ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል ፖሊሶችና አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል። እርምጃው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኖበታል። በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ በተለይን በለገጣፎ አካባቢ ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የኦሮምያ ፖሊስ አባላት ምሽት ላይ ...

Read More »

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄው ነጻነትን ማስፋትእና ሁሉን አቀፍ ውይይት መደረግ ሲችል ነው አሉ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄው ነጻነትን ማስፋትእና ሁሉን አቀፍ ውይይት መደረግ ሲችል ነው አሉ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲሊርሰን እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ስልጣንን የማሸጋገር ሂደት እንደግፈዋለን ያሉት ባለስልጣኑ፣ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በጥብቅ መቃወሙዋንም ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እንደሚገድብ በተለይም ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንደሚያፍን ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደገለጹላቸው ሚኒስትሩ ...

Read More »

ወደ ውጭ የሚላከው እቃ በመጥፋቱ አብዛኛው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎቱ ተቋርጧል ተባለ

ወደ ውጭ የሚላከው እቃ በመጥፋቱ አብዛኛው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎቱ ተቋርጧል ተባለ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በኦሮምያ የሚካሄደውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ከክልሉ የሚመጡና ወደ ውጭ አገር በኢክስፖርት ስም የሚላኩ እቃዎች በመቋረጣቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት በአብዛኛው ስራ ማቋረጡን ምንጮች ገልጸዋል። አመጹ ከመጀመሩ በፊት እረፍት ያልነበረው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎት ፣ በአሁኑ ሰአት ሙሉ በሙሉ በሚባል ...

Read More »

የጎሳ ግጭቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ አዲስ የርሃብ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያናት ህብረት አስታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በአሁኑ ወቅት ያለው የድርቅ ሁኔታ ካለፈው ዓመት 2017 እ.ኤ.አ. ጋር ሲነጻጸር በከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለው ህብረቱ፣ በተለይም በአፋር፣ በሶማሊያና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ አርብቶ አደሮች በድርቁ ክፉኛ ተጠቅተዋል ። በኢትዮጵያ ካለፉት አርባ ዓመታት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጊዜያት ረሃብ እየተከሰቱ ነው። በአገሪቱ የርሃብ አደጋዎች ከዓመት ወደ ዓመት ከመደጋገማቸው በተጨማሪ እየከፋም መጣቱንም ኅብረቱ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት የተከሰተው ረሃብ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በዘውግ ላይ ካነጣጠሩ የፖለቲካ ግጭቶች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው። በተለይም ሰፊውን የድንበር ወሰን በሚዋሰኑት የሶማሊያና የኦሮሞ አካባቢዎች የሚታየው ግጭት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ ኅብረቱ በሪፖርቱ አመላክቷል። ገዥው ፓርቲ አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ ቢያውጅም መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው አሁንም መፈናቀላቸውን ቀጥለዋል። በመላ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቀት ያሉት ግጭቶች እጅግ ወደ ከፋ ደረጃ ተቀይሮ ረሃብ እንዲፈጠር አድርገዋል። ግጭትና ረሃብ በመሸሽ ከቀያቸው የፈለሱ ሰላማዊ ዜጎች መጠለያ ጣቢያዎችን እየቀያየሩ አሳሳቢ በሆነ ይዞታ ላይ ይገኛሉ። የዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያናት ህብረት ቁጥራቸው ከ250 ሽህ በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች አፋጣኝ የሆነ ድንገተኛ እርዳታ በመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩን ሪሊፍ ዌብ ዘግቧል።

የጎሳ ግጭቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ አዲስ የርሃብ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያናት ህብረት አስታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በአሁኑ ወቅት ያለው የድርቅ ሁኔታ ካለፈው ዓመት 2017 እ.ኤ.አ. ጋር ሲነጻጸር በከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለው ህብረቱ፣ በተለይም በአፋር፣ በሶማሊያና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ አርብቶ አደሮች በድርቁ ክፉኛ ተጠቅተዋል ። በኢትዮጵያ ካለፉት አርባ ዓመታት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጊዜያት ረሃብ እየተከሰቱ ነው። ...

