Amsterdam

የሶማሊ ልዩ የሚሊሺያ አባላት የደሞዝ ጭማሪ ጠየቁ። ታጣቂዎቹ ትእዛዝ ለመቀበል ፈቀዳኛ አለመሆናቸውንም አስታውቀዋል

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከ200 ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆችን በመግደላቸው እየተወነጀሉ ያሉት በአቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የሚመሩት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያ አባላት ፣የደረሰባቸውን ጥቃት ተከትሎ፣ የጉዳት ካሳና ደሞዝ ካልተጨመራቸው ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል። የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ለመዝመት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወደ አካባቢው በቅርቡ የተጓዙት አዲስ የተሾሙት የደህንነት አባል መከላከያው የልዩ ሃይሉን ቦታ ...

Read More »

በደቡብ ጎንደር ዞን ዜጎች በብዛት እየታሰሩ ነው

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ ወዲህ በተለያዩ ሰበቦች በርካታ ዜጎች እየታፈሱ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። የማሰር ዘመቻው ወደ ካህናቱም ወርዶ በትናንትናው እለት በአንዳቤት ወረዳ በርካታ ካህናት ቤተክርስቲያን ማስተዳደር አልቻላችሁም ተብለው ታስረዋል። የደቡብ ጎንደር ሃገረ ሰብከት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት መላከ ሰላም አባ ሃይለየሱስ ቢያድግልኝ መታሰራቸውንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የእርሳቸው መታሰር የአካባቢውን ...

Read More »

አራተኛው የህዝብ ቆጠራ ህዳር ወር ላይ ይካሄዳል ተባለ

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በመጪው ዓመት ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ አራተኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ እንደሚያካሂድ የኮምሽኑ ምንጮች ገለጹ። የሕዝብና ቤት ቆጠራ በ10 ዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን ኮምሽኑ በ1999/2000 ዓ.ም ያካሄደው ሶስተኛው ቆጠራ የብአዴን/ኢህአዴግ የፓርላማ አባላትን ጭምሮ በርካታ ዜጎችን ያስቆጣ ነበር። ኮምሽኑ ህዳር 25 ቀን 2001 ዓ.ም 3ኛውን የሕዝብና ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዓለማቀፉ ፕሬስ ኢንስቲትዩት የ2017 የፕሬስ ጀግኖች ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለማቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት በምህጻረ ቃሉ- አይ ፒ አይ ይፋ እንዳደረገው፤69ኛውን የዓላማችን የፕሬስ ጀግኖች ሽልማት ፣ ፕሬስን ለማፈን የወጣውን የጸረ ሽብርተኝነት ህጉን በመተቸቱ ምክንያት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና ጦማሪ እስክንድር ነጋ አሸንፏል። አይ ፒ አይ ዛሬ ባወጣው በዚሁ መግለጫ የአፍጋኒስታን ጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ የነጻ ሚዲያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ድርቅ ተከትሎ 16 ሺ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸው ተዘገበ

ሚያዝያ ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኘው ዶሎ ዞን በ30 አመት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ ምክያት በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 16 ሺ ሰዎች መያዛቸውንና በየወሩም ከ3 ሺ 500 በላይ ሰዎች ወደ ህክምና ማእከል እንደሚገቡ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከሆነ ወረርሽኙን ለመከላከል 1ሺ 200 ባለሞያዎች በ100 ጣቢያዎች አገልግሎት ለመስጠት ቢሞክሩም፣ ባካባቢው የመሰረተ ...

Read More »

በአማራ ክልል በተለያዩ የፍትህ እጦት በቀን ከ5 እስከ 11 ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ

ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ወኪላችን የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ እና ፖሊሶች በየቀኑ የሚለዋወጡ የስልክ መረጃዎችን ተንተርሳ ባጠናቀረችው መረጃ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከፍትህ መጓደል፣ ከመሬት ጋር በሚነሳ አምባጓሮ ፣ ድህነትና ስራ አጥነት ፣ ሙስናና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በሚፈጠሩ አለመግባባቶች እንዲሁም ፖሊሶችና ወታደሮች በሚወስዱዋቸው እርምጃዎች ከሰኞ እስከ ሃሙስ በአሉት ቀናት ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ህጻናት በጎርፍ ተወሰዱ

ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጅንካ አዋሳኝ በሆነው በካይሳ ቀበሌ ቅዳሜ ሚያዚያ 14/2009 ከሰዓት በኋላ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ አቶ ታደሰ የተባሉ የቀበሌው ነዋሪ ሁለት ልጆች፣ የታናሽ ወንድማችው አንድ ልጅ፣ እንዲሁም የጎረቤታቸው አንድ ልጅ በአጠቃላይ አራት ህጻናት በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የጎርፍ አደጋው የደረሰው የዞኑ ግብርና ቢሮ ከቀበሌው ...

Read More »

አዲስ የተሾሙት አመራሮች በቡድን ተደራጀው በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ እየተመደቡ ያሉ አመራሮች በቡድን ተደራጅተው በህብረተሰቡ ላይ ችግሮችን በመፍጠር ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት የአዴት ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ እማመይ አለባቸው፣ ከቀበሌ ሁለት አመራር ጀምሮ እስከ ከንቲባው ድረስ ህዝብን በማመስ ማስቸገር እንጅ ምንም አይነት ስራ ሲሰሩ አይታዩም ይላሉ። ከአሁን በፊት በብአዴን አባልነት ይሳተፉ እንደነበር የገለጹት ቅሬታ አቅራቢ ስርዓቱ ሙሰኝነት የተንሰራፋበት በመሆኑ በዚህ ...

Read More »

ታዋቂው ጸሃፊ የፖለቲካ ሰውና የህግ ባለሙያ አቶ አሰፋ ጫቦ አረፉ

ሚያዝያ ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አሰፋ ጫቦ ከአባታቸው አቶ ሰዴ ሃማ ከእናታቸው ወ/ሮ ማቱኬ አጆ በቀድሞው አጠራር በጋሞጎፋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በጨንቻ ከተማ 1936 ዓ.ም ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በቤተክህነት ውስጥ ፊደል በመቁጠር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን እስከ ድቁና ማእረግ በመድረስ አገልግለዋል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጨንቻ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ደግሞ ሻሸመኔ እና አዲስ አበባ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የነጻነት ታጋዮች የሚፈጽሙት ጥቃት ቀጥሎአል

ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 አባላት የሆኑ ታጋዮች በደምቢያ ወረዳ ሰረባ መስኖ አጠገብ ሌሊት ላይ ጥቃት ፈጽመው፣ 2 ገልባጭ መኪኖችና አንድ እስካቫተር መኪና የተቃጠሉ ሲሆን፣ በታጋዮች እና ድርጅቱን በሚጠብቁት መካከል ለ30 ደቂቃ ያክል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንና አንድ ወታደር መገደሉን ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል። ኢሳት ወደ አካባቢው ነዋሪዎች ስልክ በመደወል በመኪኖች ላይ ከፍተኛ ...

Read More »