የስቅለት በአል ተከብሮ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 28/2010) የስቅለት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደመቀ ስነስርዓት ተከብሮ ዋለ ። በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በዓሉ በጾም፣በጸሎትና በስግደት ተከብሮ ውሏል። በየዓመቱ የሚከበረው የስቀለት በዓል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት እለት ነው የእምነቱ ተከታዮች እለቱን በድምቀት ሲያከብሩት አምላክ ለሰው ልጅ የከፈለውን እዳ በማሰብ እንደሆነ ይገልጻሉ። በመጽሀፍ ቅዱስ ኢየሱስንም ያዙት መስቀሉንም አሸክመው በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ...

Read More »

ኳታር በአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ተጋበዘች

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010)በገልፍ ሃገራት ውስጥ በገባው የፖለቲካ ቀውስ  በበርካታዎቹ የአካባቢው  ሃገራት መገለል የገጠማት ኳታር በአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ተጋበዘች። በተለይም ክሳኡዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኤምሪት ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ የቆየችው ኳታር  በሳኦዲ አረቢያ በሚካሄደው የአረብ ሊግ ስበሰባ ላይ እንድትገኝ ከሳኡዲ አረቢያ የቀረበውን ግብዣ   የተቀበለች ሲሆን ፣በሚሄዱት ልኡካን ደረጃ ላይ ግን  ውሳኔ  አለማሳለፏምንም አስታውቃለች። እንዳውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 15 /2018 በሳኡዲ አረቢያ ...

Read More »

ከኢትዮጵያ ተዘርፈው የተወሰዱ ቅርሶች በአደራ መልክ ሊመለሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010) በእንግሊዝ ሃይሎች ከኢትዮጵያ ተዘርፈው የተወሰዱ ቅርሶች በአደራ መልክ ሊመለሱ መሆኑ ተነገረ። አንድ ክፍለ ዘመን ሙሉ በእንግሊዝ ተዘርፈው የቆዩት የኢትዮጵያ ቅርሶች በእዳ መልክ ለተወሰነ ጊዜ ተመላሽ እንደሚደረጉ ታውቋል። በእንግሊዝ ሙዚየም የሚገኙ እነዚሁ ቅርሶች በአጼ ቴድሮስ ጊዜ ከመቅደላ የተዘረፉ መሆናቸውም ተነግሯል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1868 እንግሊዞች በአጼ ቴድሮስ የታሰሩ ዜጎቻቸውን ለማስለቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ሲዘምቱ የተመዘበሩ ቅርሶች በርካታ ናቸው። አጼ ...

Read More »

ሜጄር ጄኔራል ገብሬ አድሃና በአብዬ ግዛት ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010) ሜጄር ጄኔራል ገብሬ አድሃና በአብዬ ግዛት የሰላም አስከባሪው አዛዥ ሆነው በተባበሩት መንግስታት መሾማቸው ተገለጸ። የሕወሃቱ ታጋይ ጄኔራል ገብሬ አድሃና የሚተኩት ሌላውን የሕወሃት ታጋይ ሜጄር ጄኔራል ተስፋዬ ግደይን እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል። የዚህ ተልዕኮ ምክትል አዛዥ ሆነው ተሹመው በመስራት ላይ የሚገኙትም ሌላዋ የሕወሃት ታጋይ ብርጋዴር ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ ናቸው ። ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡበት አቢዬ ግዛት ከተሰማራው 4ሺ ያህል ...

Read More »

ሕዝቡ የጀመረውን እምቢተኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010)የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመረውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት አጠናክሮ እንዲቀጥል አለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል ጥሪ አቀረበ። በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም የጀመሩትን የዲፕሎማሲ እና የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ትግሉን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቋል። አለም አቀፉ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል ባወጣው መግለጫ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተስፋና በስጋት ጊዜ ላይ ይገኛል። በኢሕአዴግ ውስጥ የለውጥ አቀንቃኝነት ዝንባሌ ያላቸው ፖለቲከኞች ወደ ፊት አመራርነት መምጣታቸው እንደ ተስፋ ይታያል ነው ...