Read More »

የትምህርት ስርዓቱ ችግር ከሃያ ስድስት ዓመታት በኋላም እንዳልተስተካከለ መምህራን ተናገሩ፡፡

የትምህርት ስርዓቱ ችግር ከሃያ ስድስት ዓመታት በኋላም እንዳልተስተካከለ መምህራን ተናገሩ፡፡ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በትምህርት ጥራት ዙሪያ መደረግ ስላለበት የማስተካከያ እርምጃ የክልሉን መምህራን እየተዘዋወረ ሲያነጋግር ለነበረው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራር ቡድን አስተያየታቸውን የሰጡት መምህራን፣ በክልሉ ተማሪዎች ዕውቀት ላይ ከፍተኛ ቀልድ እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ህልውና የተቀመጠው በተማረው የሰው ኃይል ላይ ቢሆንም፣ በየጊዜው የሚወጡ ውጤታማ ያልሆኑ ...

Read More »

የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ሲውል፣በቀብሪደሀር የህወኃት የጦር መኮንን በኦሮሚያ ፖሊስ እንደተገደሉ ተዘገበ።

የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ሲውል፣በቀብሪደሀር የህወኃት የጦር መኮንን በኦሮሚያ ፖሊስ እንደተገደሉ ተዘገበ። (ኢሳት ዜና የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሶስት ቀናት የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ዛሬም በተለይ በኦሮምያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ሆኗል። የፌደራል ፖሊሶችና የአጋዚ ወታደሮች በብዛት በመውጣት እንደተለመደው የንግድ ድርጅቶችን ሲያሽጉ ውለዋል። በድርጅቶቻቸው አቅራቢያ የተገኙ ነጋዴዎችም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። አድማውን ያስተባብራሉ የተባሉ የመንግስት ሰራተኞች፣ የወረዳና የዞን ...

Read More »

በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 28 አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ ጠየቁ።

በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 28 አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ ጠየቁ። (ኢሳት ዜና የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ተፈጥሮ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረትም ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ ባወጡዋቸው 5 የአቋም መግለጫዎች፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ፣ የዜጎች መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እውን እንዲሆንና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲከፈት፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ እንዲደረግና ከመቀባበር ፖለቲካ ወደ ሰለጠነ ህገመንግስታዊ የሽግግር ስርዓት ሽግግር ...

Read More »

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። (ኢሳት ዜና የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵያ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ እና የዋጋ ግሽበቱ ባስከተሉት ጫናዎች ምክንያት የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ፍጥነት እየናረ እንደሚገኝ ተነገረ። የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ዛሬ ባወጣው ወርሃዊ የዋጋ ንረት ልኬት ቀመር መሰረት በየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በ15 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጿል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ምግብና ...

Read More »

በጣሊያን የመጀመሪያው ጥቁር ሴናተር ተመረጡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) አንድ ናይጄሪያዊ በጣሊያን የመጀመሪያው ጥቁር ሴናተር ሆነው ተመረጡ። ቶኒ ኢዎቢ የተባለው ናይጄሪያዊ በአውሮፓ ምድር የተመረጠ የመጀመሪያ ጥቁር ሴናተርም ሆኗል ሲል አወድሶታል ናይጄሪያን ፖለቲክስ የተባለው ድረገጽ። ቶኒ ኢዎቢ የኮምፒዩተር ሳይንስ ባለሙያና ኑሯቸውን ላለፉት 39 አመታት ያህል በጣሊያን ማድረጋቸውም ታውቋል። በማቶ ሳልቫኒ ፓርቲ ውስጥ ዘረኝነት ከምን ግዜውም በላይ እየታየ ነው በተባለበት በዚህ ሰአት መመረጣቸው ብዙዎችን አስገርሟል። የቶኒ ኢዎቢ በሴናተርነት ...

Read More »

በአሲድ ጥቃት ቃጠሎ የደረሰባትን ኢትዮጵያዊት ለመርዳት እርዳታ እየተሰበሰ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት በአሲድ ጥቃት ቃጠሎ የደረሰባትን ኢትዮጵያዊት ለመርዳት የእርዳታ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ተጀመረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ የነበረችውና አሜሪካ ከገባች ገና ሁለት አመት ብቻ ያስቆጠረችው ኢትዮጵያዊት የአሲድ ጥቃት የተፈጸመባት በደባልነት በሚኖር ግለሰብ እንደሆነም ኒውስ ፎር ቴሌቪዥን በዘገባው አመልክቷል። ሰላማዊት ተፈራ የተባለችውን ኢትዮጵያዊት ከሳምንት በፊት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 24/2018 ከምሽቱ 1 ሰአት ከ30 አካባቢ ሰልፈሪክ አሲድ ...

Read More »