Amsterdam

የፉጋ ማህበረሰብ እየተባሉ የሚጠሩት ለመጥፋት ተቃርበዋል ተባለ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል በአላባ ልዩ ዞን የሚገኝው የፉጋ ማህበረሰብ ከፍተኛ ለሆነ መገለል እና መድሎ ተጋላጭ በመሆኑ እና ምንም አይነት ፤ የትምህርት ፣ የጤና ተደራሽነት በማጣቱ ወደ ማህበረሰባዊ በቀል እና ጥላቻ የወለደው አመፅ ሊያመሩ እንደሚችሉ የፌደሬሽን ምክርቤት አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ባስጠናው ጥናት  ኢህአዴግ እስካሁን ድረስ አገዛዙን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ ማህበረሰቡ “የተካደ የተናቀ እና ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ስኮት በርግ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ዜጎች ጋር በጋራ በመቆም ራሳቸውን ለመከላከል እየሞከሩ ነው።

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከደርባን በ76 ኪ/ሜትር ላይ በምትገኘዋ ስኮት በርግ ከተማ በምትገኝ መንደር ውስጥ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 4 ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል፣ 8ቱ ደግሞ ቆስለዋል። 11 ሱቆቻቸውም ተዘርፈውባቸዋል። 1 የደቡብ አፍሪካ ፖሊስም ተገድሏል። አምስት ዘራፊዎችና ነፍሰ ገዳዮች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ ፣ የዋስ መብታቸውን ለማስጠበቅ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ድርጊቱን ለማውገዝና ፍትህ እንዲሰጣቸው ...

Read More »

ቤተ እስራኤላዊያን የሚደርስባቸውን ዘረኝነት በመቃወም ብሄራዊ ወታደራዊ አገልግሎትን ተቃወሙ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ ቤተእስራኤላዊያን በተቋም ደረጃ በእስራኤል ውስጥ የሚደርስባቸውን ዘረኝነትና መገለል በመቃወም ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም ሲሉ ተቃውሞ አደርገዋል። ቤተእስራኤላውያኑ በእስራኤል መንግስት መስሪያቤቶች በወታደራዊ እና ፖሊስ ተቋማት ውስጥ መገለል እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል። እነዚህ 300 ኢትዮእስራኤላዊ አይሁዶች በወታደራዊ አገልግሎት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩ ናቸው።

Read More »

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለ12 አመቱ ታዳጊ ኢትዮጵያዊ አውስትራሊያዊ ደብዳቤ መልስ ሰጠ።

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ12 አመቱ ታዳጊ ኢዮስያስ መላኩ በኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግድያ፣ አፈናና እስራት የአውስትራሊያ መንግስት እንዲያወግዝ እንዲሁም በአገዛዙ ላይ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቅ በድምጽ የተቀረጸ መልእክት ለአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ማልኮም ተርንበል ካስተላለፈ በሁዋላ፣ የጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ደብዳቤውን ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁሊየ ቢሾፕ ማስተላለፉን የሚመለከት ምላሽ ተልኮለታል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ...

Read More »

የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደተዘጋ ነው

ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሁለት ቀናት በፊት  የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ላለመሄድ በመወሰናቸው ዛሬ አርብ፣ ትምህርት ቤቱ ተዘግቶ ውሎአል። ባለፈው ረቡዕ በተደረገው ተቃውሞ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች ከፍተኛ ደብደባ የተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ዛሬ ትምህርት ይጀምራሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀርቷል። ከአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ...

Read More »

አርበኛ መቶ አለቃ ደጀኔ በተኩስ ልውውጥ መሃል መሰዋቱ ታወቀ

ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታህሳስ 12 ቀን 2009 ዓም በነጻነት ሃይሎች እና በህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች መካከል ቋራ ላይ ተደርጎ በነበረው ከባድ ውጊያ ከመንግስት በኩል ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ወታደሮች ሲገደሉ፣ ከነጻነት ሃይሎች መካካል ደግሞ መቶ አለቃ ደጀኔ መንግስቱ መስዋት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አርበኞቹ እንደሚሉት  መቶ አለቃ ደጀኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጣውን ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ አስመልሳለሁ በሚል ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥር ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ የሃመር ወጣቶች ‹‹ከዱር አራዊት በታች መታየት የለብንም›› በማለት የጀመሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ አሁንም መፍትሄ ባለማግኘቱ ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በአስቸኳይ አዋጅ ስም ጥያቄውን ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ህዝቡን ለበለጠ አለመረጋጋት መዳረጉን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። “ተቃውሞው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰራተኞች ፣ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ አባላት ተገድለዋል። ...

Read More »

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የመነሻ ሃሳብ እንዲቀርብላቸው ጠየቁ

ታኅሣሥ ፲፬ (አሥራ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ ስርዓቱን አደጋ ውስጥ መጣሉን የተረዳው ኢህአዴግ፣ መነጠኛ የህገ መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እንዲቀርብለት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኩል ትእዛዝ አስተላልፏል። ጥናቱ በሁለት ወራት ውስጥ ተጠናቆ እንዲቀርብ ያዛል። ክልሎቹን ህገመንግስቱን ለማሻሻል የሚያስችል አቅም ያላቸው አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አመራሮች ምርጫ አካሂደው እንዲያሳውቁ ታዘዋል። የሚሻሻሉት ህጎች የትኞቹ እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ...

Read More »

በአምቦ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተማዋ ለሁለተኛ ቀን ውጥረት ሰፍኖባት ዋለ

ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ  ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትናንት ትምህርት በማቆም በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እንዲፈቱ እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ጉዳት ያደረሱት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲጠይቁ ከዋሉ በሁዋላ፣ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ግቢው በመግባት በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመዋል። በርካታ ተማሪዎችንም ይዘው አስረዋል። ዛሬ ሃሙስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ወታደር ወደ ከተማዋ በማምራት ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ከቦ ያረፈደ ...

Read More »

አቶ ሃይለማርያም በደቡብ ኦሞ ባደረጉት ጉብኝት የዞኑ ፖሊሶች እንዳይገኙ ተደረገ

ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ  ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ  – ታህሳስ 9/2009 ዓ.ም አቶ  ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ፕሬዝዳንትና  ከደህዲን አመራር አባላት ጋር በደቡብ ኦሞ የሚገኙትን  የኩራዝ አንድና ሁለት የስኳር ፕሮጀክትና የጂንካን ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ መጎብኘታቸውንና በዚያው ቀን  ተመልሰው አዲስ አበባ መሄዳቸውን የገለጹት ምንጮች፣ በዚህ ጉብኝታቸው የዞኑ ፖሊሶች እንዳይገኙ ተደርጓል። የአቶ ሃይለማርያም ጉብኝት በከፍተኛ ሚስጢር ተይዞ እንደነበርና ከደህንነቶች ...

Read More »