ጥር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን የተገነባው የጎጃም ጎንደር አባይ ድልድይ ከዛሬ ጠዋት 4:00 ሰዓት ጀምሮ በቆርቆሮ ተዘግቶ አገልገሎት መስጠት አቁሟል ፡፡ ከጎንደር እና ከጎጃም የሚመጡ መሻገር የግድ የሆነባቸው ተሽከርካሪዎች በሶስት ረድፍ ተሰልፈው በአማራ ልዩ ኃይል ፈቃድ አልፎ አልፎ በድልድዩ አንድ መስመር ብቻ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ እየተደረገ ሲሆን፣ ህዝቡ በከፍተኛ ምሬት በእግሩ እየተጓዘ ነው። በእድሜ የገፉ ...
Read More »Amsterdam
በበለሳ የህወሃት/ኢህአዴግ ሰራዊት በታጋዮች ላይ ያደረገው ከበባ ተሰበረ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አርባያ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የነጻነት ታጋዮችን በአንድነት በማሰባሰብ የትግል ምክክር ለማድረግ የተጠራውን ስብሰባ ለመክበብ ሙከራ ያደረገው የህወሃት/ኢህአዴግ ሰራዊት፣ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት መበታተኑን ታጋዮች ተናገሩ። በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የነጻነት ታጋይ ቴዎድሮስ እንደገለጸው፣በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በጋራ በሚወጣ የትግል ስትራቴጂ አገዛዙን ለመግጠም ምክክር ለማድረግ በተጠራ ስብሰባ ላይ ህወሃት መራሹ አገዛዝ፣ አስቀድሞ ...
Read More »አውስኮድ እንደ ህብር ስኳር ሁሉ በሜቴክ መዘረፉን ሰራተኞች ተናገሩ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰራተኞች እንደገለጹት የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት /አውስኮድ/ከ2002 ዓ/ም ህዳር ወር ጀምሮ የጣና በለስን የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ለመስራት ከፌዴራል መንግሥት የ6 ቢልየን ብር የግንባታ ስራ ውል ተሠጥቶት ሠራተኞች በሁለት ፈረቃ ቀንና ሌሊት በማሰራት የቦይ ሥራ ስርቶ አስረክቧል። የሸንኮራ አገዳው ዝግጁ እንዲሆን ቢደረግም፣ ፋብሪካውን እገነባለሁ ብሎ ኮንትራት የወሰደው በሜ/ር ጄኔራል ክንፈ ...
Read More »በአርባምንጭ ከተማ የስፖርት ሜዳ ላይ የተቃውሞ ወረቀት ተበተነ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት በአርባምንጭ ከተማ ኳስ ጨዋታ ለመመልከት ወደ ሜዳ የገቡ ሰዎች የአርባ ምንጭ ወጣቶች ለመከላከያ ሰራዊት እንዳይመለመሉ የሚመክር እንዲሁም ወጣቶች ለመብታቸው እንዲነሱ የሚጠይቅ ወረቀት ተበትኖ ማግኘታቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። በራሪ ወረቀቱ “የአገር መከላከያ ሰራዊት ምልመላ ለአገር ድንበር ጥበቃ ወይስ እናትና አባትን መግደያ?” የሚል ርእስ ያለው ሲሆን፣ መላው የአገራችን ህዝቦች በወያኔ ኢህአዴግ የከፋፍሎ መግዛት ...
Read More »የሸጎሌ ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ማግኘት ካቆሙ 3 ወራት እንዳለፋቸው ተናገሩ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ ሸጎሌ ኪዳነ ምህረት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ዉሃ ከተቋረጠ ሶስት ወራት ማለፉን ተናገሩ። ወትሮም ቢሆን በ15 ቀናት ዉስጥ አንድ ሌሊት አሳቻ ሰዓት ጠብቆ የሚለቀቀው ውሃ ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። በአካባቢው የሚኖሩ ህጻናትና አቅመ ደካሞች ከውሃ ጋር በተያያዘ ለሚመጡ በሽታዎች ...
