ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ዲማ ነገዎ ይህን የተናገሩት፣ በጀርመን የሙኒክ ከተማ ንቅናቄውን ለህዝብ ለማስተዋወቅና ድጋፍ ለመሳበሰብ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ነው። “ኢህአዴግ አርበኞች ግንቦት7 ትን ካወገዛችሁ ከእናንተ ጋር ድርድር ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ቢላችሁ፣ ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ትሆናላችሁ? “ ወይ ተብሎ ለቀረቡላቸው ጥያቄ ፣ ዶ/ር ዲማ ...
Read More »Amsterdam
የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች ሃረርን አጨናንቀዋል
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው ህዳር 29 የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል ምክንያት በማድረግ በከተማው የሚታየው የጸጥታ ቁጥጥር የከፋ መሆኑን ገልጿል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ወደከተማ የገቡ ሲሆን፣ ለጸጥታ ስጋት ናቸው የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። ከሃረር ወጣ ብሎ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ከ500 በላይ የሚሆኑ የአማራ እና የሌሎችም አካባቢ ...
Read More »በአማራ ክልል የብአዴን አባላት ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ግምገማ ጀመሩ።
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩ የብአዴን አባላት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥልቅ ተሃድሶ በሚል ግምገማ ተጀምሯል። በክልሉ የውሃ ሃብት ውስጥ የሚሰሩ የብአዴን አባላት በአማራ ክልል መሰብሰቢያ አዳራሽ ዓርብ ሕዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም የተጀመረው ስብሰባ ከተወያዮቹ ከፍተኛ ተቃውሞዎች ቀርበውበታል። ስብሰባውን በዋና አወያይነት የመሩት በአማራ ክልል የምእራብ አማራ የውሃ ...
Read More »የዶ/ር መረራ ጉዲና እስራት እንዳሳሰበው የአሜሪካ መንግስት መግለጫ አወጣ
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር እና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና እስራት እንዳሳሰበው የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቃል አቀባዩ በኩል የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ማርክ ቶነር እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር መረራ ጉዲና ማሰሩን የአሜሪካ መንግስት መንግስት እያሳሰበው መምጣቱን እና ...
Read More »የአማራ ክልል የጎንደር ማረሚያ ቤት ሃላፊ የታሰሩት በፌደራል ደህንነትና አቃቢ ህግ ነው አለ
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው አርብ ጀምሮ በቁጥጥር ስር የሚገኙት የጎንደር ማረሚያ ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ልጃለም መሰረት ፣ ደብዳቤ እንዲያስገቡ ተነግሯቸው ለክልሉ መንግስት “ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ ወይም እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ቢያስገቡም፣ የአማራ ክልል መንግስት “ አንተን ያሰረህ የፌደራል ደህንነትና የፌደራል አቃቢ ህግ በመሆኑ ክልሉ አያገባውም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ኢንስፔክተር ልጃለም ለፌደራል ጠ/አቃቢ ህግ ...
Read More »ነጋዴዎች በካሽ ሬጀስትራር ማሽን ለብዝበዛ እየታጋለጡ መሆኑን ገለጹ።
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በአገሪቱ የኢንትርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉን ተከትሎ የሂሳብ ማሽን (ካሽ ሬጀስትራር) የሚጠቀሙ የመርካቶ ነጋዴዎች ፣ ማሽናቸው ከጥቅም ውጭ በመሆኑ እሱን ለማስተካከል ማሽኖችን ወደ ገዡባቸው ድርጅቶች ሲሄዱ በነፍስ ወከፍ 280 ብር እንደሚጠየቁ ነጋዴዎች ተናግረዋል። “ ችግሩ የእኛ አይደለም፣ ችግሩ የመንግስትና የቴሌ ነው። እኛ ማሸን ግዙ ተብለን ገዛን፣ ቴሌ ደግሞ ኔትወርክ አቋረጠብን፣ ...
Read More »ነዋሪነቱ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ ውስጥ የሆነ የሰላማዊ ሰልፈኛ ቤተሰብ ታሰሩ ።
ኅዳር ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የሕግ ጠበቃና ዳኛ የነበሩት ሽኩሪ ሻፊ በአውስትራሊያ ከሚገኙ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የሶማሌ ብሔር ተወላጆች ጋር በመኾን ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ኡመር የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር። አቶ ሽኩሪ ሻፊ በሜልቦርን ከተማ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፉ ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ሦስት ወንድሞቻቸውን ...
Read More »የዶክተር መረራ ጉዲና መታሰር አለማቀፍ ትኩረት እያገኘ ነው
ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና በአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በተጋባዥነት እንግድነት ንግግር አድርገው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በህወሃት ኢህአዴግ ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር አስመልክቶ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ አውጥቷል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ እና ታላላቅ ሃይቆች ምክትል ዳሬክተር ...
Read More »በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ ፖሊሶች ታሰሩ
ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶስት ቀናት በፊት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው በፌደራል ፖሊስ ዋናው ጽ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ውስጥ ቦንብ ተገኝቷል በሚል ሰበብ በርካታ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ ፖሊሶች ታሰረዋል። ምንጮች እንደገለጹት ቦንቡ ሆን ተብሎ ፖሊሶችን ለማጥመድ ተብሎ በህወሃት የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰዎች የተቀነባባረ ነው። በወንጀል ምርምራ ክፍል ውስጥ የጦር መሳሪያ እንደማይገባ የሚገልጹት ምንጮች፣ ድርጊቱ አገዛዙን ...
Read More »በፍኖተሰላም በህገወጥ መንገድ የተገደሉ እስረኞችን ቀብር ያጋለጡ አባት ታሰሩ
ኅዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖሰላም ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከታሰሩት መካከል የ2 እስረኞች አስከሬን በድብቅ በሌሊት በቁስቋም ቤተክርስቲያን ሲቀበር የተመለከቱት ሊቀ ጳጳስ መካነ ሰላም፣ ድርጊቱን በመቃወማቸውና ድርጊቱንም ለህዝብ በመንገራቸው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሊቀ ጳጳሱ ለቁስቋም ቤተክርስቲያን ንግስ ከደብረሊባኖስ ገዳም ወደ ፍኖተሰላም መሄዳቸውን የገለጹት ምንጮች፣ በቅዳሴ ሰአት ፖሊሶች ሁለት ...
Read More »