Amsterdam

ሂልተን ሆቴል ሊሸጥ ነው

ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለአምስት ኮከብ ሆቴል የነበረውን ሒልተን ሆቴል ሊሸጥ መሆኑን ሳምንታዊው ሪፖርተር ዘግቧል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የሂልተንን ሽያጭ አስመልክቶ ከሦስት ወራት በኋላ ጨረታ ያወጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከአሥርያላነሱ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እየተጠባበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ሂልተን አዲስ አበባን ለመግዛት ፍላጎት ...

Read More »

የደሴ ከተማ በተከታታይ ጎርፍ እየተጠቃች መሆኗን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት በተለይ ከሰሞኑ የሚጥለው ተከታታይ ዝናም እየስከተለ ባለው ከባድ ጎርፍ ቤታቸው በመጥለቅለቁ በርካታ ንብረት እየወደመባቸው ይገኛል። ጉዳዩን አስመልክቶ ለአካባቢው መስተዳድር አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ጊዜያዊም ሆነ ዘላቂ ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን የሚናገሩት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ አንዳንዶች ጎርፉ ክፉኛ ቤታቸው ዘልቆ በመግባቱ መኖሪያቸውን ጥለው በየዘመዶቻቸው ቤት መጠለላቸውን ይገልጻሉ። ከዚህም ...

Read More »

አልሸባብ በኢትዮ ሶማሌ ድንበር ላይ በምትገኘውን ስልታዊዋ የዋጅድ ከተማ ላይ ጥቃት ፈጸመ

ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተሽከርካሪ ላይ የተጠመዱ ከባድ መሳሪያዎችን የጫኑ የአልሸባብ ሚሊሻዎች በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የምትገኘውን ስልታዊዋን የዋጅድ ከተማ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውንም የሶማሊያ ወታደራዊ ባለስልጣናት እሁድ እለት አስታወቁ። በቦቆል ግዛት ውስጥ በደቡባዊ ምእራብ ሶማሊያ ከሞቃዲሾ 305 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ቤዝ ላይም ጥቃት ፈጽመዋል። ...

Read More »

በበለና እና በአማሮ ወረዳዎች መካከል በተነሳ ግጭት የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በደቡብ አካባቢ በሰገን ዞን በአማሮ ወረዳ እና አጎራባች በሆነው በጉጂ ዞን ውስጥ በሚገኘው በላና ወረዳ በተነሳ ግጭት የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው። በአካባቢው የተነሳውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦች ለእንስሳት መኖና ውሃ በማጣታቸው ከአካባቢው አካባቢ መሰደዳቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ከተጀመረበት ካለፉት 4 ...

Read More »

የይርጋለም መምህራን ለአባይ ቦንድ በግዳጅ እንዲገዙ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በይርጋለም ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለአባይ ግድብ ግንባታ በግዳጅ እንዲያወጡ መጠየቃቸውን ከተቃወሙ በሁዋላ፣ ዛሬ አርብ ደግሞ የይርጋለም መምህራን ለግድቡ እንዲያዋጡ የተጠየቁ ቢሆንም፣ መምህራን ተቃውመውታል። “መምህራኑ እኛ ያለን ዲግሪ ነው፣ ወረቀት ነው፣ ለራሳችን የሚሆን ፍጆታም የለንም” በማለት ተቃውመውታል። የካቢኔ ስብሰባ ላይ “የመንግስት ባለስልጣናትን ልብሳቸውንና ሰውነታቸውን ብታዩት ደረጃውን የጠበቀ ነው፣ ማሰብ ግን ...

Read More »

የተመድ የሰብዓዊ መብት ካውንስል ሃላፊ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ዋና አዛዥ የሆኑት ዘይድ ራድ አል ሁሴኒ በመጪው ሳምንት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ድርጅቱ አስታውቋል። የእሳቸው ጉብኝት ከመካሄዱ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያለቁበት ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበውን ጥያቄ፣ ...

Read More »

በሶማሊያ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የኬንያ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ከመጠን በላይ ሃይል ተጠቅመው ዜጎችን መግደላቸውን ሪፖርቶች አጋለጡ

ሚያዝያ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬኒያ እና ኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ለማደን በሚል ምክንያት ድንበር አቆራርጠው ወደ ሶማሊያ ግዛት በመግባት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከመጠን በላይ የሆነ የሃይል እርምጃዎችን መውሰዳቸውን በሶማሊያ የተሰማሩ የረድኤት ድርጅቶች ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ባቀረቡት ሪፖርቶች አጋልጠዋል። በሶማሊያ ጌዶ ግዛት ውስጥ ከ2015 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የኬንያ አየር ሃይል፣ አርብቶ አደሮች በተሰማሩባቸው አካባቢዎች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜያት ድንበር ...

Read More »

በአርባምንጭ ገዢው ፓርቲ የሚያሰማው የቦንድ ግዢ ቅስቀሳ ሰሚ አላገኘም

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት የአባይ ግድብ ዋንጫ ወደ ከተማው ይመጣል በሚል ህዝቡ ዋንጫውን እንዲቀበል የገንዘብ መዋጮና የቦንድ ግዢ እንዲፈጽም ቢጠየቅም፣ ከህዝቡ የተገኘው ምላሽ ዝቅተኛ ነው። ነጋዴዎች እስከ 20 ሺ ብር፣ በአነስተኛ ስራ የሚተዳደሩት ደግሞ እስከ 150 ብር እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ ነዋሪዎች ግን መክፈል ካለብን በፈቃዳችን እንከፍላለን እንጅ ልንገደድ አይገባም በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ...

Read More »

ጄ/ል ገብሬ አዲሱን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ነቀፉ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ራሳቸውን የምስራቅ አፍሪካ አገራት ሕብረት -ኢጋድ የሶማሊያ ተወካይ አድርገው የሚቆጥሩት የቀድሞው በኢትዮጵያ የሶማሊያ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገብሬ ዲላ ፣ አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በሶማሊያ ለተሰማሩት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር አባላት አክብሮት አላሳዩም በሚል ነቅፈዋቸዋል። ብ/ ጄኔራል ገብሬ በኦፊሻል የትዊተር ገጻቸው ላይ በጻፉት አጭር መልእክት ላይ እንዳሉት ”ፕሬዚዳንቱ ...

Read More »

የሰብአዊ ኮሚሽን ሪፖርትን ተከትሎ አመጽ ይነሳል በሚል በኦሮምያ የፌደራል ፖሊሶች ተሰማሩ

ሚያዝያ ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀደሞው ምርጫ ቦርድ ም/ል ሰብሳቢ በህወሃቱ አባል ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው ራሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ብሎ የሚጠራው ድርጀት ከፍተኛ አመጽ ተነስቶባቸው በነበሩ የኦሮምያ ከተሞች 495 ሲቪል ዜጎች መገደላቸውን ይፋ ካደረገ በሁዋላ፣ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቀሴ በድጋሜ ሊጀመር ይችላል በሚል በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ አካባቢው ልኳል። በደንብ የታጠቁ ወታደሮች የአመጹ ...

Read More »