Read More »ኮማንደር ዋኘው አዘዘው መንግስትን በመክዳት ወንጀል ተከሰሰ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰሜን ጎንደር ዞን የጸረሽምቅ ግብረሃይል አዛዥ የሆነው ኮማንደር ዋኘው አዘዘው ከወራት እስር በሁዋላ መንግስትን በመክዳት ወንጀል መከሰሱ ታውቋል። ኮማንደር ዋኘው በጎንደር በነበረው ህዝባዊ አመጽ ፓርቲውንና መንግስትን በመክዳት ከህዝብ ጋር በመሆን በመንግስት ላይ የተነሳውን አመጽ ለማስቆም ባለመቻሉ፣ መንግስትንና ፓርቲውን ከድቷል የሚል ክስ ቀርቦበታል። በተለያዩ የሰሜን ጎንደር አካባቢዎች በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ...
Read More »ለመለስ ዜናዊ ፓርክ በተመደበው በጀት ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈጸመ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ መስተዳድር የጉለሌ እጽዋት ማእከል በሚል ሲጠራ የነበረውና በቅርቡ የመለስ ዜናዊ ፓርክ ተብሎ የተሰየመው እንጦጦ ላይ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት የታጠረው ጥብቅ የደን ተቋም በያዝነው አመት 200 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ ሂሳብ ፣ ለኦዲት ምቹ ያልሆነ ነው በሚል ባክኖ መቅረቱን ምንጮች ገልጸዋል። ለፓርኩ ዝግጅት የወጣ ወጪ ቢኖርም አብዛኛው ወጪ ህጋዊ ደረሰኝ ...
Read More »በአማራ ክልል ከሚገኙ ሆስፒታሎች የቀዶ ጥገና ህክምና መስጠት የሚችሉት ከ7 አይበልጡም ተባለ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ 55 ሆስፒታሎች ቢኖሩም የቀዶ ህክምና የሚሰጡት ሰባቱ ሪፈራል ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው።እነዚህም በአግባቡ መስጠት የሚያስችል አቅም የላቸውም::ሆስፒታሎች በጣም አነስተኛ ከመሆናቸው ጋር ታካሚዎች ህክምናውን ለማግኘት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለተለያዩ ወጪዎች ይጋለጣሉ። ሁሉም ሆስፒታሎች ከፍተኛ የባለሙያ እና የቁሳቁስ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ገዢው ፓርቲ በጤናው መስክ የሚሊኒየሙን የልማት እቅድ አሳክቻለሁ ቢልም፣በአገሪቱ በሚገኙ የጤና ተቋማት ከፍተኛ የሆነ ...
Read More »የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ መጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እፎይታን ሰጠ።
ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ አገራት 28ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ የኅብረቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ሰሞኑን ሲካሄድ ሰንብቷል። ከስብሰባው መቃረቢያ ሰሞን ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ የከተማ ነዋሪዎች በፀጥታ ሃይሎች ከመጠን ያለፈ ቁጥጥር ምክንያት የሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ለከፍተኛ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች ተዳርገዋል። በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች አቅራቢያ ...
Read More »በደሴ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ስብሰባ የጸጥታ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ሆኖ ቀረበ
ጥር ፳፭ (ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢህአዴግ አባላት እየተሳተፉበት ባለው ስብሰባ የጸጥታ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል። በተለያዩ መድረኮች በተደረጉት ስብሰባዎች ላይ በክልሉ የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ በአባላት ዘንድ ተደጋግሞ የቀረበ ጥያቄ ነበር። በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ጥሩ እንደሆነ ገለጻ የሰጡት የመድረኩ መሪዎች፣ ይህንን እንዲያረጋግጡ ከወልቃይት፣ አርማጭሆ እና ቋራ ...
Read More »