ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉት የትምህርት እርከኖች ባለፉት አመታት ከታሰበው ግብ ለመድረስ እንዳልቻለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ገለጹ፡፡ አቶ ብናልፍ ሰሞኑን ከትምህርት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ስለዓለፈው ዓመት የትምህርት አፈጻጸም በተወያዩበት ጊዜ እንደተናገሩት አጠቃላይ የርብርብ ማዕከል ይሆናል ተብሎ በተያዘው ዕቅድ መሰረት በቅድመ መደበኛ፣በመጀመሪያ ደረጃ፣በሁለተኛ ...
Read More »Amsterdam
ካናዳ በኢትዮጵያ ሁሉንም ያሳተፈ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሄድ ጠየቀች
ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታዎች እያሳሰበው መምጣቱንና በሰላማዊ እና ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ የአገሪቱን ችግሮችን ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ውይይቶች በማካሄድ ፖለቲካዊ ተሃድሶ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል። በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በተነሱት ሕዝባዊ አመጾች ምክንያት ብዙ ዜጎች በመገደላቸው በአካባቢዎቹ አለመረጋጋቶች ተፈጥረዋል። ሁኔታዎቹ ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው አስቀድሞ መፍትሔ እንዲበጅላቸው ሲሉ በካናዳ መንግስት የውጭ ...
Read More »የመን በእስር ላይ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች 150 ዎቹን ወደ አገራቸው መለሰች
ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሕርና በረሃ አቆራርጠው በሕገወጥ መንገድ ወደ የመን ገብተዋል ያለቻቸውን ቁጥራቸው 150 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም (IOM) አማካኝነት ወደ ትውልድ አገራቸው መላካቸውን የመን አስታውቃለች። በቀይ ባህር ዳርቻ በምትገኘው የወደብ ከተማዋ ሁዴዳ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት እስረኞች መካከል 150 በጎ ፈቃደኛ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከአይኦኤም ጋር በመተባበር ወደ ትውልድ ...
Read More »በወገራ በነጻነት ሃይሎችና በወታደሮች መካከል ያለው ፍጥጫ ቀጥሎአል
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ እንቃሽ በሚባለው አካባቢ የሚገኙ የነጻነት ሃይሎች ከህዝብ ጋር በመተባበር በመንግሰት ታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሱ በሁዋላ፣ አሁንም ፍጥጫው መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። እነዚህ ራሳቸውን ያደራጁ ሃይሎች እንደገለጹት፣ ከትናንት ጀምሮ ቀሳውስቱ በመካከላቸው ትልቅ መስቀል በማቆም ጦርነቱ እንቆም ቢያደርጉም አሁንም ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዞ ተፋጦ ይገኛል። ወታደራዊ አዛዦች ...
Read More »የኮንሶ ህዝብ መሪዎች እየታደኑ ነው
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንሶ ህዝብ ያቀረበውን ጥያቄ በሃይል ለመጨፍለቅ ተደጋጋሚ የአፈና እርምጃ ሲወስድ የቆየው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ተቃውሞውን ያስተባብራሉ ያላቸውን የአካባቢውን የአገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለመያዝ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ብዙዎች ራሳቸውን ለመደበቅ ተገደዋል። አገዛዙ፣ መሪዎቹን በአሸባሪነት የፈረጃቸው ሲሆን፣ በተገኙበት እንዲያዙ አልያም እንዲገደሉ ትእዛዝ መስጠቱን መንጮች ገልጸዋል። ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ ተፈላጊ ሰዎችን ጠቁሙ እየተባሉ ስቃይ እየደረሰባቸው ...
Read More »ጸሃፊ በፈቃዱ ሃይሉ ታሰረ
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ ፖለቲካዊ ትችቶችንና መረጃዎችን በመጻፍ የሚታወቀው በፈቃዱ ሃይሉ ህዳር 02/2009 ዓም “ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋሀል” ተብሎ በፖሊስ ተጠርቶ በድጋሜ ለእስር ተደርጓል። በ2006 ዓም ዞን ዘጠኝ እየተባሉ ከሚጠሩ ጻሃፊዎች ጋር ታስሮ ከ18 ወራት የእስር ጊዜ በሁዋላ በ20 ሺ ብር ዋስ የተፈታው በፈቃዱ ፣ ከእስር ከወጣ በሁዋላ ውይይት መጽሄት ላይ በዋና አዘጋጅነት የስራ ...
Read More »በአፋር ክልል በዞን ሶስት የኮሌራ በሽታ የነዋሪዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው
ኅዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በዞን ሶስት በገዋኔ፣ ቡሪሞዳይቶና አሚባራ ወረዳዎች ውስጥ የተከሰተው ከፍተኛ የኮሌራ ወረርሽኝ ህጻናትንና አዛውንቶችን እየቀጠፈ ነው። እስካሁን ድረስ ለበሽታው በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ የጉዳት መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።
Read More »በወገራ ወረዳ በእንቃሽ በተደረገው ውጊያ የተገደሉት የመንግስት ታጣቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ኅዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጦርነቱ የተካፈሉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት በእንቃሽ በህዝብ በሚደገፉት የነጻነት ሃይሎች በአንድ ወገን የመንግስት ታጣቂዎች በሌላ ወገን ባደረጉት ውጊያ 23 የመከላከያ፣ 4 የጸረ ሽምቅና 3 የአካባቢ ሚሊሺያ ወይም ጉጅሌ ተገድለዋል። 25 የሚሆኑ ወታደሮች የተማረኩ ሲሆን፣ ከ20 በላይ ደግሞ ቆስለዋል። በውጊያው መትረጊስ፣ ክላሽንኮቭ፣ አብራራውና ሌሎችም የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎች ከአንድ የመገናኛ ሬዲዮ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን የነጻነት ሃይሎች እና የመንግስት ወታደሮች ለሁለተኛ ቀን ተዋጉ
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የህወሃት/ ኢህአዴግን አገዛዝ በመሳሪያ ሃይል ለመታገል ወደ ጫካ የወጡ የነጻነት ሃይሎች በየጊዜው ከመንግስት ወታደሮች ጋር እየተታኮሱ ሲሆን፣ ትናንት በወገራ ወረዳ እንቃሽ በሚባለው አካባቢ የተደረገው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ መዋሉንና በርካታ የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። የተወሰነ የመንግስት ታጣቂዎች አስከሬን ጎንደር ከተማ ገብቷል። የነጻነት ሃይሎች እንደሚሉት ምንም አይነት ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በሁዋላ የሞጣ መምህራን አድማ በመምታት የመጀመሪያዎቹ ሆኑ
ጥቅምት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንም አይነት የስራ ማቆም አድማ ማድረግም ሆነ መሰብሰብ ህገወጥ መሆኑን ዝርዝር መመሪያ ካወጣ የሞጣ ከተማ መምህራን የስራ ማቆም አድማ በማድረግ የመጀመሪያ ሆነዋል። መምህራኑና ተማሪዎች ትናንት የጀመሩትን ተቃውሞ ዛሬ ትምህርት በመዝጋት የቀጠሉ ሲሆን፣ የከተማዋ ባለስልጣናትና የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተማሪዎችን እና መምህራንን በማስፈራራት ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም። መምህራኑና ...
Read More »