Amsterdam

በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ማስከበር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች 95 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መዘጋታቸውን ጥናቶች አመለከቱ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብት እና የዴሞክርሲ ግንባታ ላይ ለመስራት ፍቃድ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ከመቶ በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በአሁኑ ወቅት አምስቱ ብቻ ስራቸውን እየሰሩ መሆኑን ቪዥን ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ጉባኤ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ጥናቶች አመለከቱ። ድርጅቶቹ እስከ ምርጫ 1997 ዓ.ም መባቻ ድረስ ስራቸውን በአግባቡ ያከናወኑ እንደነበርም ጥናቱ አመላክቷል። ...

Read More »

ኢህአዴግ የኦሮሞን ህዝብ ያስደስታል ብሎ ያወጣው ህግ ያልተጠበቀ ውጤት በማሳየቱ ህዝቡን በግድ የድጋፍ ሰልፍ ሊያስወጣ ነው

ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የኦሮሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚያስከበር አዋጅ መደንገጉ ለድርጅቱ ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ ያስገኝለታል በሚል በኢህአዴግ የፖሊሲ፣ ጥናትና ምርምር ተቋም የቀረበው ምክር እንዳልሰራ በመታመኑ ፣ ሰነዱ በኦሮምያ ክልል በየደረጃው ባሉ አካላት ውይይት ተካሂዶበት፣ የድጋፍ ሰልፍ እንዲደረግለት ልዩ ትዕዛዝ ተላልፏል። በአቶ በረከትና አባይ ጸሃዬ ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ

ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው ፖለቲከኛ የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊ/መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የተከሰሱበት ክስ ከአርበኞች ግንቦት 7፣ ከፕ/ሮ ብርሃኑ፣ ከአቶ ጃዋር፣ ከኢሳትና ከኦኤም ኤን ተነጥሎ እንዲታይላቸው ያቀረቡት መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ ዛሬ አርብ በዋለው ችሎት ውድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ምስክሮች የሚቀርቡት በሁሉም ተከሳሾች ላይ በመሆኑ ፣ ክሱ ተነጣጥሎ መቅረብ የለበትም፣ ምስክሮች መጉላላት አይገባቸውም በሚል ...

Read More »

የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የቤት ግንባታ ተቋራጮች ገንዘባችንን ተቀማን ይላሉ

ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተንዳሆ ቤቶች ልማት ግንባታ ምዕራፍ ሁለት ታሳተፊ ስራ ተቋራጮች ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓም ለተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ለአቶ አህመድ አብተው በጻፉት ደብዳቤ ከ200 በላይ የስራ ተቋራጮች ለግንባታ ያወጡት ገንዘብ እንዲመለስላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት ደብዳቤዎችን ቢጽፉም መልስ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል። “254 ስራ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚታየውን የትጥቅ ትግል ተንተርሶ እርሻ አለመታሩሱን ታጋዮች ተናገሩ

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርበኞች ግንቦት7 ስር ታቅፈው እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት ታጋዮቹ ፣ ህወሃት ለአንድ አርበኛ ታጋይ 400 ያክል ወታደሮችን አሰልፎ ታጋዮቹን ለመፈለግ በሚያደርገው ዘመቻ አርሶአደሩ እየተያዘ እስር ቤት በመወርወሩ እርሻ አልታረሰም። “ አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተካውም “ የሚሉት ታጋዩ፣ “ከማረሻ ውጭ ምን አለን? ማረሻ ከተሰቀለ፣ ቀንበር ከተሰቀለ፣ ጅራፍ ከተሰቀለ ከዚህ ...

Read More »

የኩራዝ አንድ የስኳር ፕሮጀክት ምርት ጀመረ ተብሎ መዘገቡን ሰራተኞች አስተባባሉ ።ማኔጂመንቱና ሜቴክ እየተወዛገቡ ነው።

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት በአማራጭነት ያቋቋመው የቴሌቪዥን ጣቢያ ፣ ኢኤንኤን /ENN/ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ “ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በአካባቢው ነዋሪዎች ‘ፋብሪካው ሥራ የሚጀምረው በምጽዓት/በፍርድ ቀን ነው፣ ወይም የፋብሪካውን ሥራ መጀመር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው (ሜቴክም አያውቀውም)’ ሲባል የነበረው የኦሞ-ኩራዝ 1 የስኳር ፋብሪካ ምርት ጀመሮ ፤ በቀን 650 ቶን ስኳር እንደሚያመርት ፣ ...

Read More »

በአዲስ አበባ በደረሰ የጎርፍ አደጋ አምስት ሰዎች ሞቱ። የአባትና ልጅ አስከሬን እስካሁን አልተገኘም።

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በተከታታይ የጣለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በአዲስ አበባ አምስት የከተማዋ ነዋሪዎች መሞታቸውን የአደጋ ሰራተኞች አስታወቁ። የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳሉት ”በመዲናዋ ደቡባዊ አዋሳኝ ላይ የሚገኝውን ወንዝ ለመሻገር በሚሞክሩበት ወቅት አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል።” በተጨማሪም በቦሌ ጃክሮስ ...

Read More »

በበቆጂ ከተማ የውሃ እጥረት ነዋሪዎችን አማረረ

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርሲ ዞን የምትገኘው የበቆጂ ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ሙሉ ለሙሉ በማጣታቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን አስታውቀዋል። በከተማዋ የነበረው ጥንታዊ የውሃ መስመር አገልግሎት መስጠት ካቆመ ረዥም ጊዜያት ሆኖታል። የከተማዋ መስተዳድርም ሆነ የውሃ ልማት ድርጅቱ የነዋሪዎችን የውሃ ችግር ለመፍታት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታይም። አንድ የአካቢው ነዋሪ ”እኛ የምንኖረው ኑሮ ኑሮ ...

Read More »

በአማራ ክልል ስራቸውን የሚለቁ አመራሮች ቁጥር እያሻቀበ ነው

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት የበላይነት በሚዘወረው ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ስራቸውን የሚለቁ የፖሊስ አዛዦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ፣ እስካሁን ባለው መረጃ ከ21 በላይ ኮማንደሮች ስራቸውን ለቀዋል። ትናንት በነበረው ግምገማ በባህርዳር የጣና ክ/ከተማ ሃላፊ ኮ/ር በላይ ደምሴ ፣ የህዳር 11 ክ/ከተማ ሃላፊ ኮማንደር አልምነው አደመ፣ የበላይ ዘለቀ ክፍለከተማ ...

Read More »

የደቡብ አሪ ወረዳ አስተዳደር መምህራኑን ለማስፈራራት እየሞከረ ነው

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወረዳው መምህራን እንደሚሉት ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ ያለፈቃዳቸው 30 በመቶ ተቆርጦ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ሊሰጥባቸው መሆኑን በመቃወም ፊርማቸውን አሰባስበው ካስገቡ በሁዋላ ፣ ሚስጢራችንን “ለጸረ ሰላም ሃይሎች አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል” በሚል ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው። መምህራኑ ማስፈራሪያውን ወደ ጎን በማለት አሁንም በአቋማቸው በመጽናት ጥያቄያችን ይመለስልን በማለት እየተጠየቁ ነው። በመጋቢት ወር መምህራኑ ...

Read More »