Amsterdam

እነ ታጋይ ገብሬ ንጉሴ በመንግስት ወታደሮቹ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አቃቢ ህግ ገለጸ

ሐምሌ ፲፪ ( አሥራ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታዩ ያሉት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት የሆኑት 14 ተከሳሾች፣ በ2007 ዓም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው በመግባት በመንግስት ወታደሮች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ የፌደራሉ አቃቢ ህግ በተከሳሾች ላይ ያቀረበው የክስ ዝርዝር ያመለክታል። የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በሰሜን ጎንደር ለሚካሄዱ ጦርነቶች በአደባባይ እውቅና የማይሰጥ ቢሆንም፣ በታጋይ ወታደሮች ...

Read More »

ከግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል ሐምሌ ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ ከተሞች ከእለታዊ ገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ ለሁለተኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሎአል። በአምቦ የንግድ ድርጅቶችና ሌሎች አገልግልሎት ሰጪ ተቋማት እንደተዘጉ ናቸው። በአምቦ መስመር ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ወለጋ የሚሄዱ መንገዶች በመዘጋታቸው የተሸከርካሪ አግልግሎት ተቋርጧል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ወረው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ላይ ናቸው። በጊንጪም እንዲሁ የተቃውሞውን ጥሪ ባለማክበር ሲሰራ የተገኘ አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሬ በድንጋይ ተሰባብሯል። በወሊሶም እንዲሁ አድማው ተጠናክሮ ቀጥሎአል። ሆቴሎችና ሱቆች ተዘጋግተዋል። የባጃጅ አገልግሎት ተቋርጧል። ፖሊሶች ከተማዋን ተቆጣጥረው ቅኝት እያደረጉ ነው። የክልሉ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በአምቦ የተጀመረው አድማ በሰላም መጠናቀቁን ቢናገሩም፣ አድማው ግን ዛሬም ድረስ ለሁለተኛ ጊዜ እንደቀጠለ ነው። አድማው በበርካታ አነስተኛ ከተሞችም በመካሄድ ላይ ነው። በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች አድማውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የሚያደርጉ ወረቀቶች እየተበተኑ ነው። በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ፣ ጂንካና በአካባቢው የሚገኙ ጋዘር፣ ቶልታ እና የመሳሰሉት ከተሞችም መንግስት የህዝቡን ገቢ፣ የኑሮ ሁኔታ ፣ እንዲሁም በየጊዜው ከህዝቡ በልማት ሥም በፈቃድና ጫና /ተጽዕኖ የሚሰበሰበውን ገቢና በባለሥልጣናት የሚመዘበረውን የህዝብ ሃብት ባላገናዘበ መንገድ የከመሩትን የቀን ገቢ ግምት ህዝቡ የማይቀበለው መሆኑ በግልጽ እየተነገረ ነው ፡፡ የንግዱ ማኅበረሰብ ዞናችን በድርቅ በተመታበትና የአርብቶአደር ህዝባችን የኑሮ መሰረት በተናጋበት ወቅት ‹አደጋውን በጋራ ለመመመከት በጋራ ምን ማድረግ እንችላለን› በሚል ሳያነጋግር፣ ዛሬ ‹‹ግብር ለመሰብሰብ መምጣቱን እንቃወማለን› እያሉ ነው።

ሐምሌ ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ ከተሞች ከእለታዊ ገቢ ግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ ለሁለተኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሎአል። በአምቦ የንግድ ድርጅቶችና ሌሎች አገልግልሎት ሰጪ ተቋማት እንደተዘጉ ናቸው። በአምቦ መስመር ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ወለጋ የሚሄዱ መንገዶች በመዘጋታቸው የተሸከርካሪ አግልግሎት ተቋርጧል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ወረው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ...

Read More »

አማራና ትግሬን እናስታርቃለን በሚል ህወሃት ያዘጋጀው ስብሰባ በራሱ ሽማገሌዎች ተተቸ

ሐምሌ ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመቀሌ ከተማ ለ3 ቀናት የአማራውና ትግራይን ህዝብ ለማስታረቅ የሚል አጀንዳ የተሰጠው ስብሰባ እክል ገጥሞታል። በብአዴንና በህወሃት የተመለመሉት የአገር ሽማግሌዎች፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደማያውቁ እየተናገሩ ነው። “በመጀመሪያ ህዝብ ከህዝብ አልተጣላም” የሚሉት ሽማግሌዎች፣ ያልተጣላን ህዝብ እንዴት አድርገው እንደሚያስታርቁ ግራ መጋባታቸውን ይናገራሉ። “ቁርሾው ያለው በህዝቡና በህወሃት መሪዎች መካከል እንጅ በትግራይና በአማራ ...

