ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ በርካታ የነዳጅ ማደያዎች የቤንዚንና ናፍጣ እጥረት መታየቱን ወኪላችን ዘግቧል፡፡ ወጣ ገባ በሚል ሁኔታ ሲከሰት የቆየው የነዳጅ አቅርቦት ከያዝነው ወር መጀመሪያ አንስቶ ከዕለት ወደ ዕለት እጥረቱ እየተባባሰ መሄዱን አሽከርካሪዎች ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡ ከአሁን በፊት የነዳጅ እጥረት የሚከሰተው በወሩ መጨረሻ ከታሪፍ ጋር በተያያዘ መልኩ የገቢዎች ሰራተኞች ከማደያ ባለንብረቶች ጋር ...
Read More »Amsterdam
በአዲስ አበባ ቤታቸው ይፈርስባቸዋል የተባሉት ነዋሪዎች ለመስተዳድሩ ማስጠንቀቂያ ሰጡ
ታኅሣሥ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ መስተዳደር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በወረዳ 9፣ 10፣ 11፣ 12 እና 13 የሚገኙ ቤቶችን ለማፍረስ ማስታወቂያ ካወጣ በሁዋላ፣ በወረዳ 10 እሁድ ህዝቡ ለስብሰባ የተጠራ ሲሆን፣ በከፍተኛ የቁጣ ስሜት ውስጥ የነበረው ህዝብ “ እኛ የእናንተን ውሸት መስማት ሰልችቶናል፣ በቃችሁን፣ ቤታችንን አታፈርሱትም፣ ደጃፋችን ላይ እንሞታለን፣ ሂዱልን” በማለት ስብሰባው እንዲበተን ተደርጓል። ህዝቡም መስተዳድሩ ...
Read More »የአማራ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ከስልጣን ተነሱ
ታኅሣሥ ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በክልሉ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ደሴ አሰሜ ከሃላፊነት ተነስተው እንዲንሳፈፉ ተደርጓል። ለአገዛዙ ታማኝ ናቸው የሚባሉት አቶ ደሴ፣ እንደሌሎች ከሃላፊነት እንደተነሱት ሰዎች ወደ እስር ቤት ባይወሰዱም፣ በአሁኑ ሰአት ከስልጣን ተነስተው ያለስራ ተቀምጠዋል። በክልሉ ውስጥ በተለይም የሙስሊም አትዮጵያውያን እንቅስቃሴ ...
Read More »በኬንያ ናይሮቢ ስደት ላይ የነበረ ኢትዮጵያዊ ታፍኖ መወሰዱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ
ታኅሣሥ ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮቻችን የላኩት መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርብ ጊዜ ከኢትዮጵያ የመጣውና ላለፉት ሶስት ወራት በናይሮቢ በስደተኝነት የቆየው ስደተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ ሲሆን ፤ ምናልባትም ከፍ ያለ ማእረግ ሳይኖረው እንዳልቀረ ጠቁመዋል። ይህ የመንግስት ሰው የነበረውና በቅርቡ ከሀገር ቤት ከድቶ የመጣው ስደተኛ ትናንት በናይሮቢ ዲዶራይ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሳለ የኢትዮጵያ ደህንነቶች በፓትሮል በመምጣት አፍነው እንደወሰዱት ምንጮቹ ...
Read More »በሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ ወጣቶች በግዳጅ ተመልምለው ወታደራዊ ስልጣና እየወሰዱ ነው
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የትውልድ ቦታ በሆነው በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ በሚገኙ 17 ቀበሌዎች የሚገኙ ወጣቶች፣ በጎንደር በኩል ወራሪ ጠላት መጥቷል በሚል እየተያዙ በግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወጣቶቹ ከሌሊቱ 8 እና 9 ሰአት ላይ እየታፈሱ በግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ በተደረገው 5 ዙር ስልጠና ከ300 ...
Read More »ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ወንጀል ሊከሰሱ ነው።
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር በብራሰልስ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ ለስብሰባ መጥተው ሲመለሱ ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ሊከሰሱ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ፕሮፌሰር መረራ ከሁለት ሳምንታት በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ የተመለሱ ሲሆን፤ መርማሪዎች የኢሜይልና የፌስቡክ አካውንታቸውን አስገድደው በመውሰድ በሽብርተኝነት ሊያስከሣቸው ይችላሉ ብለው የሚያሥቧቸውን መረጃዎች እያሰባሰቡ ...
Read More »በደቡብ ኦሞ ዞን ያንዣበበው የረሃብ አደጋ አሳሳቢ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ቆላማ የአርብቶ አደር አካባቢዎች በተለይም በሃመር፣ ኛንጋቶምና ዳሰነች እንዲሁም ሳላማጎ ወረዳዎች የረሃብ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ዓለም አቀፍ ተቋማት ድምጻቸውን ማሰማት ከጀመሩ የቆዩ ቢሆንም፣ ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ ረሃብ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የግብርና ባለሙያዎች ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ረሃቡ ቅድመ ግምት በተሰጣቸው ቆላማ ወረዳዎች ሳይወሰን ወደ ወይና ደጋና ደጋ አርሶአደር ...
Read More »በአዲስ አበባ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ሊፈርሱ ነው
ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ በሚከለሰው ማስተር ፕላን ስም በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ አዲስ ዘመቻ ሊጀመር መሆኑን መስተዳድሩ አስታውቋል።በዚህ ዘመቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለምንም ተተኪ ቤቶች ይፈናቀላሉ። እንዲፈርሱ ትእዛዝ የተላለፈባቸው አካባቢዎች ፈረንሳይ፣ ካራ፣ የካ፣ አባዶ፣ ወሰን፣ ምኒሊክ፣ ኮተቤ፣ ሲኤምሲ፣ ቦሌ እና የካን የሚያዋስነው መስመር፣ መገናኛ፣ አዲስ አበባን ከኦሮሚያ ...
Read More »ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ የደህንነት ሰራተኞች ደሞዝ በብር ተከፈለ
ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የውጭ ደህንነት ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ ደሞዛቸው በብር እንዲከፈላቸው ተደርጓል። እስካሁን ድረስ ደሞዝ ይከፈለው የነበረው በአሜሪካን ዶላር ቢሆንም፣ በዚህ ወር ግን ዶላር የለም በሚል ምክንያት በብር እንዲከፈለን ተደርጓል ሲሉ ለኢሳት ተናግረዋል። በጎረቤት አገራት በደህንነት መረጃ ማሰባሰብ ስራ ላይ ከተሰማሩት የደህንነት ሰራተኞች መካከል ብዙዎቹ ከብሄራቸው ጋር በተያያዘ ከሚፈጸምባቸው ...
Read More »የደቡብ ኦሞ ዞን ም/ል አስተዳዳሪ አምጸው ጫካ መግባታቸው ተሰማ
ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደኢህዲን/ኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬና የዞኑ ም/አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሥጦታው ጋርሾ ከገዢው ፓርቲና መንግስት ጋር የፈጠሩትን ቅራኔ ተከትሎ በትውልድ አካባቢያቸው በና-ጸማይ ወረዳ ውስጥ ወጣቶችን አስከትለው መሸፈታቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሥጦታው ጋርሾ ከዞኑ የደህንነት ቢሮና አስተዳደር ጋር በተፈጠረ ቅራኔ ‹ተገምግመው › በተለያዩ የሙስ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ወህኒ ወርደው ከተፈቱ በኋላ ወደ ትውልድ ...
Read More »