Read More »

በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ለማስፈታት የተደረገው ዘመቻ ውጤታማ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 27/2010)በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ለማስፈታት የተደረገው ዘመቻ ውጤታማ አለመሆኑን ተከትሎ ለሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ጥሪ መደረጉ ተሰማ። ወደየቤተሰቦቻቸው የተበተኑት የሚሊሺያ አባላቱ በኮማንድ ፖስቱ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ መሳሪያ ወደ ማስፈታት ዘመቻ እንዲገቡ መታቀዱን የኢሳት ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የህወሀት አገዛዝ የአማራ ተወላጆችን በጦር መሳሪያ ማስፈታት ዘመቻ እርስ በእርስ ለማጋጨት ያቀደው ሴራ በመሆኑ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል። የህዝባዊ ወያኔ ...

Read More »

የሶማሊው ፕሬዚዳንት አንቀጽ 39ን ተግባራዊ አደርገዋለሁ እያሉ በመዛት ላይ ናቸው

የሶማሊው ፕሬዚዳንት አንቀጽ 39ን ተግባራዊ አደርገዋለሁ እያሉ በመዛት ላይ ናቸው (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ደስተኛ ያልሆኑት የህወሃቱ ቀኝ እጅ አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የህገ መንግስቱን አንቀጽ 39ን በመጥቀስ የመገንጠል ጥያቄ አቀርባለሁ በማለት እየዛቱ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩ የክልሉ አገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ፖለቲከኞች ወደ ጅጅጋ የተጠሩ ሲሆን፣ የልዩ ሃይል አዛዦች፣ የልዩ ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 11 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ተፈቱ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 11 ታዋቂ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ተፈቱ (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓም ታስረው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ አዲሱ ጌታሁን፣ ጦማሪ ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን፣ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሃይሉ፣ ወ/ት ወይንሸት ሞላ፣ ስንታየሁ ቸኮልና ተፈራ ተስፋዬ ዛሬ ተለቀዋል። ትናንት በመታወቂ ዋስ እንደሚፈቱ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ...

Read More »

ኦነግ የዶ/ር አብይን መመረጥ ወያኔ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ለማስፋፋት የወጠነው ማባበያ ነው አለ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል

ኦነግ የዶ/ር አብይን መመረጥ ወያኔ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ለማስፋፋት የወጠነው ማባበያ ነው አለ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ኦነግ በመግለጫው በ27 ዓመታት ኢህአዴግ ስርዓት አገዛዝ ዘመን ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ችግር አለመፈታቱንና ወደ ባሰ ሁኔታ መሸጋገሩን ገልጾ፣ የወያኔ ስርዓት አስተማማኝ መፍትሄ ለማግኘት ከመስራት ይልቅ በማባበያና እውን በማይሆን ተስፋ ዓላመውን ማሳከቱን መርጧል ብሎአል። ...

Read More »

የሰሜን ጎንደር የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የዘር ፍሬያቸውን በመመታታቸው ለህመም እንደተዳረጉ ተናገሩ

የሰሜን ጎንደር የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የዘር ፍሬያቸውን በመመታታቸው ለህመም እንደተዳረጉ ተናገሩ (ኢሳት ዜና መጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) አቶ ሙላት ፍሰሃ እንደተናገሩት በጎንደር የተካሄደውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ተይዘው ከታሰሩ በሁዋላ በማዕከላዊ እስር ቤት ሌሊት ሌሊት እየተጠሩ መደብደባቸውን ተናገሩ። “ቴዲ ከሚባል ሽፍታ ጋር ተገናኝተሃል፣ ከአርበኞች ግንቦት7 አመራሮች ጋር በመገናኘት በጎንደር ማረሚያ ቤት ላይ ጥቃት ልትፈጽም ነበር” ...

Read More »