Amsterdam

የደህንነት መስሪያ ቤቱ የነጻነት ታጋዮችን በድለላ ለማስገባት የጀመረው ጥረት እስካሁን ውጤት አላመጣም

ጥቅምት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ በረሃዎች የሚንቀሳቀሱ በርካታ የነጻነት ሃይሎችን በማታለል እጃቸውን ለህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት  የነጻነት ሃይሎች ውድቅ አድርገውታል። ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች ጋር በተያያዘ አገዛዙ የወሰደው እርምጃ በርካታዎች ጫካ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። በጎንደር የተካሄዱትን ታውሞዎች ተከትሎም፣ ብዙ ወጣቶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጫካ የገቡ ሲሆን፣ በአገዛዙ ወታደሮችና ድርጅቶች ...

Read More »

በአማራ እና በሌሎችም ክልሎች እስራቱና ድብደባው በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ኮማንድ ፖስት በሚል ባቋቋመው የአፈና መዋቅሩ የአማራ ክልል ወጣቶችንና የመንግስት ሰራተኞችን ኢላማ  በማድረግ ከፍተኘ ስቃይ እየፈጸመ ነው። ህወሃት የበቀል ጅራፉን በክልሉ ዜጎች ላይ አሳርፎአል የሚሉት ነዋሪዎች፣ ድርጊቱ ወደ አልተፈለገ ደም መፋሰስ ሊያመራ እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው። ባለፉት አራት ቀናት በተለያዩ የክልሉ ከተሞች በርካታ ወጣቶች ታፍሰው በገፍ ወደ እስር ...

Read More »

በእነዋሬ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ከአካባቢያቸው  ከሚዘረፈው  ማዕድን ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን ከእነዋሪ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የወረዳዋ ሃብት ከሆኑ ተራራዎች ለሲሚንቶ አገልግሎት ሊውል የሚችል ማዕድን በየቀኑ እየተጫነ መጓጓዙ አግባብ አለመሆኑን በእነዋሬ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በየቀኑ የሚመላለሱት ከባድ የጭነት ተሸከርካሪዎች የከተማዋን መንገድ በማፈራረስ ላይ መሆናቸውንም የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው  የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ ሊሆን የሚገባው የአካባቢው ማህበረሰብ መሆን ሲገባው ...

Read More »

የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጸሃፊ የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ለሚታየው ችግር አስቸካይ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠየቁ

ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ሕብረት ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኒኮላ ዛና ዲላሚኒ ዙማ በኢትዮጵያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ አስመልክቶ ሁሉን ያሳተፈ አስቸኳይ የሆነ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርብዋል። ዋና ጸሃፊዋ ሁሉንም ያሳተፈ ድርድር ማድረግ ለአገሪቷ የመጨረሻ አስተማማኝ እና ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ያስገኝላታል ሲሉ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች እና ...

Read More »

የቀበና ችግኝ ጣቢያ ቦታ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤት መስሪያ ተሰጠ

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ10 ሺ ካሬ መሬት በላይ ስፋት ያለው የቀበና ችግኝ ጣቢያ ተነስቶ ፣ ቦታው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን መኖሪያ ቤት መስሪያ ተሰጥቷል። ግንባታው የሚካሄደው በመንግስት ወጪ ሲሆን፣ ወ/ሮ አዜብ ቦታውን በስማቸው አዙረዋል።የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ቦታውን ለቤተመንግስት ሰዎች እንዲያስረክብ የተጠየቀበት፣እንዲሁም የከንቲባ ጽ/ቤት ለቦሌ ክፍለ ከተማ መስተዳደር የጻፉዋቸው ደብዳቤዎች እና ሌሎችም ...

Read More »

በርካታ የጎንደር እስር ቤቶች በእስረኞች ተጨናንቀዋል ተባለ

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮማንድ ፖስት እያለ ራሱን የሚጠራው የህወሃት/ኢህአዴግ የአፈና መስመር ዛሬ በጎንደርና ባህርዳር እንዲሁም በዙሪያ ከተሞች ከፍተኛ አፈሳ ሲያካሄድ ውሎአል። በጎንደር ቀበሌ 2፣ 4 እንዲሁም 14 በርካታ ሰዎች ኢሳትን ታያላችሁ በሚል መታሰራቸውን ተከትሎ እስር ቤት በእሰረኞች ተጨናንቀው ታይተዋል።ፖሊሶች ጣራ ለጣራ እየወጡ ዲሽ ሲነቅሉ መዋላቸውም ታውቋል። በዳባትም እንዲሁ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። በባህርዳር ...

Read More »

የአቶ አንዳርጋቸው የደኅንነት ሁኔታ እንዳሰጋው ሪፕሪቭ አስታወቀ

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዓለምአቀፍ ሕግን በሚጻረር መልኩ ከየመን ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ታግተው የተወሰዱት የነፃነት ታጋዩ የአቶ አንዳርጋቸው የደኅንነት ሁኔታ እንዳሰጋው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው የህግ ባለሙያዎች ስብስብ አስታውቋል።የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ የሞት ቅጣት ባለባት ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኘው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚገኝና  የደኅንነቱ ሁኔታ ...

Read More »

በአባይ ግድብ ተቀጥረው የሚሰሩ ከ30 በላይ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች ታፍነው ተወሰዱ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሚፈለጉት መካከል ግድቡ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤት ስራ አስኪያጅም ይገኙበታል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓም በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከ30 በላይ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ተይዘው ሲታሰሩ፣ የአካባቢው የንግድ ባንክ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊያዙ ሲሉ አምልጠዋል። በርካታ ወታደሮች ወደ አካባቢው በመሰማራት በሜቴክ እና በሳሊኒ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ቤት የማፍረሱ ዘመቻ ተጀመረ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ቤት የማፍረሱ እንቅስቃሴ እንደአዲስ ተጀምሯል። በለገጣፎና አካባቢዋ ዛሬ በርካታ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ ብዛት ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትና ቀይ ኮፍያ ለባሽ የአጋዚ ወታደሮች በብዛት ቁጥጥር ሲያደርጉ ውለዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች አገዛዙ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ማንኛውንም አይነት ተቃውሞ ማድረግ ስለማይችሉ፣ አጋጣሚውን በመጠቀም ቤት የማፍረሱ ዘመቻ ...

Read More »

አልሸባብ ለኢትዮጵያ ሲሰልሉ ነበሩ የተባሉ አምስት ሶማሊያዊያንን አንገት ቀላ

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር ላለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እና ለሶማሊያ መንግስት በመረጃ እና ስለላ ስራ ላይ በመሰማራት ድጋፍ ሰጪ ሆነው ሲያገለግሉ ነበሩ ያላቸውን አምስት ሶማሊያዊያንን አንገት መቅላቱን አልሸባብ አስታውቋል። አልሸባብ የታይግሎ ከተማን ከተቆጣጠረ ወዲህ በከተማ ያለው ድባብ አስፈሪ ነው። አምስቱን ሰላማዊ ንጹሃን ዜጎችን ጨምሮ ነጋዴዎችና ...

Read More »