ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2009 ዓ.ም የስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ 325 በእስር ላይ የነበሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። አሃዙ በቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት የጋዩት እና በጥይት የተገደሉን እንዲሁም በብርሸለቆ እና በሰባት አሚት እስር ቤት በግፍ የተገደሉ እስረኞችን ያካተተ ነው። ይሁን እንጅ አሃዙ በየቀበሌው ያሉትን ጊዚያዊ እስር ቤቶችን መረጃ አላካተተም። ከ325 ሟች እስረኞች መካከል 49 ኙ ...
Read More »Amsterdam
የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ከሽፏል ተባለ
ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመንና በበርካታ የሶሻሊስት አገሮች ሲሰራበት የነበረው የመንግስት ሰራተኛውን በአንድ ለአምስት አደራጅቶ የመቆጣጠርና የመምራት አሰራር መክሸፉን አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል። ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ አመራር አካዳሚ በተደረገ ስብሰባ ላይ የአካዳሚው ዳይሬክተር፣ የመንግስት ሠራተኛው የአንድ ለአምስትን ስብሰባን “መቼ ነው አላቆኝ የማየው?” በማለት በምሬት እስከ መግለጽ ደርሷል ብለዋል፡፡የዚህ ዓይነት ጥላቻ ...
Read More »በአማራ ክልል ብቻ ከ66 ሺ በላይ ዜጎች በማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ
ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እንዳስታወቀው በክልሉ 66 ሽህ 102 ዜጎች በፍርድ እና ያለፍርድ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። በክልሉ የእስረኛው ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ በመሄዱ የክልሉ ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡበት ጠይቋል። እስረኞቹን ለማስተናገድ የተበጀተው በጀት ማለቁንም ኮሚሽኑ አስታውቋል። እስረኞቹ በአማካኝ ከ5 እስከ 10 ዓመታት በፍርድ ወይም ያለፍርድ በእስር እንደሚማቅቁ የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ክልሉ ...
Read More »የተቅማጥ (አተት በሽታ) በመላ አገሪቱ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል
ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ከሚታየው ድርቅና የንጽህና ጉድለት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ከፍተኛ ስጋር ፈጥሯል። በአዲስ አበባ የበሽታው ስርጭት እየቀነሰ ነው ቢባልም፣ በዚህ ሳምንት ብቻ 25 በሽተኞች ህክምና ማግኘታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአማራ ክልል በ21 ወረዳዎች ፣ በትግራይ 5 ወረዳዎች ፣ በኦሮሚያ 16 ወረዳዎች ...
Read More »የከተሞች የምግብ ዋስትና መጓተት በገዢው ፓርቲና በአለም ባንክ መካከል አለመግባባትን ፈጠረ
ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ‹‹የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮግራም በከተማ ኗሪ የሆኑ ‹‹በሚቀጥሉት 10 አመታት ከአጠቃላይ ድህነት ወለል በታች ያሉ 90 በመቶ የሚሆኑ ስራ አጦችን እንዲሁም ለማህበራዊ ኑሮ ችግርና ጠንቅ የተጋለጡ ዜጎች ወደ ስራ እንዲሰማሩና 10 በመቶ የሚሆኑት የመስራት አቅም የሌላቸው የማህበራዊ ጠንቅ ሰለባዎች የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኙ›› የሚል አላማ ይዞ በ2005 ...
Read More »በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እና 10 የመልሶ ማልማት ‹‹መሰረት ድንጋይ ›› ሳይቀመጥ ቀረ
ሚያዝያ ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኝ 10 ሺህ ካሬ/አንድ ሄክታር/ ለሆቴል ግንባታ በካሬ 650 ሺህ ብር ሊዝ የገዙት የኳታሩ ባለሃብት ፣ አገዛዙ ቦታው ላይ የሰፈሩትን ነዋሪዎች በሙሉ አንስቶ ቦታውን አጽድቶ መጨረሱን በመግለጽ የመሰረት ድንጋይ እንዲያስቀምጡ ቢጋብዝም፣ ባለሃብቱ ግን ‹‹ህዝብ ተፈናቅሎ እያለቀሰ ባለበት ሰአት የመሰረት ድንጋይ አላስቀምጥም›› ማለታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የገዢው ፓርቲ ...
Read More »በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ
ሚያዝያ ፲፩ (አሥራ አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የቦንብ ፍንዳታን ባስተናገደችው ጎንደር፣ ማክሰኞ ምሽት 2 ሰአት አካባቢ ታክሲ ማዞሪያ በጌምድር ሆቴል አካባቢ ቦንብ መፈንዳቱን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በፍንዳታው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የሚገለጹት እማኞች፣ በፍንዳታው ወቅት ከፍተኛ ድምጽ ከመሰማቱ ጋር ተያይዞ በአካባቢ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር ብለዋል። የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከ15 ...
Read More »በእስር ቤት ለወራት ታስረው የሚገኙ የነጻነት ታጋዮች ለችግር ታድርገዋል
ሚያዝያ ፲፩ (አሥራ አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉና የእስረኞችን ሁኔታ የሚከታተሉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ለመብታቸው በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ገብተው ሲታገሉ የነበሩ፣ በግላቸው በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲያጋልጡ እንዲሁም በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርተው ለአገራቸው የሚችሉትን መስዋትነት በመክፈል ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ከሚደርስባቸው ስቃይ በተጨማሪ፣ መሰረታዊ የሚባሉትን ልብስ እና ጫማዎችን ለመቀየር አልቻሉም። ከአማራ ...
Read More »አቶ መኳንንት ካሳሁን በማእከላዊ ድብደባው እንዲቆምለት ፍርድ ቤቱን ጠየቀ
ሚያዝያ ፲፩ (አሥራ አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ብስራት አቢ እና ደቡብ ወሎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ መኳንንት ካሳሁን ከደሴ ከተማ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ ከአንድ ወር ከ5 ቀን በኋላ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። አቶ መኳንንት ካሳሁን ሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. አራዳ በሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ክቡር ፍርድ ...
Read More »የደህንነት ሰራተኛው ለኢሳት ሚስጢራዊ መረጃ ሰጥተሃል በሚል ታስሮ እየተሰቃየ ነው
ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ኢጄንሲ (ኢንሳ) ውስጥ የደህንነት ሰራተኛ የሆነው ጸጋየ ተክሉ የተባለ ግለሰብ ለኢሳት መረጃ ታቀብላለህ በሚል በቂሊንጦ እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል። ጸጋዬ በ2003 ዓም በመረጃ መረብ ውስጥ በሚሰራበት ወቅት ከኢሳት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የድርጅቱን ሚስጢር ለኢሳት ሰጥቷል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፣ በማስረጃነትም ኢሳት ከሌላ ግለሰብ ጋር ያደረገውና የራሱ ...
Read More »