ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ የሰሜን ዕዝ ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 4:00 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ ቆላድባ አካባቢ ልዩቦታው ወንፈላ በተባለው የሚገኝ የገዥው ፓርቲ ንብረት ላይ ጥቃት ፈፀሟል። ንብረትነቱ የዳሽን ቢራ በሆነ መጋዝን ላይ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት የኦክስጅን ጋዝ መጋዝን ከነ ሙሉ ዕቃው ሲቃጠል፣ የጂኒሪተር ክፍሉበከፊል ቃጠሎ ደርሶበታል። ...
Read More »Amsterdam
የኮሚሽነርነት ማዕረግ የመጣለት የምርመራ ኃላፊ አልፈልግም ብሎ ሥራውን ለቀቀ
ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ሥራቸውን በፈቃዳቸው በሚለቁ ፖሊሶችና ሹመኞች ውዝግብ እየታመሰ ነው። በተለይ ሰሞኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የአቶ ዓለምነው መኮነን አጃቢ በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል መገደላቸውን ተከትሎ እስከ ኮማንደር ድረስ ማዕረግ ያላቸው ፖሊሶችና አዛዦች በፈቃዳቸው ከሥራቸው እየለቀቁ ነው። የምዕራብ ጎጃም ዞን የምርመራ ሀኃፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ፓሊስ ...
Read More »በአዳማ ከተማ ሙሉ ለሙሉ መብራት በመቋረጡ ነዋሪዎቹ ተቸግረናል እያሉ ነው
ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋብሪካዎች ተዘግተዋል በአዳማ ከተማ ከሃሙስ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የመብራት አገልግሎት መቁረጡን ተከትሎ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ በጨለማ መዋጧን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። ከመብራት መቋረጥ ጋር በተያያዘ ፋብሪካዎች፣ የሕክምና መስጫ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራቸውን ለማቆም ተገደዋል። በተጨማሪም በተወሰኑ የከተማ ክፍል የስልክ ...
Read More »ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰባት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የፍርድ ብያኔ ተሰጠ
ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ኢትዮጵያ ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ እንቢተኝነት በኋላ በሰላማዊ መንገድ ገዥውን ሕወሃት ኢህአዴግን ይታገሉ የነበሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ ያነጣጠረ የጅምላ እስራት ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወሳል። ከማእከላዊና በተለያዩ የማሰቃያ እስር ቤቶች ውስጥ ለዓመታት ሰቆቃ ሲፈሰምባቸው ከነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል በሰባቱ ላይ የፍርድ ብያኔ ተሰጠ። የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ...
Read More »ህወኃት የነጻነት ታጋዮችን ለማደን ብዛት ያለው ወታደር አሰማራ። የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ሊረሸኑ የነበሩ ወንድማማቾችን ታደገ
ሰኔ ፲፭( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህዝባዊ ወያነ ኃርነት ትግራይ -ህወኃት በመተማና በጭልጋ አካባቢ ያሉ የነጻነት ታጋዮች ላይ ጥቃት ለመፈጸም በርካታ ወታደሮችን ወደስፍራዎቹ ማንቀሳቀሱ ተገለጸ። ታጋዮቹ ያሉበትን ሥፍራ ማወቅ የተሳናቸው የህወኃት ታጣቂዎች በትናንትናው ዕለት ወደታጋዮቹ ዘመዶች ቤት በመሄድ አሠሳ ከማድረጋቸውም በላይ ታጋዮቹ ያሉበትን ቦታ ተናገሩ በማለት ዘመዶቻቸውን ሲያስጨንቁ አምሽተዋል። ዘመዶቻቸው የታጋዮቹን አድራሻ እንደማያውቁ ቢገልጹም “ያሉበት ...
