ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ ላለፉት 2 ሳምንታት የተካሄደው የንግዱ ማህበረሰብ አድማ ዛሬም ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ በአየር ጤና አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ መደብሮችን በመዝጋት ተቃውሞ እያደረጉ ሲሆን፣ አካባቢው በፖሊሶች ተወሯል። በደጀን ከተማም እንዲሁ ትናንት የተጠራውን አድማ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ዛሬ ተግባራዊ አድርገውታል። ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ጭር ብላ የዋለች ሲሆን፣ ...
Read More »Amsterdam
በጉጂ ዞን ያለው ግጭት ተባብሶ ቀጥሎአል
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃምሌ 16 ቀን 2009 ዓም ከቀንድ ከብቶች መዘረፍ ጋር በተያያዘ በጉጂ ኦሮሞዎችና በኮሬ ብሄረሰብ መካከል የተጀመረው ግጭት ተባብሶ ቀጥሎአል። ካለፉት 4 ቀናት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት እስካሁን ከሁለቱም ወገን ከ13 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን እና ከ300 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ ገልማ መታሪ በሚባለው ...
Read More »አገሩ ባለቤት አልባ ሆኗል ሲሉ የኢህአዴግ የታች አመራር አባላት ተናገሩ
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ የወረዳ አመራሮች እንደሚሉት ባለፉት 26 ዓመታት አገሪቱ ባለቤት አልባ በመሆኗ ዝርፊያው ተጧጡፏል ። “ይችን አገር ከእንግዲህ ምን ልናደርጋት ነው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። አቶ መላኩ አምሳሉ ላለፉት 24 አመታት በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ ሰርተዋል። በእነዚህ አመታት ሁሉ የተረዱት ነገር ቢኖር አገሪቱ ባለቤት አልባ መሆኗን ነው። ሙስናው እና ቢሮክራሲው አለ፣ ...
Read More »አቃቢ ህግ የአቶ በቀለ ገርባን የዋስትና መብት ተቃወመ
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦፌኮ ም/ል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ የቀረበባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ተቀይሮና በወ/ህ ቁጥር 257/ሀ መሰረት እንዲከላከሉ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው መሆኑን ተከትሎ፣ አንቀጹ የዋስትና መብት የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢያመለክቱም፣ አቃቢ ህግ ተቃውሞ አቅርቧል። አቃቢ ህግ “ ይህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ማየት ሲጀምር በህግ አግባብ ተከሳሹን የዋስትና ...
Read More »በሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ወረቀት ከሌላቸው 400 ሺህ ከሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ወደ ሀገራቸው የተመለሱት 60 ሺህ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘገበ።
ሐምሌ ፲፱ ( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሪያድ ባለፈው መጋቢት ወር ህጋዊ ወረቀት የሌላቸው ስደተኞች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሯን እንዲለቅቁ የሰጠችው ማስጠንቀቂያና የጊዜ ገደብ የተጠናቀቀው ትናንትና ነው። በተጠቀሰው ጊዜ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ ባለመፈለጋቸው ዛሬ በሳኡዲ አረቢያ መንግስት ተጨማሪ የአንድ ወር የምህረት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያውያኑ ...
Read More »እየተካሄደ ያለው የነጋዴዎች አድማ እንደቀጠለ ነው
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት 2 ሳምንታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የሰነበተው የነጋዴዎች አድማ ዛሬም ቀጥሎአል። በታላቁ መርካቶ ገበያ ትናንት ሰኞ የተጀመረውን አድማ ለማስቆም ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የደህንነትና የፖሊስ ሰራዊት በማሰማራት በነጋዴዎች ላይ ማስፈራሪያ ሲያደርግ ቢውልም፣ ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች መደብሮች ተዘግተው ታይተዋል። በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቄራ የገበያ አዳራሽ ደግሞ ...
Read More »ህወሃት በአገሪቱ ለሚታየው ችግርና ለኢህአዴግ ውድቀት ብአዴንን ተጠያቂ አደረገ። የብአዴን አመራሮች የክልሉ ጸጥታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው በማለት ተናግረዋል።
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን የክልል አመራሮችን፣ ሁሉም የቢሮ ምክትል ኃላፊዎችን እንዲሁም በጥንቃቄ የመረጣቸውን አባሎቹንና አገዛዙን የደግፋሉ ያላቸውን የሃገር ሽማግሌዎች ቡድን ይዞ መቀሌ ቢሰነበትም፣ ያገኘው መልስ ወቀሳና ተጠያቂነትን ያዘለ ትችት ብቻ እንደነበር ምንጮች ይገልጻሉ። ብአዴንና ህወሃት የህዝብ ለህዝብ ፣ የከፍተኛ አመራሮች እና የሁለቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ብቻ የተገኙበትን “ሶስትዮሽ” የተባለውን ውይይት አድርገዋል። ...
Read More »በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ወጣት ህክምና ተከልክሎ ህይወቱ ማለፉ ተዘገበ
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የችሎቱን ውሎ ተከታትሎ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንደዘገበው በእነ መልካሙ ክንፈ የክስ መዝገብ በሽብር ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት ታስሮ የነበረው ወጣት አየለ በየነ ነገሰ ፣ ህክምና እንዳያገኝ ተከልክሎ ህይወቱ አልፏል። ወጣት አየለ በየነ ህክምና ተከልክሎ ለሞት እንደተዳረገ በአባሪነት የተከሱት እስረኞች፣ ሀምሌ 18/2009 ዓ.ም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ...
Read More »በጉጂ ኦሮሞዎቸና በደቡብ ክልል ልዩ ሃይል መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ሰዎች ተገደሉ
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት ቀናት በፊት የጉጆ ኦሮሞዎች ከብት መወሰዱን ተከትሎ በኮሬ ማህበረሰብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል ግጭት ቢነሳም፣ የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ጣልቃ በመግባትና በጉጂዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር 3 የጉጂ ብሄረሰብ አባላት ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ቡሌ ሆራ ሆስፒታል ተወስደዋል። ግጭቱ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ...
Read More »ፖሊስ በወልቃይት ኮሚቴዎች ላይ አንድ ምስክር ለማቅረብ የበጀት እጥረት ገጥሞኛል አለ
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ በሽብር ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት የወልቃይት ኮሚቴ አባላት ላይ በተደጋጋሚ ያልቀረበውን አንድ ምስክር አስሮ እንዲያቀርብ ታዞ የነበር ቢሆንም ምስክሩ የሚኖረው ትግራይ ክልል ውስጥ በመሆኑና በጀት ስላልተለቀቀልኝ ምስክሩን አስሮ የሚያመጣ አባል መላክ አልቻልኩም ሲል ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት መልሱን በደብዳቤ ገልፆአል። ...
Read More »