ኒኮላስ ሳርኮዚ በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2018) የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ወደ ወህኒ ለመጋዝ ምክንያት የሆነባቸው ከቀድሞው የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙአመር ጋዳፊ መንግስት ለምርጫ ዘመቻ በሚሊየን ዮሮ የሚቆጠር ገንዘብ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ተቀብለዋል በሚል ነው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2007 ለተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊየን ዩሮ ተቀብለዋል በሚል የተወነጀሉት ሳርኮዚ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ ምርመራ ሲካሄድባቸው ...

Read More »

የትግራይ ተወላጆች ወደ አድዋና አካባቢው እየተመለሱ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) ከአማራ ክልል ባህርዳር የትግራይ ተወላጆች ንብረታቸውን ሸጠው ወደ አድዋና አካባቢው እየተመለሱ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በባህርዳር ኢትዮ ስታር ተብሎ በትግራይ ተወላጅ ንብረትነት  የሚታወቀውን ሆቴል የጎጃም አዴት ተወላጅ የሆኑትና  የሙሉጌታ ሪል ስቴት ባለቤት እንድገዙት  ታውቋል። አባ አድጎይ ተብለው የሚታወቁትን ኤርትራዊ ቤተሰቦች በማፈናቀል ቦታውን በተጭበረበረ መንገድ በሊዝ የወሰደው የትግራይ ተወላጅም ይዞታውን ሸጦ መቀሌ ገብቷል። ኢትዮ ስታር ሆቴል ከጣና ሃይቅ ...

Read More »

አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመርን ማስቀጠል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመርን ማጠናከርና ማስቀጠል አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የኢሕአዴግ ስራአስፈጻሚ ገለጸ። የኢህአዴግ ስራአስፈጻሚ ለ8 ቀናት ያካሄደውን የስራ አስፈጻሚ ግምገማ አጠናቆ የድርጅቱን አጠቃላይ የምክርቤት ስብሰባ ጀምሯል። ስራአስፈጻሚው ስብሰባውን ሲያጠናቀቅ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ታዲያ በአመራሩ መካከል የነበረው የአመለካከት ልዩነት ወደ ተሻለ አንድነት እንዲመጣ አቅጣጫ ተቀምጧል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመርን በሚያጠናከር መልኩ በአመራሩ መካከል የአመለካከት ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ተራዘመ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለአንድ ሳምንት መራዘሙ ተገለጸ። በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ላይ ውጤታማ የተባለውን ዘመቻ በሌሎች አካባቢዎችም ለማስፋፋት በሚል የተራዘመው ዘመቻ ሌሎች እንቅስቃሴዎችም በተጓዳኝ እንደሚኖሩት ታውቋል። በአንድ ሳምንቱ ዘመቻ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር የተቻለ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ነዳጅ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገባ፣ በሀገር ውስጥም የነዳጅ ማመላለሺያ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርገውን ዘመቻ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ጋምቤላ ቤንሻንጉልና ሌሎች ...

Read More »

በሶማሊያ የሚገኙ ሁለት ጎሳዎች አለመግባባታቸውን ለማስወገድ ተስማሙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) በሶማሊያ የሚገኙ ሁለት ጎሳዎች በመካከላቸው የቆየውን አለመግባባት ለማስወገድ መስማማታቸው ተሰማ። ሳዳ ዮኒስና በኢዶ በተባሉት ጎሳዎች መካከል ለረጅም አመታት የቆየውን የእርስ በርስ ግጭት ለማስቆም  ሶስት ሳምንታትን የፈጀ ውይይት መደረጉም ታውቋል። ሳዳ ዮኒስና በኢዶ በተባሉት ጎሳዎች መካከል ለረጅም አመታት በቆየው ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሲዘገብ ቆይቷል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ የጎሳ መሪዎቹ ለሶስት ሳምንታት  ውይይት ማድረጋቸውንና በሰላም ለመኖር ከስምምነት ...

Read More »

የእምቦጭ አረምን ለመከላከል 140ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010)ጤና ለጣና በሚል እምቦጭ አረምን ለመከላከል በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ በአንድ ቀን ብቻ 140ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ። በዝግጅቱ ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በመድረኩ በርካታ ታዋቂ ድምጻውያንና ኮመዲያን ተገኝተው ለዝግጅቱ ድምቀት ሰጥተውታል። የዝግጅቱ አስተባባሪ አለም አቀፍ ትብብር የጣና መልሶ ማልማት ድርጅት ሰብሳቢ ዶክተር ሰለሞን ክብረት ጣናን ከጥፋት ለመታደግ የባለሙያዎች ቡድን የጥናትና የቴክኒክ እገዛ ማድረጉንና ...

Read More »

በዋልድባ መነኮሳት ችሎት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገኙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) ዛሬ በዋለው የዋልድባ መነኮሳት ችሎት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መገኘታቸው ታወቀ። አጋርነትን ለማሳየት በተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የዋልድባ አባቶች መደሰታቸውን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል። በካቴና እጆቻቸው አንድ ላይ ታስረው የሚታዩበት ፎቶግራፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ቁጣ መነሳቱም ታውቋል። በችሎቱ አካባቢ ፎቶግራፍ አንስታችኋል ተብለው የታሰሩ እንዳሉም ተገልጿል። በአባቶቹ ላይ እየተፈጸመ ያለው ስቃይ እንዲቆም ...

Read More »

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ነገ ስብሰባውን ይጀምራል

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) የኢሕአዴግ ምክር ቤት ቀጣዪን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ ከነገ ጀምሮ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው። በስብሰባው የግንባሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመረጥም ተነግሯል። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ማንን ለማስመረጥ እደወሰነ ግን የተገለጸና የታወቀ ነገር የለም። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ስለመጠናቀቁም የተሰጠ መግለጫ የለም። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያካሄደውን ስብሰባ ማጠናቀቁ ይነገራል። ስራ አስፈጻሚው ሰሞኑን ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ የግምገማ ...

Read More »

ነዳጅን የማስተጓጎሉ የመጨረሻ ቀን ዘመቻ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተጠራው የማስተጓጎል ዘመቻ በመጨረሻ ቀኑ ዛሬም በመካሄድ ላይ ነው። በሰሜን ጎንደር ሸሃዲ አካባቢ በአንድ የነዳጅ ማመላለሺያ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በአንድ ሳምንት ግዜ ወስጥ የተቃጠሉ የነዳጅ ቦቴዎች ቁጥር ሶስት ደርሷል። በአዲስ አበባ የነዳጅ አቅርቦት ባለመኖሩ  ጥቂት የማይባሉ ማደያዎች ዝግ ሆነው መዋላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በጎንደር ነዳጅ ለማግኘት ታክሲዎች ረጅም ሰልፍ ይዘው መቆየታቸውንም የደረሰን መረጃ ...

Read More »

ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ ጨመረ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ መጨመሩን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ። የነዳጅ እቀባ ጥሪውን ተከትሎ ስጋት የገባቸው የነዳጅ ቦቴ ሾፌሮች  በአንዳንድ ቦታዎች መቆማቸውንም የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ለመንግስትና ለፓርቲ መገናኛ ብዙሃን አምነዋል። የሞያሌ ነዋሪዎች ወደ ኬንያ የተሰደዱት ደግሞ ኦነግ በነዛው ውዥንብር ነው ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ...

Read More »