ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወኪላችን እንደዘገበው ባለፉት ሁለት ቀናት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በቆላ ድባና በገጠር አካባቢዎች በሰማራት በህዝቡ ላይ ድብደባ ከመፈጸም ጀምሮ አንዳንዶችን ይዘው በማሰር ላይ ናቸው። ባለፈው አመት የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ሳይቋረጥ ከቀጠለባቸው የሰሜን ጎንደር ከተሞች መካከል ቆላ ድባ አንዷ ስትሆን፣ በአካባቢው የሚካሄደውን የትጥቅ ትግል ተከትሎ አካባቢው አመቱን ሙሉ በውጥረት ...
Read More »Amsterdam
በሶማሌ ክልል በዶሎ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በርሃብ ምክንያት 68 ሕጻናት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው የርሃብ አደጋ ወደ አስጊ ደረጃ መሸጋገሩን እና በርሃብ ምክንያት ባለፈው ወር በሶማሌ ክልል በዶሎ ዞን 68 ታዳጊ ሕጻናት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ። በክልሉ ከድርቁ በተጨማሪ ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋዎች በመከሰታቸው የረድኤት ሥራውን ይበልጥ ውስብስብ አድርጎታል። በድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን በቀጠናው ላለፉት 12 ዓመታት በረድኤት አገልግሎት ሥራ ...
Read More »የአሜሪካና የሶማሊያ ወታደሮች በአልሸባብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገለጹ
ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሃሙስ ጠዋት የአሜሪካና የሶማሊያ ጦር ሃይል በደቡብ ሶማሊያን በአልሸባብ ተይዞ በነበረ ቦታ ላይ በሰነዘሩት ድንገተኛ ጥቃት ብዙ የአልሸባብ ወታደሮችን ገድለዋል። የሶማሊ ኮማንዶዎች ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር በመሆን በሁለት ሄሊኮፕተሮች ተጉዘው ኩንያ ባሮ የሚባለውን የአልሸባብ እስር ቤት የሚገኝበትን ቦታ በመውረር በፈጸሙት ድንገተኛ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ እስረኞች ተለቀዋል። ...
Read More »የአምቦ ነጋዴዎች ተቃውሞ ሲያካሂዱ ዋሉ
ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ የግብር መክፈያ ቦታዎችም በአቤቱታ አቅራቢዎች እየተጨናነቁ ነው የእለታዊ ገቢ ግብር አሰራርን በመቃወም በአምቦ ከተማ ዛሬ ተቃውሞ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ አንድ የፌደራል ፖሊስ መኪና ሲቃጠል ፣ አንድ አውቶቡስና ሌሎች የመስሪያ ቤት መኪኖችም ተሰባብረዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ 11 ሰአት ድረስ በከተማዋ ተኩስ ይሰማ ነበር። ወደ ...
Read More »የአቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተበየነ
ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ሃሙስ ሀምሌ 6/2009 ዓም በዋለው ችሎት በኦፌኮው ም/ል ሊ/መንበር በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀረበውን የሽብር ወንጀል ክስ በመቀየር ፣ በወንጀለኛ ህጉ አንቀፅ 257 ሀ ስር የተደነገገውን ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ በይኗል። በጉርሜሳ አያና መዝገብ ከተከሰሱት መካካል ከ ተራ ቁጥር አንድ ...
Read More »ወጣት ታዲዮስ በየነ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
ሐምሌ ፮ ( ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ታዲዮስ በምርጫ 97 ወቅት በቅንጅት ውስጥ ታቅፎ አዲስ አበባ ወጣቶችን በማደረጀትና በመምራት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በወቅቱ ካሰራቸው ወጣት የቅንጅ አመራሮች መካከል አንዱ ነበር። ወጣት ታዲዮስ በእስር ቤት ውስጥ ለ2 አመታት ያክል ታስሮ ከተፈታ በሁዋላ ወደ አውስትራሊያ ተሰዶ ፣ በነጻነት ትግሉ ውስጥ አስተዋጽኦ ሲያካሂድ ቆይቷል። በጓደኞቹ ...
Read More »በጎንደር ከተማ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ አንደኛ አመት በከተማዋ እየታሰበ ነው
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “የወልቃይት የአማራ ማንነት ይከበር” በሚል መነሻ የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቀሴ ወደ አጠቃላይ የመብት እና የእኩልነት ጥያቄዎች ተሸጋግሮ፣ በሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እንዲሁም በአዊ ዞን ከፍተኛ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አመጹ የተጀመረበትን ቀን ለመዘከር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው። ይህ ህዝባዊ አመጽ የስርዓቱን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉን ...
Read More »በኦነግ ስም በተከከሱ 22 ሰዎች ላይ ምስክሮች በዝግ እንዲሰሙለት አቃቢ ህግ ጥያቄ አቀረበ
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተካሄደውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ከኦነግ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል ተከሰው በታሰሩ 22 ተከሳሾች ላይ አቃቢ ህግ ምስክሮቹ በዝግ ችሎት እንዲታዩለት ጥያቄ አቅርቧል። ከተከሳሾች መካከል በአንደኛ ቁጥር ላይ የሚገኘው ደረጀ አለሙ ከእስር ቤት በማምለጡ ጉዳዩ በሌለበት በመታየት ላይ ነው። አቃቢ ህግ ሀምሌ 3 ቀን 2009 ዓም ለከፍተኛው ፍርድ ...
Read More »ታጋይ አበበ ካሴ ጨለማ ቤት መክረሙ ታወቀ
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርበኞች ግንቦት7 በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታጋይ አበበ ካሴ ፣ በእስር ቤት የተሰፋለትን ዩኒፎርም አልለብስም በማለቱ ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ መክረሙ ታውቋል። አበበ ዩኒፎረም እንዲለብስ ሲጠየቅ “ ጥሩ ጊዜ ላይ ነው ያሰፋችሁት እናንተው ትለብሱታላችሁ፣ እኔ አልለብስም” በማለቱ የተበሳጩት ፖሊሶች፡ ለወራት በጨለማ ቤት ውስጥ አስገብተው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ...
Read More »የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወለድ አርሶ አደሩን እያሰደደ ነው፡፡
ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ አርሶአደሮች ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የራሱ ድርጅት ከሆነው ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በምህጻረ ቃል አብቁተ በግድ ተበድረው እንዲወስዱ በማድረጉ፣ አርሶአደሮች በወለድ አመላለስ እና በምርታመነት ችግር ምክንያት መሬታቸው እና ከብቶቻቸው እየተወረሱባቸው እንደሚገኙ እየተናገሩ ነው። በምዕራብ አማራ በሚገኙ 73 ወረዳዎች አምና 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በግዳጅ በወሰዱት ብድር ምክንያት ...
Read More »