ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደርግ ስርዓት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት እና ጠቅላይ ሚንስርነት ሆነው ያገለገሉት አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ያዴሳ በተወለዱ በ77 ዓመታቸው ህዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በ1932 ዓ.ም በቀድሞው ሸዋ ክ/ሃገር አንቦ ከተማ ውስጥ የተወለዱት አቶ ተስፋየ ፣ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አንቦ በሚገኘው ማዕረገ ሕይወት ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ትምህርት ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ...
Read More »Amsterdam
46 ወታደሮች እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቀሉ
ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት7 የኢትዮጵያ ክፍል ወኪሎች ለኢሳት እንደገለጹት ከረጅም ጊዜ ድርድር በሁዋላ 46 ወታደሮች የተለያዩ መሳሪያዎችን ይዘው ተቀላቅለዋል። ወታደሮቹ ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር ተቀላቅለው በስልጣን ላይ ያለውን ሃይል ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን የግንባሩ የአመራር አባል ገልጸዋል። ወታደሮቹ 9 መትረጊስ፣ 6 ስናይፐር፣ሁለት ዲሽቃና አንድ አርፒጂ መያዛቸውን አመራሩ ተናግረዋል። “ወታደሮቹ ግንባሩን የተቀላቀሉት ኤርትራ ነው ወይ ተብሎ ...
Read More »የዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ በርካታ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች እየተያዙ ነው
ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው። እስሩ እርሳቸው በተያዙ ማግስት የጀመረ ሲሆን፣ እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮምያ ወረዳዎች እንዲሁም በአምቦና አጎራባች ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ሃይቅ ከተማ በርካታ ወጣቶች በአዲሱ ወታደራዊ ...
Read More »በአፍሪካ የቀጭኔ ዝርያዎች እየተመናመኑ በመምጣት ላይ ናቸው ተባለ
ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከፍተኛ ሁኔታ የሕዝብ ብዛት መጨመርን ተከትሎ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሚገኙ የቀጭኔ ዝርያዎች እየተመናመኑ መጣታቸውን ዓለምአቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ኅብረት International Union for the Conservation of Nature (IUCN) አስታወቀ። ድርጅቱ በጥናታዊ ሪፖርቱ እንዳመላከተው በአፍሪካ ውስጥ በእ.ኤ.አ.1985 ቁጥራቸው 155 ሽህ የነበሩ የቀጭኔ ዝርያዎች እ.ኤ.አ በ2015 ዝርያቸው ተመናምኖ ወደ 97 ሽህ ዝቅ ብሏል። ለቀጭኔ ዝርያዎች ...
Read More »በጃኖራ የሚደረገው ውጊያ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል
ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዳባት ወረዳ በጃኖራ ቀበሌ ልዩ ስሙ መንደርጌ በተባለው ቦታ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ዛሬም እንደቀጠለ ሲሆን፣ በጦርነቱ ላይ የሚሳተፉ ተዋጊዮች እንደሚሉት በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው። በአቶ መሳፍንት ተስፉ የሚመራው የነጻነት ሃይሎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ50 በላይ ወታደሮችን መግደሉን የሚገልጹት ተዋጊዮቹ፣ በትናንቱ ጦርነትም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ...
Read More »የጃዊ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ለሁለተኛ ጊዜ በእሳት ተቃጠለ
ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በመገንባት ላይ ያለው እና ከመጠናቀቂያ ጊዜው ለአንድ አመት ያክል የዘገየው የስኳር ፋብሪካ ንብረት የሆነ 60 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቷል። ድርጊቱን ማን እንደፈጸመው በስም ያልጠቀሱዋቸው አካላት እያጣሩት ነው ሲሉ፣ የጠቀሱት የፋብሪካው ሃላፊ አቶ ባይነሳኝ፣ ጥናቱ ሳያልቅ መንስኤውን ይፋ ማድረግ አይቻልም ይላሉ። ሌሎች ወገኖች ደግሞ ድርጊቱ ...
Read More »በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ሊያደርግ ነው
ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በሚል ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2009 ዓም ይካሄዳል። ጥሪውን ያስተላለፈው በአገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሲሆን፣ ዘመዶቻቸው በግፍ የተገደሉባቸውም ሆኑ አገዛዙን የሚቃወሙት ሁሉ በኢምባሲው ተገኝተው ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።
Read More »በሰሜን ጎንደር ውጊያው ቀጥሎአል በርካታ ቤቶችም ተቃጥለዋል
ኅዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር በነጻነት ሃይሎች እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ያልጠበቀው ጉዳት የደረሰበት አገዛዙ የአርሶአደሮችን ቤቶችን በማቃጠል የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው። በወገራ ወረዳ በእንቃሽ ከትናንት በስቲያ ከ10 በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን፣ ዛሬ ማክሰኞ ደግሞ በጃኖራ አቶ መስፍን የተባሉ ታጋይ ሁለት ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ሲሆን፣ ከጠዋት እስካሁን የተኩስ ለውውጥ እየተካሄደ ነው። ...
Read More »በሰሜን ጎንደር በሚደረገው ጦርነት የነጻነት ሃይሎች ድል እንደቀናቸው ተናገሩ
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች ከህወሃት/ኢህአዴግ ጦር ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ድል እየቀናቸው መሆኑን ለኢሳት ተናግረዋል። በውጊያው በመሳተፍ ላይ ካሉት መካከል አንዱ በሰሞኑ ወጊያ መትረጊስ ሳይቀር መማረኩን እና በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ገልጿል። ወኪላችን የሰሞኑን የውጊያ ውሎ በማስመለከት በላከው ሪፖርት አገዛዙ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ነው። በዳባት ወረዳ በአጅሬ ጃኖራ ከህዳር ...
Read More »የወልድያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ
ኅዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2009 ዓም በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን በአል ለማክበር በተጠራ ዝግጅት ላይ “ተማሪዎች በአሉ እኛን አይወክልም” በማለት ከመሰብሰቢያ አዳራሹ በመውጣት በጩኸት ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርስቲ ግቢ በመግባት 37 ተማሪዎችን ይዘው አስረዋል። የአማራ ክልል ተወላጆች “ ወልቃይት ማንነቱ አማራ ነው” የሚሉና ሌሎችንም አገዛዙን የሚያወግዙ ...
Read More »