመንግስቱ ሃይለማርያምም አልበጀም ሲሉ የአባገዳዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር አባገዳ በየነ ሰንበቶ አሳሰቡ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የዋህና ለሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለሃይማኖት አባቶችና ለአባገዳዎች የሚታዘዝ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ አያስፈልገውም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የኦሮሞ አባገዳዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር አባገዳ በየነ ሰንበቶ የወቅቱን ሁኔታ በተመለከተ በሀገር ቤት ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ይሄ ኮማንድ ፖስት የሚባለውን ነገር አልወደውም”ሲሉ ...

Read More »

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው አድማ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው አድማ በኦሮሚያ ክልል ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። አዲስ አበባ ዙሪያን ጨምሮ በምዕራብ ሸዋ፣ በወለጋ፣ በምዕራብ ሀረርጌ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በባሌና በአርሲ ለሶስት ቀናት የተጠራው አድማ ተጠናክሮ መቀጠሉን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል። ከአዲስ አበባ ወደተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቋርጧል። በሆለታ አንድ ወጣት በአጋዚ ወታደር በጥይት መመታቱ ታውቋል። በመቱ አቅመ ደካማ ለሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ...

Read More »

በኦሮምያና ጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

በኦሮምያና ጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃወም በኦሮምያ ክልል እና በጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል። አድማው በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ነው። በአዲስ አበባ ዛሬም ያልተከፈቱ የንግድ ድርጅቶች መኖራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ ከጠዋት ጀምረው ድርጅቶቻቸውን የሚዘጉና የሚከፍቱ ሰዎችን ለመሰለል ሰቪል ለብሰው ቁጥጥር ሲያደርጉ የዋሉት የደህንነት ...

Read More »

የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት “መላ በሉን” እያሉ ነው

የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት “መላ በሉን” እያሉ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፖሊስ አባላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው። ከዚህ ቀደም ባልታዬ መልኩ የጸጥታ ሃይሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ መጋባታቸውን፣ የተደራጀ ሃይል ውስጥ ተቀላቅለው ትግሉን ማካሄድ ቢፈልጉም የመረጃ እጥረት እንደገጠማቸውና በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ፎቶግራፋቸውን ...

Read More »