Read More »

በእነ ንግስት ይርጋ ላይ ለመመስከር የተጠሩ ምስክሮች ሳይቀርቡ ቀሩ

ሐምሌ ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በሴትነቷ ጥቃት እንደተፈጸመባት በቅርቡ ለህዝብ ይፋ ያደረገችው በሰሜን ጎንደር ተካሂዶ የነበረውን ህዝባዊ አመጽ በማስተባበር በተከሰሰችው ንግስት ይርጋ እና ሌሎች ተከሳሾች ላይ ሊቀርቡ የነበሩት የአቃቢ ህግ ምስክሮች ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ፌደራል ፖሊስ የምስክሮችን አድራሻ አለማግኘቱን በመናገር ሌላ ቀጠሮ ጠይቋል። የተከሳሾች ጠበቃ አቃቢ ህግ ለ5ኛ ጊዜ ቀጠሮ ...

Read More »

የያንግ ሩት እንግሊሽ እስኩል ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጠፋ

ሐምሌ ፲፩ ( አሥራ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኘው የያንግ ሩት እንግሊሽ እስኩል ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ጠፍትዋል። ተማሪዎቹ እና ወላጆች በውጤቱ መጥፋት ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መውደቃቸውን የትምህርት ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ታፈሰ ዋቺሶ ለሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ተናግረዋል። የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የፈተናውን ውጤት ለማግኘት የአዲስ አበባ ትምህርት ...

Read More »

በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የስራ ማቆም አድማ በመደረግ ላይ ነው

ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእለታዊ ገቢን ተንተርሶ የተጣለውን ግብር በመቃወም ለ3 ቀናት የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ሰኞ ተጀምሯል። ባለፈው ሳምንት ተቃውሞአቸውን ወደ አደባባይ በመውጣት ያሰሙት የአምቦ ነዋሪዎች፣ ዛሬ የንግድ ድርጅቶቻቸውንና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በመዝጋት ተቃውሞአቸውን በመግልጽ ላይ ናቸው። በአምቦ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ ትምህርት ቤቶችና አንዳንድ ባንኮች ተዘግተዋል። ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችም ተዘግተዋል። ...

Read More »

በቡሌ ሆራ የኦህዴድ ካድሬዎች ወጣቶችን አደራጅተው “ዘረኝነት የተሞላበት ቅስቀሳ” ሲያካሂዱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት እሁድ የኦህዴድ ካድሬዎችና የቀበሌው ሊቀመንበር ወጣቶችን አደራጅተው፣ በከተማዋ የሚኖሩ የሌሎች ብሄረሰቦች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅተው እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሙስሊሞች እና በአንድ ግለሰብ መካከል የቀብር ቦታን አስመልክቶ የ ድንበር ውዝግብ መነሳቱን የሚገልጹት የአይን ምስክሮች፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ካቢኔዎችንና ታጣቂዎችን ሰብስቦ ወደ ቦታው ሲሄድ፣ በአካባቢው ከነበሩ ሙስሊሞች ጋር ...

Read More »

በአርበኞች ግንቦት7 አባልነት በተከሰሱት ላይ ምስክሮች ተሰሙ

ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት አቃቢ ህግ በአርበኞች ግንቦት7 ስም በከሰሳቸው በእነ ትንሳኤ በሪሶ ላይ የደረጃ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል። የቀረቡት ሁለቱም ምስክሮች ማዕከላዊ ዐንጀል ምርመራ ቃላቸውን ሲሰጡ ታዝበናል ያሉ የደረጃ ምስክሮች ናቸው። እንዳልክ ዘርፉ የተባለው በአፍሪካ ህብረት ሰራተኛው በአቶ ትንሳኤ በራሶ ላይ የመሰከረ ሲሆን፣ አቶ ትንሳኤ “አይ ኤስ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ የዋስትና መብት ተፈቀደላቸው

ሐምሌ ፲ ( አሥር ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው በእስር ሲሰቃዩ የነበሩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ሲል የቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት ሀምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ተከሳሾች ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብሎ የዋስትና መብታቸውን ከመቀበሉ በተጨማሪ ጉዳያቸው ...

Read More »

ከግብር ጋር በተያያዘ ነጋዴዎች የሚያሰሙት ተቃውሞ ቀጥሎአል

ሐምሌ ፯ ( ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ መጠን ያለው ግብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ ነጋዴዎች ተቃውሞቸውን በስብሰባ ቦታዎች ከመግልጽ አልፈው ወደ አደባባይ በመውጣት በማሰማት ላይ መሆናቸውን ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። በአምቦ ትናንት ሃሙስ በተነሳው ተቃውሞ መኪኖች የተቃጠሉና የተሰባበሩ ሲሆን፣ በምስራቅ ሃረርጌ ደግሞ ከ3 ቀናት በፊት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በፈዲስ፣ ጭሮ ( አሰበ ተፈሪ)፣ ...

Read More »