Amsterdam

የአፋሯ አርቲስትና አክቲቪስት ማፋራ መሀመድ ላሌ ተፈታች

ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ  ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከህዝባዊ አመጹ ጋር በተያያዘ ላለፉት ወራት  ታስራ የቆየችው የአፋሯ አርቲስትና አክቲቪስት ማፋራ መሀመድ ላሌ ከትናትን በስቲያ  ከእስር ተፈታች። በአውሮፓ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ገአስ አህመድ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ከዱብቲ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አስነስተሻል ተብላ ለወራት ለእስር የተዳረገችው አርቲስት ማፋራ  የተፈታችው በዋስ ነው። ፍርድ ቤት በዋስ እንድትፈታ ሲወስን ...

Read More »

የተወሰኑ መምህራን፣ ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት  ከእስር ተለቀቁ

ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ  ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ከመኖሪያ ቤታቸው ከስራ ገበታቸው እንዲሁም ከመንገድ ላይ እየተያዙ ከአንድ ወር በላይ በእስር ሲንገላቱ ከነበሩት ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መካከል የተወሰኑት  ተፈተዋል። የዞን 9 አምደመረብ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ፣ የበይነ መረብ አምደኛው ስዩም ተሾመ፣ ወጣት ብሌን መስፍን፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ሰሎሞን ስዩም፣ መምህር አበበ አካሉ እና ወጣት እያስፔድ ተስፋዬ እና ሌሎችም ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የሚታየው ተቃውሞ ያሰጋው የኢህአዴግ መንግስት ሰራባ ላይ አዲስ ክፍለ ጦር ሊያቋቁም መሆኑ ተሰማ

ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ  ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር የነጻነት ሃይሎች፣ አርሶአደሮችና የታጠቁ ሃይሎች በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመሩን ተከትሎ፣ አገዛዙ ሰራባ ላይ 46ኛ ክፍለ ጦር ለማቋቋምና ሰራባን የጦር መሳልጠኛ ለማድረግ ማሰቡንም ምንጮች ገልጸዋል። ሰራባ የሚገነባው ክፍለጦር፣ አዘዞ ሎዛ ማሪያም ላይ ያለው 24ኛው ክፍለ ጦር ፈርሶ ይሁን ወይም ተጨማሪ አልታወቀም። በዞኑ ወታደራዊ ፍተሻው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ፍተሻው ...

Read More »

የእንግሊዝ ፓርላማ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ረጅም ሰአት የፈጀ ውይይት አደረገ

ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ  ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከየመን በህገወጥ መንገድ ተይዘው ለህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ተላልፈው ከተሰጠቡት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከሰኔ 2፣ 2014 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ትናንት ማክሰኞ በእንግሊዝ ፓርላማ ጉዳያቸው የመወያያ ርእስ ሆኖ  የቀረበ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የፓርላማ አባላት በሙሉ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ላይ አስፈላጊውን ጫና ፈጥሮ አቶ አንዳርጋቸው የሚለቀቁበትን መንገድ ...

Read More »

ወደ የመን የሚሰደዱ ሕገወጥ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ቁጥራቸው እጅግ ጨምሯል ኢትዮጵያውያን በቁጥር ቀድሚያውን ይዘዋል

ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ  ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ ተባባሩት መንግስታት ድርጅት የጥናት ሪፖርት መረጃ መሰረት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2016፣ 107 ሽህ 532  አጠቃላይ ስደተኞች ወደ የመን የገቡ ሲሆን፣  ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ በኋላ ወደ የመን የገቡ ኢትዮጵያዊን ስደተኞች ቁጥር 92 ሽህ 768 ወይም 83 በመቶ የሚሆነውን ይይዛል። ካለፈው መስከረም ወር ወዲህ ብቻ ቁጥራቸው 3 ሽህ 109 የሚሆኑ ...

