ጥር ፲፮ ( አሥራ ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የቀጠለው ግጭት አሳስቦኛል ያለው ድርጅቱ፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ቦታዎች የሰብአዊ እርዳታ ሊደርስ እንዳልቻለ ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት በዝግ ባደረገው ምክክር ተጨማሪ ሃይል ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲላክ መወሰኑን የድርጅቱ የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ስዊድናዊው ኦሎፍ ስኮግ ተናግረዋል። ሰኮግ የደቡብ ሱዳን መንግስት ከጸጥታው ምክርቤት ጋር እንዲተባበርና የድርጅቱ የሰላም አስከባሪ ሃይል ...
Read More »Amsterdam
የሰራዊት ምልመላ በደላሎች መካሄድ ጀመረ
ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላ አገሪቱ የሚወጡ አዳዲስ የመከላከያ ሰራዊት የቅጥር ማስታወቂያዎች በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት በማጣታቸው ገዢው ፓርቲ አዳዲስ ስልቶችን እየተጠቀመ ነው። ቀደም ብሎ በየቀበሌዎች የሚጣለው ኮታ ውጤት ባለማምጣቱ አሁን ደግሞ በደላሎች አማካኝት ቅጥር ለመፈጸም ሙከራ እየተደረገ ነው። በመከላከያ ብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር የሚታደደረው የቢሸፍቶ አውቶሞቲቭ ሰሞኑን የወታደሮች ቅጥር ማስታወቂያ ቢያወጣም፣ የሚመዘገብ ሰው ...
Read More »በሶማሊላንድ የአማራና ኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ተያዙ
ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከ250 ያላነሱ የአማራ እና ኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በሶማሊላንድ ፖሊሶች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ከእስሩ ጀርባ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት እጅ እንዳለበት ታውቋል። የኦነግ እና የአርበኞች ግንቦት7 ወኪሎች በሶማሊላንድ መኖራቸውን መረጃ ደርሶናል በሚል የህወሃት/ኢህአዴግ የደህንነት አባላት ከሶማሊላንድ የጸጥታ አባላት ጋር በመሆን የተያዙት ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፉ እየጣሩ ነው። ብዙዎቹ የተባበሩት መንግስታት ...
Read More »አዲስአበባ ሌላ አወዛጋቢ ማስተር ፕላን ልታጸድቅ ነው
ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ እና ፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንደሚሆን ዝግጅት መኖሩን በመቃወም ሕዝባዊ ቁጣ ከተቀሰቀሰ በኋላ የተከለሰው የአዲስአበባ ማስተር ፕላን ላይ በየደረጃው ያሉ አካላት እየተወያዩበት ሲሆን የአዲስአበባ ከተማ ነዋሪዎችም ያሳተፉ ውይይት ለማካሄድ መታቀዱ ተሰምቷል፡፡ በአዲስአበባ እስካሁን ዘጠኝ ማስተር ፕላኖች ተዘጋጅተው ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን፣ የመጨረሻውና ዘጠነኛው ማስተር ፕላን የአገልገሎት ጊዜውን ...
Read More »አንድ ወጣት አንድ የሚሊሺያ አዛዥ ገድሎ ተሰወረ
ጥር ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሰሜን ጎንደር ዞን በአጅሬ ጃኖራ አወቀ ካሴ የተባለ ወጣት ከአርበኛ ማሳፍንት ጋር በተያያዘ ታስሮ ስቃይ ሲደርስበት ከቆየ በሁዋላ፣ ወደ ዋና ከተማው ዳባት ሲመጡት “ ድልድልዬ” ከተባለ ቦታ ላይ፣ ኮማንደር መሰለ ጥጋቡ የሚባለውን ሚሊሺያ መሳሪያ በመቀማት እና በ3 ጥይቶች በመግደል የራሱንና የአባቱን መሳሪያ ይዞ በማምለጥ የነጻነት ሃይሎችን ...
Read More »በአዲስአበባ ክፍለከተሞች በደንብ አስከባሪ ስም በርካታ ቁጥር ያላቸውን በህዝቡ ውስጥ የጸጥታ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ የሚያከናውኑ ወጣቶችን መመልመል ተጀመረ፡፡
ጥር ፲፪ ( አሥራ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለስራ መደቡ በመስፈርትነት የተቀመጠው ዕድሜ ከ18 ዓመት ያላነሰ ከ30 ዓመት ያልበለጠ ሆኖ የስነምግባር ችግር እንደሌለበት ከሚኖርበት ወረዳ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ወይንም ቀድሞ ከሚሰራበት ድርጅት በስነምግባር ችግር ያልተቀነሰ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች በእኩልነት ማገልገል የሚችል እንዲሁም በቀድሞ የሁለተኛ ደረጃ ያጠናቀቁ ወይንም በአዲሱ ካሪኩለም 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ የሚል ይገኝበታል። ምልመላውን ለማከናወን በየወረዳው ኮሚቴ ...
Read More »ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበውን የባለስልጣናት ሃብት ይፋ ማድረግ አልቻለም
ጥር ፲፪ ( አሥራ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብአዴን አንጋፋ አባሉ አቶ ዓሊ ሱሌይማን የሚመራው የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የባለሥልጣናትን ሐብት መመዝገብ ከጀመረ ሰባት ዓመታት ቢያስቆጥርም እስካሁን የምዝገባ መረጃውን ለህዝብ እና ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑ እያነጋገረ ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን አንዳንዶቹ በስም በመጥቀስ የባለስልጣናቱ የሐብት ምዝገባ መረጃ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፣ ኮምሽኑ የተለያዩ ምክንያቶችን ...
Read More »በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ወጣቶች እንዲሰጥ የተዘጋጁ ሸዶች ለባለሃብት መሰጠታቸው ቅሬታ ፈጠረ፡፡
ጥር ፲፪ ( አሥራ ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ውስጥ ተገንብተው ለረዥም ጊዜ ያለ አገልግሎት ተቀምጠው የነበሩ ከ60 በላይ ሸዶች ለተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶች እንዲሰጥ ቢወሰንም፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ጽህፈት ቤት ግን ሸዶችን ለባለሃብቶች በማከፋፈሉ ስርዓቱን ጠብቀው የተደራጁ ወጣቶች ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለክልሉ ዘጋቢ ተናገሩ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚናገሩት በ2008 እና ...
Read More »የጥምቀት በአል በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥርና በቀዘቀዘ ስሜት ተከበረ
ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዘንድሮውን የጥምቀት በአል ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለውን ቅሬታ የገለጸበት ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥበቃ ሲያደርጉ ታይተዋል። በሰሜን ጎንደር በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የጸጥታ ቁጥጥሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠብቆ ታይቷል። በጎንደር የበአሉ ስነስርዓት ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆና በመተማ የተለያዩ የቦንብ ፍንዳታዎች ደረሱ
ጥር ፲፩ ( አሥራ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት እና ዛሬ በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ በተባለው ቦታ ሁለት የእጅ ቦንቦች የፈነዱ ሲሆን፣ ነጋዴ ባህር በተባለ ቦታ ላይም ተመሳሳይ ቦንብ ፈንድቷል። ይህን ተከትሎም አካባቢው በወታደሮች የተከበበ ሲሆን፣ በርካታ ወጣቶችም ታፍሰዋል። ከትናንት ጀምሮ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ጥቃቱ በነጻነት ሃይሎች መፈጸሙን ከመግለጽ ውጭ በዝርዝር ጥቃቱን ...
Read More »