Amsterdam

ኢህአዴግ በደንብ አስከባሪ ስም ያሰለጠናቸውን ከ1700 በላይ ሰዎች ሊያስመርቅ ነው

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የተለያዩ መረጃ የመሰብሰብ ስራዎችን እንዲሰሩለት ለወራት በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ከ1700 በላይ ሰልጣኞች ሰሞኑን ያስመርቃል። ሰልጣኞቹ ከሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች የተውጣጡ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር ከገቡት 2 ሺ ሰልጣኞች መካከል 300 የሚሆኑት የተቃዋሚዎች አስተሳሰብ አለባችሁ በሚል ተገምግመው እንዲባረሩ ተደርጓል። በስልጠናው ወቅት የአገሪቱን ችግር እያነሱ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ የነበሩ ሰዎች፣ ...

Read More »

በሜቴክ የሚሰራው የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ከመንግስት ከ4. 4 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ ጠየቀ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ5 ዓመታት በፊት ተጀምሮ በ2008 ዓም ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረውና በአሁኑ ሰዓት ከ35 በመቶ ያልበለጠ ግንባታ ያካሄደው እንዲሁም ከተፈጥሮ ውድመት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቅርብበት የቆየው ያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በመጀመሪያ የተያዘለት የ9 ቢሊዮን 600 ሺ ብር በጀት እንደማይበቃው ግንባታውን በሚያካሂደው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ በኩል ጥያቄ አቅርቧል። ኩባንያው ተጨማሪ 4 ቢሊዮን ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው ግንቦት 7 ከሌሊቱ 8 ሰአት ከ55 ደቂቃ ላይ ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን በሊቦከምከም ወረዳ በጣራ ገዳም አካባቢ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ጦሩ በተጠቀሰው ቦታ ላይ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጽም እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል። የንቅናቄው ታጋዮች ወደ ...

Read More »

ዮናታን ተስፋዬ በፌስቡክ ላይ በመጻፉ በአሸባሪነት መከሰሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮናታን ተስፋዬ መንግስትን በመተቸቱ ብቻ በሽብር ክስ መከሰሱን አውግዟል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከቅም በላይ ሃይል መጠቀማቸውን በማህበራዊ ድረገጾች ማውገዙ ሊያስከስሰው አይገባም ብሏል። ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በአንድ ወቅት ...

Read More »

አልሸባብ ሂራን በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ላይ ጥቃት አደረሰ

ግንቦት ፱ ( ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር አሜሶም ስር በሶማሊያ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ላይ አሸባሪው አልሸባብ ጥቃት ፈጸመ። ረቡእ እለት በሂራን ግዛት በሃላጋን ከተማ በሁለቱም መሃከል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። እስካሁን በግጭቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም። አልሸባብ በራሱ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወታደራዊ ቤዝ ...

Read More »

መከላከያን ጥለው የሚጠፉ ወታደሮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል

ግንቦት ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ በአማራና በኦሮምያ አካባቢዎች የተነሱትን ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተከትሎ፣ ስርዓቱን በተለያየ መንገድ አናገለግልም በማለት እየጠፉ የሚሄዱ ወታደሮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ አዳዲስ ወታደሮችን በፍጥነት ለመመልመልና በተለያዩ መንገድ ከመከላከያ የተሰናበቱትን ተመልሰው እንዲገቡ ጥሪ ለማድረግ ተገዷል። ባለፉት 4 ወራት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች መጥፋታቸው ለመከላከያ ከፍተኛ ...

Read More »

በሃረሪ ክልል የሚገኙ የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎች መብታችን ካልተከበረልን ወደ ኦሮምያ እንጠቃለል አሉ

ግንቦት ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረሪ ክልል በገጠር አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ አገር ሽማግሌዎች ለኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት በጻፉት የአቤቱታ ድብዳቤ በሃረሪ ክልል ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም፣ ከፖለቲካና ከኢኮኖሚ ጉዳዮች ውጭ በመሆናችን አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ወደ ኦሮምያ ክልል እንድንጠቃለል እንጠይቃለን ብለዋል። ከ99 በመቶ በላይ የሚሆኑ በክልሉ የሚገኙ የንግድ ቤቶች እና ቦታዎች የተያዙት ...

Read More »

ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በፌስቡክ ጽሁፎቹ በሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ

ግንቦት ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዞ ከዓመት በላይ በእስር ሲሰቃይ የቆየው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ በቀረበበት የሽብር ክስ ጥፋተኛ ተብሎአል። በፌስ ቡክ እና ትዊተር ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች ምክንያት ለእስር የተዳረገው ዮናታን ተስፋዬ የፀረ ሽብር አዋጁን 652/2001 አንቀፅ 6ን ተላልፈሃል በሚል የጥፋተኝነት ፍርድ ...

Read More »

በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የፖሊስ አመራሮች ከሃላፊነት ተነሱ

ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ የደረሰውን ተደጋጋሚ የቦንብ ጥቃት መንስኤና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለመያዝ ባለመቻላቸው የተገመገሙት የባህርዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ውበቱ አለን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ፖሊሶች ከደረጃ ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል። በተባረሩ አዛዦች ቦታ የሚተኩት አዲሶቹ አዛዦች፣ ነባሩ አመራር ሊደርስበት ያልቻለውን ህዋስ አጥንተው እንዲደርሱበት ልዩ ትእዛዝ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ...

Read More »

ከ40 በላይ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር አቅጣጫ ማምራታቸው ታወቀ

ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚደረገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ ሲሆን፣ ዛሬም ከ40 በላይ ወታደሮችን የጫኑ ኦራል ተሽከርካሪዎች በወልድያ አድርገው ወደ ጎንደር አቅጣጫ አምርተዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሽከርከሪዎች ወታደሮችን ወደ ሰሜን ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል። በቅርቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮች ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ የገቡ ...

Read More »