Read More »

የግብጽ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ንኡስ ኮሚቴ  የሳኡዲ አረቢያ ባለስልጣናት ሰሞኑን በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ዙሪያ ተወያየ።

ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ  ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ- ኢጂፕሺያን ኢንዲፐንደንት እንደዘገበው  ውይይቱ ያተኮረው በሳኡዲና በግብጽ መካከል ቅሬታ በተፈጠረበት በአሁኑ ሰዓት የሳኡዲ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ  ያደረጉት ጉብኝት- በአባይ ላይ እየተሰራ ካለው ግድብ ጋር  ስለመያያዙ ነው። የሳኡዲ ንጉስ አማካሪ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ  ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸው ታውቋል። ይህ የሳኡዲ ባለስልጣናት ጉብኝት ከአባይ ግድብ ጋር ግንኙነት  ይኖረው ይሆን ...

Read More »

በጃዊ የነጻነት ታጋዮች ከአርሶአደሮች ጋር በማበር በመንግስት ወታደሮች ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው አሁንም በውጥረት ላይ ነው

ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ  አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገለጹት ታህሳስ 5 እና 6 በነበረው ሁለተኛ ዙር ተቃውሞ አገዛዙ ሁለት ታንኮችን አስገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ ከህዝብ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቀነስ ሳይችል ቀርቷል። አርሶአደሮችና ታጋዮች ተቃውሞውን ተከትሎ እነሱን ለማጥቃት የሄደውን አንድ ታንክ እንዳቃጠሉ እየተናገሩ ቢሆንም፣ ኢሳት ከራሱ ምንጮች እስካሁን ለማረጋገጥ አልቻለም። የአካባቢው ዘጋቢያችን እና ከዋና ከተማው ራቅ ብሎ በሚገኘው የጃዊ የሸንኮራ ...

Read More »

በኦሮምያ በተለያዩ ቀበሌዎች በተደረጉት ስብሰባዎች የቀበሌ አመራሮች ተቃውሞአቸውን ገለጹ

ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ  አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው “ ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል አጀንዳ ለ5 ተከታታይ ቀናት በተደረገው ስብሰባ  ላይ የቀበሌ አመራሮች ግምገማው ትክክል ያልሆነና የህዝቡን ብሶት ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል። እናንተ ህዝባችንን ትገላላችሁ፣ እኛ ደግሞ አንድ ሰው እስከሚቀር ፣ ህዝባችን ጥያቄውን መጠየቁን አያቆምም። ጥልቅ ተሃድሶ የሚባል ከሆነ ዋናውን ችግር ትታችሁ ትንንሽ ጉዳይ ላይ ማተኮራችሁ ትክክል ...

Read More »

የኦጋዴን ነጻነት ግንባር ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር “እየተዋጋሁ ነው” አለ

ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ  አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ፣ ባለፈው ሃሙስ በኦጋዴን ቃብሪዳህር ወረዳ ዲሞዲሊ መንደር ውስጥ የህወሃት ኢህአዴግ ታጣቂዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ እንደተለመደው  የጅምላ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና እስራት መፈጸማቸውን ተከትሎ ግንባሩ ከተጠቂዎቹ ጎን በመቆም አጸፋዊ ምላሽ መውሰዱን አስታውቋል። በሁለቱ ቡድኖች መሃከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 6 የህወሃት ኢህአዴግ ወታደሮች ተገለው፣  8 መቁሰላቸውን የግንባሩ ወታደራዊ ክንፍ አስታውቋል። በኦጋዴን ግዛት ውስጥ ...

Read More »

ባንዲራ በመሥራታቸው በላሊበላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ግርማ ቅባቴ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ  አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለ11 አመታት በፖሊስነት ያገለገሉት አቶ ግርማ ፣ ከ1987 ዓም ወዲህ ስራቸውን በመልቀቅ በዲዛይነር ስራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል። አቶ ግርማ የኢትዮጵያን ባንዲራ በተለያዩ ዲዛይኖች እየሰሩ መሸጣቸውና ወደ ውጪ መላካቸው ወንጀል ሆኖ ተቆጥሮባቸዋል። ባለፉት ወራት የተከሰተውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የታሰሩት አቶ ግርማ፤ ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት እስከዛሬ ማክሰኞ ድረስ “እኔ ነኝ ያሳሰርኳቸው” የሚል አካል ...

Read More »