ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው ዛሬ ረቡዕ በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል ላይ ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና አቶ አባይ ጸሃየ የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አጠቃላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመዘጋታቸው ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ሲንገላታ ውሎአል። መረጃዎቸ እንደሚያሳዩት አጠቃላይ የዝግጅቱን ሃላፊነት የወሰዱት ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ናቸው። አጠቃላይ ዝግጅቱ ለአንድ ...
Read More »Amsterdam
የእንግሊዝ ፖሊስ በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ ክስ መሰረተ
ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ታደሰ ክስ የተሰመረተባቸው በጥር ወር ኤርትራ ቆይተው ወደ እንግሊዝ ሲገቡ፣ አየር ማረፊያ ላይ በተደረገው ፍተሻ አንዳንድ ጽሁፎችን ከዌብ ሳይት ላይ ወስደው ኮምፒተሮቻቸው ላይ አውርደውና ቦርሳቸው ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው ነው። ጽሁፎቹ በእንግሊዝ ፖሊሶች በጥርጣሬ መታየታቸውን ተከትሎ፣ ክስ እንደተመሰረተባቸው ታውቋል። ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲሞክራሲና የፍትህ ትግል ውስጥ በአርበኞች ...
Read More »“ብአዴንንና ህወሃትን፣ ህወሃትንና ኦህዴድን ለማጋጨት ፀረ-ሰላም ሃይሎች የጠነሰሱትን ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ አግዘናቸዋል” ሲሉ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ተናገሩ
ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ ብአዴን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካና ርእዮተአለም ብልሽት አጋጥሞታል። በ40 እና 50 አመታት ጊዜ ውስጥ የበለጸገ አገር የሚፈጥር መስመር ሆኖ እያለ፣ ይህንን መስመር በብቃት ባለማወቃችን ምክንያት ይህን መስመር እየተከላከልነው አይደለም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ በእኛ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ብልሽት ምክንያት ከመስመራችን በተጻጻሪ ለቆሙ ሃይሎች አቅም ሆነን እንታያለን ሲሉ በተሃድሶ ስብሰባ ላይ ምሬታቸውን ...
Read More »ዲፕሎማቶች የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይሳካል ብለው እንደማያምኑ ፋይናንሻል ታይምስ ዘገበ
ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው የቢዝነስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ ይዞት በወጣው ጽሁፍ እንዳተተው ምንም እንኳ ቻይና መራሹ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የስራ እድል በመፍጠር በአገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የስራ አጥ ቁጥር ትክክለኛ አካሄድ መስሎ ቢታይም፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ዲፕሎማቶች አጠቃላይ የኢኮኖሚ እቅዱ ይሳካል የሚል እምነት የላቸውም። ዲፕሎማቶቹ ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች መካከል የፋይናንስ አገልግሎቱ ፣ ...
Read More »በባህርዳር አየር ማረፊያ ላይ የተያዘውን ተቀጣጣይ ፈንጅ ተከትሎ በጥርጣሬ ሰዎች እየተያዙ ነው
ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተያዙት ሰዎች መካከል አንደኛው ግለሰብ፣ እቃውን እንዳደርስ አንድ ሰው ላከኝ እንጅ ፈንጅ ይሁን አይሁን አላውቅም ብሎ የተናገረ ሲሆን፣ ከጎንደር መላኩንም ገልጿል። ፈንጁን ሰጥቶታል የተባለውን ሰው ለመያዝ፣ ከግለሰቡ ጋር መርመሪዎች ወደ ጎንደር ሊወስዱት ማሰባቸውን የኢሳት የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። አንድ የአየር መንገድ ሰራተኛም በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች ገልጸዋል።
Read More »በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ሲሰቃዩ የነበሩ 120 ሶማሊያዊያን እስረኞች ተለቀቁ
ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ዓሊ ከይሬ ለ29ኛው አፍሪካ ሕብረት ስብሰባ በመጡበት በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ 120 ሶማሊያዊያን እስረኞችን ሰኞ እለት አስለቁ። ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ”ሁለታችንም መንግስታት በደረስንበት የጋራ ስምምነት አማካኝነት 120 ሶማሊያዊያን ዜጎቻችንን ከእስር ተፈተዋል።” በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ አሁንም ድረስ ስላሉት ሶማሊያዊያን ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ እዳ ከ575 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ
በውጭ ምንዛሪ ቀውስ የሚታወሰው የህዉሃት/ኤህአዴግ አገዛዝ በ2009 አ.ም አመታዊ የውጭ ወለድ ክፍያው ከ3 ቢሊዮን ብር ወደ 10 ቢሊዮን ብር እንዲሁም አመታዊ የመንግስት የውጭ እዳ ክፍያ ከ14 ቢሊዮን ብር ወደ 25 ቢሊዮን ብር አድጓል። በዚህ ምክንያት ችግሩ የህዉሃት መራሹ መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ እየከተተው እንደሆነ ተገልጿል። ከፊሉን የውጭ እዳ ለማቃለል ከወጭ ንግድ ከሚገኘው የውጭ ምንዛሪ እሸፍናለሁ በማለት ቢገልጽም በየአመቱ ከውጭ ንግድ የሚገኘው ...
Read More »ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተጣለው ግብር በመላ አገሪቱ ችግር እየፈጠረ ነው።
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እዳ አለባቸው የሚባሉ ነጋዴዎች በባንክ ያስመቀጡትን ገንዘባቸውን እንዳያወጡ እገዳ እየተጣለባቸው መሆኑን ነጋዴዎች ገልጸዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለው ገዢው ፓርቲ፣ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጣነ ግብር እንዲከፍሉ በማድረጉ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ነጋዴዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው። “ የሌለንን ገቢ እንዳለን አድርጎ የሚጣለው ግብር” በኑሮአችን ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው የሚሉት ...
Read More »በሰፈራ ወደ ተከዜ የተወሰዱ የአማራ ክልል ነዋሪዎች በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከበየዳና ደባርቅ አካባቢ ተነስተው ዘመነ ወርቅ በተባለው የተከዜ ሰው ሰራሽ ሃይቅ አካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረጉት ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት ምንም ዓይነት መሰረተ ልማት ሳያሟላ እንድንሰፍር በማድረጉ ከፍተኛ ችግር ላይ ጥሎናል ብለዋል። በ2008 ዓም. ከ1400 አባወራ በላይ ወደ አካባቢው እንዲሰፍር ቢደረገም በአጎራባች ክልሎች እንደሚካሄደው ሰፈራ የመሰረተ ልማት ተቋማት ሳይገነቡ በደፈናው ወደ ...
Read More »ቂሊንጦ እስር ቤትን አቃጥለዋል በሚል ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል የተወሰኑ እስረኞች ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርና በሌሎችም ወንጀሎች ተከሰው በእስር ቤት እያሉ እንደገና ቂሊንጦን አቃጥለዋል በሚል ክስ ከቀረበባቸው ወጣቶች መካከል፣ የተወሰኑት ዝዋይ እስር ቤት ተወስደው ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። እስረኞች ፍርድ ቤት ላይ ተቃውሞ በማሰማት፣ እንዲሁም የእስር ቤቱን አስተዳደር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ይታወቁ ነበር። በተለይ አዲስ ክስ በሀሰት ከተመሰረተባቸው በኋላና ክሱን ...
Read More »