ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው ክብር ለናቶች የልማት ተራድኦ ድርጅት በሀዋሳ መስቀል አደባባይ ፕሮግራም አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም፣ እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል የተባሉ እናቶች ሳይገኙ ፣ በእናቶች ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ተበልቷል። በፕሮግራሙ ላይ 50 በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ዋጋ የከፈሉ እና ዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኙ እናቶችን ለመሸለም እና እውቅና ለመስጠት ፕሮግራም ተይዞ ...
Read More »Amsterdam
45 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያ ውስጥ ተያዙ
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህገወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ የገቡ 45 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በበቆሎ ማሳ ውስጥ ተደብቀው መያዛቸውን የታንዛኒያ ባለስልጣናት አስታወቁ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ካለምንም ሕጋዊ ሰነድ ወደ ታንዛኒያ ሲገቡ መያዛቸውን የታንጋ ክፍለሃገር የስደተኞች ጉዳይ ዋና ሃላፊ የሆኑት ክሪስፒን ኒጎያኒ ገልጸዋል። ባለስልጣኑኑ እንዳሉት ስደተኞቹ በሰሜናዊ ምስራቅ ታንዛኒያ በሚኪንጋ አውራጃ በኬኒያ እና ታንዛኒያ ድንበር አቅራቢያ ...
Read More »በአዲስ አበባ ነጋዴዎች በግምት የሚጣልባቸውን ግብር ተቃወሙ
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳ 11 የሚገኙ ነጋዴዎች ፣ በዘፈቀደ የሚተመነውን የቀን ገቢ ግምት ተንተርሶ የተጣለባቸውን የግብር ከፍያ በመቃወም አቤቱታ ሲያሰሙ፣ በፌደራል ፖሊሶች እንዲበተኑ ተደርጓል። ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ ፈቃዳቸውን እንደሚመልስ ሲያስጠነቅቁ ውለዋል። ህዝቡ ወደ ቀበሌ በመሄድ ፈቃዳችንን ተቀበሉን እያለ ቢሆንም፣ ፈቃድም ለመመለስ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስከፍል ነጋዴዎች ይናገራሉ ። በመርካቶ አካባቢም በርካታ ...
Read More »የደቡብ አሪ ወረዳ መምህራን የተቃውሞ ፊርማ አሰባስበው አስገቡ
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ መምህራን በመጋቢት ወር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ እንዳይቆረጥባቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ደሞዛቸው ሳይቆረጥባቸው የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን የአመቱን የስራ ማጠናቀቂያ ተከትሎ መምህራን ስለሚበታተኑ ተቃውሞ አያነሱም በሚል ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ 30 በመቶ እንደሚቆረጥባቸው ወረዳው መናገሩን ተከትሎ መምህራን ...
Read More »የቂሊንጦ እስረኞች የግዳጅ የጉልበት ስራ እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቂሊንጦ እስር ቤት የግዳጅ የጉልበት ስራ እያሰራቸው መሆኑን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት እነ ጌታሁን በየነ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ እስረኞቹ ፣ 200 ኪሎ ግራም ቆሻሻና የ125 እስረኞች የሚቀርብን ወጥ ሁለት ሰዎች ብቻ እንዲሸከሙ እንደሚገደዱና ይህም ...
Read More »የማላዊ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ካለምንም ሕጋዊ ቪዛ ወደ አገሬ ገብተዋል ባላቸው 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የገንዘብ ቅጣት ፈረደ
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለምንም ሕጋዊ ቪዛ በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብታችኋል በተባሉ 27 ስደተኞች ላይ እያንዳንዳቸው 20 ሽህ የማላዊ ክዋቻ እንዲከፍሉ ሲል የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በየነ። ከተፈረደባቸው ስደተኞች ውስጥ ከአንዱ በስተቀር የተቀሩት ሃያስድስቱም በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ናቸው። ስደተኞች ማክሰኞ እለት በሕገወጥ መንገድ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው ሲጓዋዙ ይጠቀሙበት ከነበረው ተሽከርካሪ ...
Read More »በሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ በጸና ታመዋል
ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሙስና ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ፋንታ በጸና መታመማቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ጥቅምት ወር፣ 2006 ዓም በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ፣ በተከሰሱበት ወንጀል እንዲከላከሉ ባለፈው የካቲት ወር ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱ ይታወቃል። አቶ መላኩ ምንም አይነት ...
Read More »ህወሃት በዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚብሄር በኩል በአማራ ክልል ፖሊስ አዛዦች ላይ ምርመራ ጀመረ
ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርቡ በክልሉ ከታየው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በሁዋላ የታየው የፖሊሶች አቋም፣ ለህወሃት ህልውና አደገኛ ነው በሚል እምነት፣ ራሱ በሚመራው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት እየገመገመ ስራቸውን እንዲለቁ፣ ወንጀል ስርተዋል እያለ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ካደረገ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ዋና ዋና በሚባሉት የፖሊስ አዛዦች ላይ በህወሃቱ ...
Read More »በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች በተናጠል እየተሰቃዩ ነው። በእነ ወ/ት ንግስት ይርጋ ላይም የሃሰት ምስክር ሊቀርብ ነው
ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን ምንጮች አስታወቁ። እስረኞች የደንብ ልብስ እንዲለብሱ የሚገደዱት ወደ ቤተሰብ ሲወጡና ተነስተው ሲዘዋወሩ ብቻ ቢሆንም፣አሁን ግን የተኙ እስረኞች ሳይቀር የደንብ ልብስ አለበሳችሁም እየተባሉ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ እና የአመክሮ እስራት ጊዜ እንዲቀሙ ተደርገዋል። ማንገላታቱ እና አካላዊ ጥቃቶች ከሚፈጸምባቸው መካከል የፖለቲካ ...
Read More »በጋሞ ጎፋ ዞን ባለው ድርቅ ሰዎችና እንስሳት ህይወታቸው እያለፈ ነው
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ አርሶአደሮች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት ያለቁ ሲሆን፣ ሰዎችም መሞት ጀምረዋል። ድንችና የመሳሰሉት ሰብሎች በዝናብ እጥረት መጥፋታቸውን የሚገለጹት ነዋሪዎች፣ በሴፍትኔት እንዲታቀፉ ለተደረጉ ካድሬዎች እህል ቢከፋፈልም አብዛኛው ህዝብ እርዳታ ባለማግኘቱ ከፍተኛ አደጋ ተደቅኖበታል። በድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁት መካከል ኮንሶ፣ ደራሸ፣ ...
Read More »