Amsterdam

አቶ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ውስጥ ህይወታቸው አለፈ

አቶ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ውስጥ ህይወታቸው አለፈ (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ እስከዳር ይርጋ ክስ መዝገብ በ”በሽብር” ክስ አራት አመት ተፈርዶበት ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ የነበረው 2ኛ ተከሳሽ ገበየሁ ፈንታሁን ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ግለሰቡ በህመም እንደሞተ የተገለጸ ቢሆንም፣ ታላቅ ወንድሙ ግን ሟቹ ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌለበት ገልጿል። ታላቅ ወንድሙ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ ሟቹ ከሶስት ቀናት በፊት ...

Read More »

የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል አስመልክቶ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቁ

የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል አስመልክቶ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቁ (ኢሳት ዜና የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ይዞታችን አይነካ ማለታቸውን ተከትሎ ከዋልድባ ገዳም ተይዘው በማእከላዊና በተለያዩ እስር ቤቶች ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የቆዩት መነኮሳት የደረሰባቸውን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በደብዳቤ አሳውቀዋል። በጻፉት ደብዳቤ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰቶች በዝርዝር አቅርበዋል። መነኩሳቱ በጻፉት ደብዳቤ እንደገለጹት ...

Read More »

ብአዴን አቶ ደመቀንና አቶ ገዱን በስልጣን ላይ ለማቆየት ወሰነ

ብአዴን አቶ ደመቀንና አቶ ገዱን በስልጣን ላይ ለማቆየት ወሰነ (ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በዝግ ስብሰባ ለሳምንታት ሲገማገም የሰነበተው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ አቶ ደመቀ መኮንን የድርጅቱ ሊ/መንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊ/መንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳልፏል። አቶ ገዱ በሌሎች ሰዎች እንደሚተኩ አስቀድሞ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ ግን ድርጅቱ በእርሳቸው መሪነት መቀጠሉን መርጧል። አቶ አለምነው መኮንን ብአዴን ...

Read More »

በምዕራብ ዕዝ በመከላከያ አባላት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ወታደሮች መቁሰላቸው ታወቀ

በምዕራብ ዕዝ በመከላከያ አባላት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ወታደሮች መቁሰላቸው ታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ከ10 ቀናት በፊት በባህርዳር ውስጥ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ ምድብ ውስጥ ወታደሮች ከብሄር ጋር በተያያዘ እርስ በርስ በመታኮሳቸው፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በወቅቱ ሌሊቱን የተኩስ ድምጽ ሲሰሙ ያደሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በሁኔታው ተደናግጠው ነበር። የክልሉ የኢሳት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል (ኢሳት ዜና የካቲት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተለያዩ የአምራች እንዱስትሪ ባለቤቶች ሲናገሩ ሲናገሩ ቢቆዩም፣ ችግሩ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጅ እየቀነሰ አልሄደም። በአሁኑ ሰዓት የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚጠበቀው ወረፋ ከአመት በላይ መሆኑን የሚናገሩት ባለሀብቶች፣ ያም ሆኖ በቂ ዶላር ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል ይላሉ። ...

Read More »

ኦህዴድ ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ለማን መገርሳን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መረጠ

ኦህዴድ ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ለማን መገርሳን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መረጠ (ኢሳት ዜና የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ድርጅቱ እንዳስታወቀው ኦህዴድን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ ለማ መገርሳን በደ/ር አብይ አህመድ ለመተካት በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አሳልፏል። ውሳኔው ኦህዴድ ዶ/ር አብይን ጠ/ሚኒስትር አድርጎ በእጩነት ለማቅረብ ፍላጎት ያለው መሆኑን አስተያየቶች ያመለከታሉ፡ ሰሞኑን የኦሮሞ የፖለቲካ አክቲቪስቶች አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮምያ ክልል ...

Read More »

በወልቂጤና በጎንደር አድማ አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው

በወልቂጤና በጎንደር አድማ አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በጉራጌ ዞን ለሳምንት ተደርጎ የነበረውን የስራ ማቆም አድማ አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታደኑ በመያዝ ላይ መሆናቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች እና በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚሳተፉ ዜጎች ሰልፍ አስተባብራችሁዋል በሚል ምክንያት ታስረዋል። እንዲሁም ማደኛ የወጣባቸው መምህራን መኖራቸውንም ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ...

Read More »

እነ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ከእስር ቤት ወጡ

እነ ጄ/ል ተፈራ ማሞ ከእስር ቤት ወጡ (ኢሳት ዜና የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በመፍንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው ያለፉትን 9 ዓመታት በእስር ያሳለፉት ጄ/ል ተፈራ ማሞ፣ ጄ/ል አሳምነው ጽጌ፣ ኢንጂነር መንግስቱ አበበ፣ ኮ/ል አበረ አሳፋ፣ ኮ/ል ሶሎሞን አሻግሬ፣ ሻለቃ ወርቁ በላይ ፣ ሻለቃ መስከረም ካሳ፣ ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣ ኢንስፔክተር አመራር ባያብል፣ የሽዋስ መንገሻ፣ ዋና ሳጅን ጎበና በላይና ሳጅን ይበልጣል ብርሃኑ ...

Read More »

አቶ ዓባይ ጸሃዬ የፌደራል መንግስት ፕሮጀክቶች በሕዝብ ብዛትና በመሬት ስፋት ቀመር ከሚሰራ ኢህአዴግ ቢፈርስ እንደሚመርጡ አስታወቁ

አቶ ዓባይ ጸሃዬ የፌደራል መንግስት ፕሮጀክቶች በሕዝብ ብዛትና በመሬት ስፋት ቀመር ከሚሰራ ኢህአዴግ ቢፈርስ እንደሚመርጡ አስታወቁ (ኢሳት ዜና የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) የብአዴንና የኦህዴድ አመራሮች የፌደራል መንግስት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በሕዝብ ብዛትና በመሬት ስፋት ቀመር መሰረት እንዲሰሩ የሚያቀርቡትን ሃሳብ ውድቅ ያደረጉት አቶ አባይ፣ እንዲህ አይነት አሰራር ተግባራዊ ከሚሆን ኢህአዴግ ቢፈርስ እንደሚመርጡ ተናግረዋል። አቶ ዓባይ ጸሃዬ የብአዴንና ኦህዴድ አመራሮች፣ የቢሮ ...

Read More »

ደቡብ ሱዳን ተጠልፈው የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ህጻናትን እንደምትመልስ አስታወቀች

ደቡብ ሱዳን ተጠልፈው የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ህጻናትን እንደምትመልስ አስታወቀች (ኢሳት ዜና የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ/ም) የደቡብ ሱዳን ፣ የቦማ ግዛት ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ ታፍነው ወደ ደቡብ ሱዳን የተወሰዱ ህጻናትን እንደሚያስመልሱ ቃል ገብተዋል። ሬዲዮ ታማዙጂ እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት በቅርቡ ታፍነው ከተወሰዱ ህጻናት መካከል 4 ህጻናትን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። እነዚህን ህጻናት ለጋምቤላ ባለስልጣናት እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል። የአገሪቱ ባለስልጣናትም ሆኑ የጋምቤላ ክልል ባለስልጣናት ሰሞኑን ...

Read More »