Read More »ለስደተኞች የተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲራዘም በኢትዮጵያ የቀረበው ጥያቄ በሳኡዲ በኩል ምላሽ አልተሰጠውም።
ሰኔ ፲፭( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሳኡዲ ያሉ ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀው የሚወጡበት ቀነ ገደብ እንዲራዘም ጥያቄ ማቅረቡን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ። ይሁንና ቀነ ገደቡ ሊጠናቀቅ የቀረው ጊዜ በጣም አጭር በመሆኑና በዚህ አጭር ጊዜ ሁሉንም ስደተኞች መመለስ እንደማይቻል በመረዳት ጊዜው እንዲራዘም ጥያቄ ማቅረቡን ቢገልጽም እስካሁን ከሳኡዲ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም። በሳኡዲ በኩል ለሦስት ወራት የተሰጠው የስደተኞች መውጫ ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ተባብሶ መቀጠሉን ዩኒሴፍ አስታወቀ::
ሰኔ ፲፭( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀው የምስራቅ አፍሪካ አገራት ድርቅን ተከትሎ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና እየተመናመነ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት-ዩኒሴፍ አስታውቋል። በተለይ በምስራቅ ኢትዮጵያ የተባባሰው ድርቅ የቤት እንስሳትን ክፉኛ እየጨረሰ ሲሆን፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉና በየመጠለያ ጣቢያዎችእንዲጠለሉ አድርጓቸዋል። ድርቁ በፈጠረው ርሃብ ምክንያት በተለይ በደረቃማ የአየር ንብረት የሚኖሩት የኦጋዴን ነዋሪዎች ...
Read More »ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ ካንዣበበባቸው አገራት ተርታ ተመደበች
ሰኔ ፲፭( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየዓመቱ በዓለማችን ውስጥ የሚገኙ በመፍረስ እና ለመፍረስ አደጋ ያንዣበባቸው አገራትን በሚያጠናው ፍራጃይል ስቴት ኢንዴክስ(Fragile States Index) ተቋም ጥናት መሰረትኢትዮጵያ አደጋ ካንዣበበባቸው አገራት ተርታ ተመደበች። የሟሸሹ አገራት ተርታን አዲሲቷ አገር ደቡብ ሱዳን በቀዳሚነት ስትመራ ፊንላንድ አሁንም የሰላም ዋስትና ያላት የመጀመሪያዋ አገር ሆና ተመርጣለች።ሌላዋ የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ኢትዮጵያ፣ ሜክሲኮ እና ቱርክ ...
Read More »የአቶ አለምነው መኮንን የግል አጃቢ መገደል በካድሬዎች ላይ ሽብር ፈጥሯል
ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ስራውን በፈቃዱ ለቋል በአማራ ክልል ህዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠሉትና የህወሃት ቀኝ እጅ ተድርገው የሚቆጠሩት የአቶ ዓለምነው መኮንን የግል አጃቢ የሆነው አንዋር ሙሃመድ የተባለው ግለሰብ፣ ባህርዳርቀበሌ 04 በሚገኘው ግሪንላንድ ሆቴል ውስጥ በጥይት ተመትቶ ተገድሎ ከተገኘ በሁዋላ፣ የብአዴን ካድሬዎችና የአቶ ዓለምነው የቅርብ ወዳጆች ሽብር ውስጥ መግባታቸውን ...
Read More »በኦህዴድ ውስጥ የእርስ በርስ መጠላለፍና መወነጃጀል ተፈጥሯል
በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የህወሓት ታማኞች ጓዶቻቸውን እያሳደዱና እያሰሩ ነው። ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ ውሰጥ ያሉ ታማኝ የህወሓት አገልጋዮቸ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የራስ መተማመንንበማዳበር ላይ ያሉትን የኦህዴድ አመራር አባላትን ማደን ጀምረዋል። የህወኃት ተላላኪዎቹ-ጓደኞቻቸውን ኦህዴድ ውስጥ ሆነው ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። ባለፉት 2 ቀናት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ 3 የዞን አመራሮች የታሰሩ ሲሆን፤ አምስት ...
Read More »