Amsterdam

የኢንተርኔት አገልግሎት መታፈኑን ተከትሎ በርካታ መስሪያ ቤቶች ችግር አጋጥሟቸዋል

ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገራቀፍ ፈተናዎችን ምክንያት በማድረግ ባለፈው ማክሰኞ የተጀመረው የኢንተርኔት አፈና ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ባንኮች፣ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን ለማከናወን ተቸግረዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ ደርጅቶች እንዲሁም ኢንትርኔት በስልካቸው የሚጠቀሙ፣ ከውጭ አገራት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶች ሁሉ ስራቸው እንደተስተጓጎለባቸው ወኪላችን ገልጿል። በተለያዩ የመንግስት ና የግል ...

Read More »

በቆሸ ከደረሰው እልቂት ጋር በተያያዘ ድጋፍ ያላገኙ ቤተሰቦች መኖራቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ

ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሸ እየተባለ በሚጠራው የቆሻሻ መድፊያ ቦታ ላይ ቆሻሻ ተንዶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ካጠፋ በሁዋላ፣ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የገንዘብ እርዳታ ለግሰዋል። የገንዘብ ድጋፉ ገዢው መንግስት በበላይነት በሚቆጣጠረው የባንክ አካውንት እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ገንዘቡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ...

Read More »

ከ40 በላይ ሰዎች በሰሃራ በረሃ መሞታቸው ታወቀ

ግንቦት ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ለቢቢሲ እንደገለጸው ከሆነ ሀምሳ የሚጠጉ ሰዎችን ይዞ በሳህራ በርሀ በመጓጓዝ ላይ የነበረ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ አደጋ የደረሰበት በመሆኑ አርባ አራት ሰዎች በውሃ ጥም ህይወታቸው አልፏል። የተረፉት ስድስት ሰዎች ረጅም የእግር መንገድ በመጓዝ በኒጀር ዲንኮ የቀይ መስቀሉ መስሪያ ቤት መድረሳቸውን የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ሲገልጹ ...

Read More »

ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት አስመልክቶ ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው

የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ባላወቀውና ባልወሰነበት ሁኔታ ለሱዳን መሬት ለመስጠት መንቀሳቀሱ በእጅጉ እንዳበሳጫቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። “እንዲህ አይነት መንግስት አይቼ አላውቅም፣ መንግስት ሊባል አይችልም፣ በአገር ላይ የሚሰሩት ስራ ሁሉ እጅግ የሚያሳዝን ነው፣ የኢትዮጵያ ወገን አይደሉም” በማለት አስተያየት የሰጡት አንድ የሰሜን ጎንደር ነዋሪ፤ ስርዓቱን ተባብረን እስካልገታነው ድረስ መዋረዳችን ይቀጥላል ብለዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ “ በኢትዮጵያ ‘አፈሮቿ ባህር ተሻግረው እንዳይሄዱ የወራሪዎቿን እግር ...

Read More »

ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢህአዴግ ውስጥ መናበብ ጠፍቷል ተባለ

ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አባላት ለኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንደገለጹት፣ ኢህአዴግን በመሰረቱት አራት ድርጅቶች መካከል ያለው መናበብ፣ ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ በመዳከሙ፣ አቅጣጫ ሰጥቶ የሚመራ አካል እየጠፋ ነው። በኢህአዴግ ታሪክ የአባላቱ መንፈስ በዚህ ደረጃ የወደቀበትን ጊዜ አናስታውስም የሚሉት አባሎቹ፣ ማእከላዊነት የሚባል ነገር በመጥፋቱ ሁሉም በራሱ የመሰለውን ውሳኔ እየሰጠ ነው ይላሉ። “አለመግባባቱ፣ ...

Read More »

አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናን ምክንያት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ተቋረጠ

ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ ለሚጀመረው ፈተና ከማክሰኞ ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቁዋረጡ በማህበራዊ ድረገጾች ተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሯል። ቁጥራቸው 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተጨማሪም 288 ሽህ የ12ኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መሰናዶ ብሄራዊ ፈተናውን በቀጣይ ሳምንት እንደሚወስዱ ሪፖርቶች አመላክተዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት ለ12 ሰዓታት ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከትናንት ...

Read More »

ሱዳን የግብጽ የግብርና እና የእንሣት ተዋጽኦ ምርቶች ወደ አገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች

ግንቦት ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱዳን መንግስት የካቢኔ አባላት የግብጽ የግብርና እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ወደ አገራቸው እንዳይገባ ማገዳቸውን የሱዳን መንግስት ልሳን የሆነው ሱና የዜና አውታር ማክሰኞ እለት ዘገቧል። ካቢኔው አክሎም በቀጥታ ከጎረቤት ግብጽ በኩል ወደ ሱዳን የሚገቡ ማንኛውንም ምርቶች እንዳያስገቡ ለግል ባለሃብቶችም ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በሱዳን እና በግብጽ መሃከል የተነሳው ውጥረት ከጊዜ ወደ ...

Read More »

ሰመጉ “በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ” ዜጎች በእስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን ስቃይ ይፋ አደረገ

ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰብአዊ መብት ጉባኤ በ142ኛ ልዩ መግለጫው ላይ እንደጠቀሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ከመስከረም 29 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ከ22 ሺ በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የሆኑ የቅጣት እርምጃዎች በእስረኞች ላይ እንደሚፈጸሙ ገልጿል። ሰመጉ ወታደራዊ ካምፖች ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች እስርቤት ሆነው ማገልገላቸውን ገልጾ፣ በተለይ በወታደራዊ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በአንድ የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መግለጫ በደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ልዩ ስሙ ጎርጎራ ክፍል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ግንቦት21 ቀን 2009 ዓም ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በአንድ የህወሃት የደህንነት አባል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል። በደንቢያ ወረዳ የህወሃት ሰላይ በመሆን በአካባቢው ህዝብ ላይ ለሚደርሰው ግድያ ፣ አፈናና እስር ዋና ተጠያቂ ነው ባለው ...

Read More »

የሱዳን ገበሬዎች ከኢትዮጵያ ተቆርሶ የሚሰጣቸው መሬት አነስተኛ ነው በማለት አማረሩ

ግንቦት ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት ከ12 ዓመታት በፊት የተጀመረው ድርድር ተግባራዊነት እውን ሊሆን ጫፍ መድረሱን ተከትሎ የሱዳን የመገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡት ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ገበሬዎቹ የሚሰጠን መሬት ትንሽ ነው በማለት እያማረሩ መሆኑን የሱዳን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። በገዳሪፍ አካባቢ የሚኖሩ የሱዳን ገበሬዎች በቅርቡ የግዛቱ አስተዳዳሪ የሆኑት ...

Read More »