ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጀመሪያው ዙር የታተመው 500 ሺህ ኮፒ በቂ ላይሆን ይችላል የሚል ሥጋት በማሳደሩና በበርካታ አፍሪካ ሀገሮች ካሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተጨማሪ ጥያቄ በመቅረቡ ሁለተኛ ዙር ሕትመት መቀጠሉን አስተባባሪዎቹ አስረድተዋል። አልበሙ ከወጣበት ማክሰኞ ከቀኑ 6 ፡00 ሰዓት ጀምሮ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ሕዝብ ወደ ሲዲ መደብሮች በመትመሙ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ለህዝብ ...
Read More »Amsterdam
በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃገራችን ካለችበት አደገኛ የሆነ የጥፋት አዘቅት ውስጥ እንድትወጣም ሆነ ፤የስርዓት ለውጥም መምጣት የሚቻለው እያንዳንዱ ዜጋ በተደራጀ መልኩ ሲታገል ፤ድርጅቶችም ሳይጠላለፉ በመመካከር ስራዎችን በጋራ መስራት ሲችሉ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል። የትብብር መድረኩ በጀርመን አካባቢ የሚጠሩ ማናቸውም ሰላማዊ ሰልፎችና የተቃዋሚ እንቅስቃሴዎች በታቻለ መጠን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በጋራ እንዲዘጋጁ፣ በአካባቢው የሚካሄዱ ...
Read More »በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች ታሰሩ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደረሰበትን ህዝባዊ ማዕቀብ መቋቋም የተነሳነው በህወሃት/ብአዴን የሚተዳደረው ዳሸን ቢራ ስሙን ባላገሩ ቢራ በሚል ቀይሮ ባህርዳር ላይ ያዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት፣ ፍንዳታ መካሄዱን ተከትሎ ፖሊሶች በድንጋጤ በመተኮሳቸው የ2 ሰዎች ካለፈ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ብስጭትና ሽንፈት የደረሰበት ገዢው ፓርቲ፣ “ይህን ያክል ጥበቃ ተመድቦ ፣ ይህን ያክል ወታደር ጥበቃ እያደረገ እንዴት ቦንብ ሊገባ ...
Read More »ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮች ወደ አገር ገቡ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ 24 ቀን 2009 ዓም ጠዋት በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሾፌሮች ገልጸዋል። በጅቡቲ ወደብ 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮች የተራገፉ መሆኑን የሚገልጹት የአይን እማኞች፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑትን ታንኮች የጫኑ ሎቤድ መኪኖች ወደ ደብረዘይት ተንቀሳቅሰዋል። ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መራባቸው በተነገረ በሳምንት በእርዳታ ...
Read More »የእንግሊዝ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ለደህንነት ሲባል መጎብኘት የሌለባቸውን ቦታዎች ይፋ አደረገ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእንግሊዝ መንግስት የውጭ ጉዳይ እና የጋራ ብልጽግና ጽ/ቤት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርጓቸውን ማንኛውንም ጉዞዎች ለደህነታቸው አስጊ እና አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል ያላቸውን አካባቢዎች ለይቶ አሳውቋል። የቱሪስት መስህብ ከሆኑት ደብረዳሞ እና የሃ በስተቀር ከኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር አካባቢ በሚገኙት ከአክሱም እስከ አዲግራት ባሉ ዋና መንገዶች ዜጎቹ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል። በሱዳን ...
Read More »በከተሞች ዙሪያ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ተተኪ ቦታ ባለማግኘታቸው እየተንገላቱ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመርአዊ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች እንደገለጹት ፣ በተለያዩ ሰበቦች የእርሻ መሬታቸውን ከተነጠቁ በኋላ፣ ተተኪ የመኖሪያ ቦታ ባለማግኘታቸው ቤተሰቦቻቸው በቤት ኪራይ እየተሰቃዩ ነው። ወይዘሮ ፈንታነሽ አድማሴ በመርዓዊ ዙሪያ በሚገኝ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ከከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚኖሩበት አካባቢና የእርሻ ቦታቸው በመካለሉ አሮጌ ቤታቸውን አድሰው ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ለመኖር ተከልክለዋል፡፡የከተማ ...
Read More »የኢሳት 7ኛ አመት በሙኒክ ጀርመን በተሳካ ሁኔታ ተከበረ
ሚያዝያ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢሳት አለማቀፍ የድጋፍ ኮሚቴ የበላይ መሪነት እና በሙኒክ የኢሳት ቤተሰቦች የተዘጋጀው የኢሳት 7ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አዘጋጆች ገልጸዋል። በእለቱ የክብር እንግዳ ሆነው የቀረቡት ከአሜሪካ የቢቢኤን ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድና የኢሳት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ነበሩ። ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ፣ ባለፉት 25 አመታት የህወሃትን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ...
Read More »ዳሸን ቢራ “ባላገሩ ቢራ” በሚል የስያሜ ለውጥ በባህርዳር ከተማ ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ በፈነዳው ቦምብ 2 ሰዎች መሞታቸውና 31 ሰዎች መቁሰላቸው ተነገረ።
ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በባህር ዳር የጅምላ አፈሳ ሲካሄድ ውሏል። ኮንሰርቱ እየተካሄደ ያለበት ሥፍራ በሁለት ተከታታይ የቦምብ ፍንዳታዎች መናወጡን ተከትሎ ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፣ በርካታ ታዳሚዎች በፖሊስ ተከበው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ኮንሰርቱ ላይ ሙዚቃ ስትጫዎት ፍንዳታ በመሰማቱ ክፉኛ የደነገጠችውን ድምጻሚ ኩኩ ሰብስቤን ጨምሮ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ...
Read More »ከፍተኛ ወጪ የወጣበትና ትናንት ሚያዚያ 22 ቀን 2009 ዓ ም በጎንደር የተከፈተው 7ኛው የከተሞች ፎረም እንደተጠበቀው ሊደምቅ አለመቻሉ ተገለጸ።
ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት በዓሉን በልዩ ድምቀት ለማክበር በማሰብ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ ግብረ ሀይል አቋቁሞ በርካታ የሰው ሀይል በመመደብና እና ከፍተኛ ገንዘብበማፍሠስ በዓሉ ርብርብ ቢያደርግም፣ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የታሰበውን ያህል ውጤት ማግኘት ሳይቻል መቅረቱ ተመልክቷል። በጎንደር መከበር በጀመረው በዚህ በዓል ተይዞ የነበረው ዕቅድ ህብረተሰቡ በነቂስ ወደ አደባባይ ...
Read More »በዓለም ላይ ለ128ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ42ኛ ጊዜ የሚዘከረውን የላባደሮች ቀን -ሜይ ዴይን ምክንያት በማድረግ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
ሚያዝያ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለይ በመካከለኛው ምሥራቅ በሊባኖስ፣ እንዲሁም በስዊድንና በኖርዌይ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ባደረጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች በአኢትዮጵያ ውስጥ በነገሠው አምባገነን አገዛዝ የሠራተኛውም ሆነ የሁሉም ዜጋ መብት መረገጡን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ሰላማዊ ዜጎችና ንጹሀን ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ሳቢያ በእስር እየማቀቁ በሚገኙባት ኢትዮጵያ የዓለም ላባደሮች ከመቶ ዓመት በፊት የተቀዳጇቸው መብቶች ሊከበሩ እንዳልቻሉ የጠቀሱት ...
Read More »