ኅዳር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያኑ በሴውል ከተማ በመሰባሰብ በአሉን ያከበሩ ሲሆን፣ በበአሉ ላይ የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አበበ ገላው በስካይፕ ተገኝቶ ንግግር አድርጓል። ኢትዮያውያኑ ኢሳትን በቋሚነት ለመደገፍ ቃል መግባታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ተመሳሳይ የኢሳት ስድስተኛ አመት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በእንግድነት በተገኘበት በፍራንክፈርት ፣ ጀርመን ተከበሯል።
Read More »Amsterdam
በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድ ዋለ
ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም ልዩ ስሙ ሃመረ በተባለ ቦታ ላይ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሃት /ኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸው ታውቛል። ከሁመራ ወደ ቀራቀር በሚወሰደው መንገድ ላይ ቁስቋም ማሪያም አካባቢ በሚገኝ ዳገት ላይ፣ በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አባል ...
Read More »የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደብድበው ታሰሩ
ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና (ቬተርናሪ ሳይንስ) ፋካልቲ የሚማሩ ተማሪዎች የምንማረው ትምህርት ስራ የማ ያሲዘንና የስራ እድል የማይፈጥር ነው በማለታቸው ብቻ ወታደሮች ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የፀረ -ሽምቅ አባላትና መደበኛ ፖሊሶች ወደ ግቢው በመግባት ተማሪዎችን ደብድበዋል። ከ100 በላይ ተማሪዎች ታፍነው በ2 አውቶብሶች ተጭነው ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ወታደሮች በአራቱም መአዘኖች ...
Read More »በሶማሊያ በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ዜጎች ወደ ዶሎ አዶ እየተፈናቀሉ ነው
ኅዳር ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ ያገረሸውን የእርስበርስ ጦርነት እና ድርቅ ሸሽተው ከሶማሊያ የተሰደዱ ተፈናቃዮች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አሳዋኝ ወደምትገኘው ዶሎአዶ ከተማ እየፈለሱ መሆኑን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታውቋል። ግጭቱን ሸሽተው ለመጡ ተፈናቃዮች በዶሎ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ሕጻናት እና አዛውንት ለ ከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ተገልጿል።
Read More »በአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮችና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር በአርማጭሆና ሌሎችም ቦታዎች በአርበኞች ግንቦት7 ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የአርበኞች ግንቦት 7 አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መከበቡብ እንዳወቀ ራሱን ሰውቷል። ቀደም ብሎ በኢህአዴግ መከላከያ ውስጥ ሲያገለግል ቆይቶ፣ በስራዊቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነትና በህዝቡ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ መቋቋም ተስኖት፣ አርበኞች ግንቦት 7ትን የተቀላቀለው ...
Read More »ወታደራዊ እዙ ( ኮማንድ ፖስት) በአዳማ ተቃውሞ ገጠመው
ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ከሰኞ እስከ ዓርብ ኢህአዴግና የከተማው መስተዳድር በአዳማ ከተማ ከኢህአዴግ አባላትና ደጋፊ የከተማው ነዋሪዎች ጋር ስለ ወታደራዊ እዙ ተግባርና ኃላፊነት፣ ስለተደረገው ሹም ሽር እንዲሁም የክልሉንና የከተማዋን ልማትና ጸጥታ ሁኔታ በሚመለከት በተደረገው ስብሰባ ላይ ያልተጠበቀ ተቃውሞ ተነስቷል። በዚህ መድረክ የተሳተፉት የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ቢሆኑም የከተማዋ የኮማንድ ፖስት ኃላፊ ማንነት እንደተገለጸ ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረጉት ፍተሻዎች የህብረተሰቡን ኑሮ እያወኩ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ኅዳር ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በሚደረጉ ፍተሻዎች ነዋሪው እየታወከ መሆኑን በባህርዳር የጣናና ሽምብጥ ክፍለከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት ተናገሩ፡፡ በውድቅት ሌሊት የመንግስት ወታደሮችና ታጣቂዎች በወደ ግለሰቦች ቤት በመግባት ‹‹ፍተሻ እናካሂዳለን!!›› በማለት ከሌሊት እስከ ንጋት ድረስ ሲያንገላቷቸው ያድራሉ፡፡በተለይ በጣና ክፍለ ከተማ ቀጠጢና በተባለ መንደር የሚገኙ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ወደ ሆቴል ...
Read More »በተለያዩ የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ውጊያዎች በመካሄድ ላይ ናቸው
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ዛሬ በአብድራፊ አንገረብ ወንዝ አካባቢ ራሳቸውን ባደራጁ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዷል። ዛሬ ሲካሄድ በዋለው ውጊያ በነጻነት ሃይሎችም ሆነ በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። በሌላ በኩል በወልቃይት ትርካንና ማይነብሪ አካባቢ በአርበኞች ግንቦት7 ወታደሮችና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል መለስተኛ ውጊያ ...
Read More »በጂማ ዩኒቨርስቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ተማሪዎች ሌሊቱን ሲደበደቡ አደሩ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በቲቶ ፉርጊሳ የምህንድስና ትምህርት ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች የጀመሩትን ተከታታይ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ወታደሮች ተማሪዎችን ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በማውጣት እስከ ሌሊቱ 11 ሰአት ድረስ እየደበደቡ ከፍተኛ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል። የኮማንድ ፖስትን በመወከል ተማሪውን ዛሬ የሰበሰቡ አካላት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። እንደ ተማሪዎቹ ገለጻ የኮማንድ ፖስት ወኪሎች ‹‹ አርፈን ...
Read More »በሃረር በርካታ ዜጎች ሲታሰሩ በባህርዳር ደግሞ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኅዳር ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመጪው ህዳር 29 ቀን 2009 ዓም ከሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል ጋር በተገናኘ ይሁን አይሁን ባይታወቅም፣ በሃረር ከተማ ከፍተኛ ፍተሻ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በፍተሻ ወቅት የክልሉን መታወቂያ ያልያዙ ሰዎች እየተያዙ ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ከሌሎች ክልሎች ሄደው በክልሉ ውስጥ በመስራት ላይ ያሉ በርካታ ዜጎች፣ የክልሉን መስተዳድር መታወቂያ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ከመጣችሁበት ክልል ...
Read More »