Amsterdam

በቂሊንጦ እስር ቤት በእሳት ቃጠሎ እና በጥይት ለተገደሉ ታራሚዎች ሞት 38  እስረኞች ተጠያቂ ሆኑ

ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ነሃሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ሆን ተብሎ የእሳት ቃጠሎ እንዲነሳ በማድረግ ከእሳቱ ለመሸሽ ሲያመልጡ የነበሩ ታራሚዎች በእሳት ቃጠሎ እና በግፍ በጥይት ተደብድበው መገደላቸው የሚታዉቅ ሲሆን ለዜጎች ሞት ምክንያት ናቸው የተባሉ 38 እስረኞች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ዛክስ ተመስርቶባቸዋል። እስረኞቹ ሆን ብለው እሳት እንዲነሳ ያደረጉት በድብቅ ...

Read More »

አልሸባብን ለማስወጣት ተጨማሪ 4 ሺ ወታደሮች ያስፈልጋሉ ተባለ

ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ አሚሶም  ስር የተሰማራው  ጦር፣ በአሁኑ ወቅት አልሸባብ ከተቆጣጠራቸው የሶማሊያ ግዛቶች ለማስወጣት ተጨማሪ 4 ሺህ ወታደሮች ማሰማራት እንደሚያስፈልጉት አስታውቋል። ጁባ ሸለቆ፣ ሂራን፣ በቆል እና አንዳንድ የተወሰኑ የድንበር ከተሞች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ውለዋል። የኅብረቱ ጦር ቃል አቃባይ የሆኑት ኮሎኔል ጆሴፍ ጊበርት እንዳሉት አሁን ካሉ 21 ሽህ ...

Read More »

የወልቃይት ማንነት ጥያቄ በሃገሪቱ ለተከሰቱት ህዝባዊ ተቃውሞዎች መነሻ በመሆኑ ባስቸኳይ ይፈታ ዘንድ  የምክር ቤት አባላት ጠየቁ

ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ምክር ቤት በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ የተገኙ የልዩ ልዩ ወረዳ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ባነሱት ጥያቄ የድንበር መካለሉ ጉዳይ ለበርካታ የሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኖ እያለ ምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት ጉዳዩ ወደ የሚመለከተው አካል ተላልፏል መባሉ እንዳልተዋጠላቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ በክልሉ ለተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ መንስዔ የመንግስት የመዘናጋት ውጤት እንደሆነ ...

Read More »

በቤንሻንግል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መሬታቸውን ያለ ከሳ እየተቀሙ መሆኑን ገለጹ

ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው በክልሉ ተወልደው ያደረጉ የአማራ ተወላጆች እንደገለጹት ቀደም ብሎ በነበረው መንግስት በሰፈራ ፕሮግራም አማካኝነት አሁን ቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ሄደው እንዲሰፍሩ ከተደረገና ልጆችን ወልደው፣ ቤት ንብረት አፍርተው ለአመታት ከኖሩ በሁዋላ፣ የአገዛዙ ሹሞች በተለያዩ ሰበብ አስባቦች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጫና እየፈጠሩባቸው ነው። ነዋሪዎቹ ልማት ላይ ያልዋሉ ቦታዎችን ገንዘባቸውን፣ ...

Read More »

በኢትዮጵያ በምርት መሰብሰቢያ ወቅት የዋጋ ንረት መከሰቱን የዓለም ምግብ ድርጅት ወርሃዊ ጥናት አስታወቀ

ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየዓመቱ እየባሰበት የመጣው የኢትዮጵያ የዋጋ አለመረጋጋት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን የማእከላዊ ስታስቲክ ጽፈት ቤትን ዋቢ በማድረግ የዓለም የምግብ ድርጅት በወርሃዊ የጥናት ሪፖርቱ አመላክቷል። ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ 5.6% የነበረው የምግብ ፍጆታ በሕዳር ወር ወደ 3.4% ከፍ በማለት ጭማሪ አሳይቷል። ይህም በአገሪቱ ውስጥ የዋጋ ንረት ማስከተሉን የደንበኞች የዋጋ አመላካች Consumer Price Index ...

Read More »

ዶክተር አብርሃም ይሳቅ በእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የመጀመሪያው ቤተእስራኤላዊ ኮሎኔል ሆነው ተሾሙ

ኅዳር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ19 ዓመታቸው ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የተጓዙት ኮሎኔል ይስሃቅ፣ በወታደራዊ ሕክምና አገልግሎት በዶክተርነት ሲገለግሉ መቆየታቸው ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በአዲ ጎሹ ፣ ቃፍታ ሁመራ አካባቢዎች ውጊያ ማካሄዱን አስታወቀ

ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከድርጅቱ ወታደራዊ ክፍል የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት ሳምንታት የድርጅቱ ታጣቂዎች በቃፍታ ሁመራ፣ አዲ ጎሹና አርማጭሆ አካባቢዎች ከህወሃት/ኢህአዴግ ቃኝ ወታደሮች ጋር ተከታታይ የተኩስ ልውውጦችን አድርገዋል።በተኩስ ለውውጡ ከመንግስት በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ሙት እና ቁስለኛ ቢሆንም፣ ከነጻነት ሃይሎች በኩል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ድርጅቱ ምርመራ እያደረ መሆኑን ገልጿል። “የንቅናቄው ሃይሎች አንዳንድ ቦታዎችን ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ  ዞን ጂንካ ከተማ የተጠራው ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ

ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ የኢህአዴግ አባልና ደጋፊ የመንግሥት ሠራተኞችን ለይተው ‹‹በወቅታዊ ጉዳዮች›› ላይ ለማወያየት የተጠራው ስብሰባ ሠራተኛው በስብሰባው ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይሳካ መቅረቱን የከተማው ሠረተኞች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሰኞ ህዳር 12/2009 ዓ.ም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ሥራ ገበታው ሲገባ የቢሮ ኃላፊዎች  የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑትን ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ እየተባባሰ ቢመጣም  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እርዳታ ለማከፋፈል ሳንካ ፈጥሯል ተባለ

ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አጥኚ ቡድን ከ ኢትዮጵያ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የድርቅ አደጋ ያንዣበባቸውን አካባቢዎች ለይተው አውጥተዋል። በደቡባዊ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢ አርብቶ አደሮች ለረሃብ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል። ለጉዳተኞቹ እርዳታዎችን ለማሰራጨት አስቸኳይ አዋጁን ተከትሎ የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው እና መንገዶች ዝግ መደረጋቸው የሰዎችን ሕይወት ለመታደክ ከፍተኛ ሳንካ ፈጥሯል። ...

Read More »

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ የታፈሱት ወጣቶች ይፋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ታስረዋል

ኅዳር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተከትሎ ከተለያዩ  የሃገሪቱ ስፍራዎች ታፍሰው የታሰሩት እስረኞች ገሚሶቹ በአዋሽ አርባ፣ በኦሮሚያ ፖሊስና በቀድሞው ህጻናት አምባ አሁን አላጌ የግብርና ኮሌጅ በመባል በሚጠራው ስፍራ እንደሆነ ታውቋል። መንግስት አዋጁን ለማስከበር በሚል ከ20ሺ እስከ 30ሺ ይደርሳል ተብሎ  የሚገመቱ ታሳሪዎችን ቤተሰብና ዘመድ ሊያውቀው በማይችልበት ስፍራ ወስዶ ማሰሩ በታሳሪዎቹ ላይ የስነ ልቦና ጫና ...

Read More »