በ10 ዩኒቨርስቲዎች ብቻ የ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጉድለት ተገኘ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2010)ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ10 ዩኒቨርስቲዎች ብቻ የ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጉድለት መኖሩን የጠቅላላ ኦዲት ቢሮ ገለጸ። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ብቻ 64 ሚሊየን ብር ጉድለት በመኖሩ በፓርላማ የመንግስት ወጭ አስተዳደርና ቁጥጥር ኮሚቴ ተቋሙን መገሰጹ ታውቋል። በኢትዮጵያ ካሉ 158 የመንግስት ተቋማት ብቻ ባለፈው አመት የ20 ቢሊየን ብር ጉድለት መገኘቱን የጠቅላላ ኦዲት ቢሮ መግለጹ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ...

Read More »

የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር የዋና የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሎአል

የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ንግግር የዋና የመነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ የጠ/ሚኒስትርነት ሹመቱን ሲቀበሉ ያደረጉት ንግግር በማህበራዊ ሚዲያውም ሆነ ከማህበራዊ ሚዲያው ውጭ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በንግግሩ መደሰታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እየገለጹ መሆኑን ወኪሎቻችን ያደረሱን ሪፖርት ያመለክታል። በተለይ የኢትዮጵአን ታሪክና የአገር አንድነትን አስመልክቶ ያቀረቡት ንግግር ለብዙ ኢትዮጵያውያን የደስታ ስሜት የሰጠ መሆኑን ...

Read More »

በተወሰኑ ክሶች አቶ መላኩ ፋንታን ነጻ ያሉት ዳኞች ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ደረሳቸው

በተወሰኑ ክሶች አቶ መላኩ ፋንታን ነጻ ያሉት ዳኞች ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ደረሳቸው (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ አቶ መላኩ ፋንታ በተወሰኑ ክሶች ነጻ እንደተባሉ፣ ደህንነቶች ዳኞችንና የዳኞቹን ፕሬዝዳንት ጭምር በመሰብሰብ እንዳነጋገሯቸው፣ “ ለምንድነው ነፃ የላችሁት?” የሚል ጥያቄ እንደጠየቁዋቸው ምንጮች ገልጸዋል። ዳኞቹ “ ሰውየው ከታሰረ ረጅም አመት ነው፣ ክሱን በደንብ አይተን የሚያስፈርድበት ሆኖ አላገኘነውም” ...

Read More »

የካናዳ መንግስት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አስቸኳይ አዋጁን በማንሳት፣ እስረኞችን በመፍታት ሁሉን አቀፍ ለውጦች እንዲያደርጉ ጠየቀ

የካናዳ መንግስት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አስቸኳይ አዋጁን በማንሳት፣ እስረኞችን በመፍታት ሁሉን አቀፍ ለውጦች እንዲያደርጉ ጠየቀ (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የካናዳ ኤምባሲ የአዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድን ሹመት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ለሁሉም የአገሪቱ ዜጎች ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ምኅዳሩን በማስፋት መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ ...

Read More »

በዶ/ር አብይ አህመድ የሹሙት ስነስርዓት ላይ አንዳንድ እንግዳ ነገሮች ተፈጥረው እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ወገኖች ገልጹ

በዶ/ር አብይ አህመድ የሹሙት ስነስርዓት ላይ አንዳንድ እንግዳ ነገሮች ተፈጥረው እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ወገኖች ገልጹ (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) “አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ተመርጦ ከማየው ብሞት ይሻለኛል” ብለው አብይ አህመድ በተገኙበት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ የተናገሩት የመንግስት የፓርላማ ተጠሪው አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ በበአሉ ላይ መገኘታቸው ብዙዎችን አስገርሞ ነበር። የህወሃት ዋና ዋና የሚባሉ አመራሮች ...

Read More »

የትግራይ ክልል ምሁር የዶክተር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቃወሙ።

የትግራይ ክልል ምሁር የዶክተር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቃወሙ። (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ጉዳዩን አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቃለ ምልልስ የሰጡት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ምሁር ፣ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ብለው ፈጽሞ እንዳልጠበቁ በመጥቀስ በምርጫው ቅሬታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል። በህዝባዊ አመጹ ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲደርስ አላወገዙም በማለት ዶክተር አብይን የከሠሱት እኚሁ ምሁር፣ ከዶክተር ...

Read More »

በእስራኤል ከ16ሺ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010) እስራኤል ወደ ሀገራቸው ልትመልሳቸው የነበሩ ከ16ሺ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ መወሰኗን አስታወቀች። ለደህንነታቸው ሰግተውና ከሃገራቸው ሸሽተው በእስራኤል ጥገኝነት ጠይቀው የሚገኙ  ስደተኞች የኢኮኖሚ ስደተኞች ናቸው በሚል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖ እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እንዳሉት ስደተኞቹን ወደ ሌላ ምዕራባውያን ሀገራት ለማስፈር እንደተወሰነ ገልጸዋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ኤርትራውያን መሆናቸው የሚነገረው አፍሪካውያኑ ስደተኞች በግብጽ ...

Read More »

ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)የደቡብ አፍሪካ የጸረ አፓርታይድ ታጋይና የቀድሞ የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት ወይዘሮ ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በ81 አመታቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ኔልሰን ማንዴላ ከ27 አመታት በኋላ ከእስር ሲለቀቁ ዊኒ ማንዴላ ከነጻናአ ታጋዩ ጋር ግንኑነታቸው ስላልተቋረጠ ዝናቸው ከፍተኛ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል። በኋላ ላይ ግን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ሲለያዩ በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ሕይወታቸው ዝናቸው ...

Read More »

አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፌን እሰጣለሁ አለች

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት፣እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች የደስታ መግለጫ አስተላለፉ። ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለች። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥሪዋን አቅርባለች። አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩልም ባወጣቸው መግለጫ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት አፋጣኝ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን እንዲያመጣ ድጋፍ እንደምትሰጥ የገለጸችው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የአስቸኳይ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ዘረኝነትና መከፋፈልን ማጥፋት ይገባል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)በኢትዮጵያ ዘረኝነትና መከፋፈልን ማጥፋት እንደሚገባ በፓርላማ የሃገር መሪነትን ስልጣን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ። ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ወደ እድልና መልካም አጋጣሚ መቀየር እንደሚገባ ዶክተር አብይ ለፓርላማው በስልጣን ርክክብ ስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል። ካለፉት 27 አመታት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግ ያወደሱት ዶክተር አብይ ሰብአዊነት ያለው ንግግር በማድረግ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፈዋል። ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ...

Read More »