የካቲት ፰ ( ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመን እና ጅቡቲ አገራቸውን ትተው በህገወጥ መንገድ በሚፈልሱ ስደተኞች መጨናነቃቸውን እና ሰብዓዊ ቀውስ መፈጠሩን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ። በእርስበርስ ጦርነት ወደምትታመሰው የመን እና ጅቡቲ በየወሩ ቁጥራቸው ከ10 ሽህ በላይ ስደተኞች በበረሃና በባሕር አቆራርጠው ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው የሚገቡ ሲሆን አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ወደ የመን ከሚገቡት ስደተኞቹ ውስጥ 30 ...
Read More »Amsterdam
ከልማት ባንክ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ዝርፊያ የምርመራ ሂደት ቀጥሎአል
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መላኩ ፋንታ ከእስር ቤት ተጠርተው ተጠይቀዋል፤ የባንኩ ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩ መጥሪያ ደርሷቸዋል፤ የህወሃት መካላከያ አባላት ሰነድ አጥፍተዋል፤ ከአገር የወጡም አሉ። የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን የሰሩትና የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ መሬት ዝርፊያ ጋር ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ ከ20 ያላነሱ የልዩ ሃይል አባላት በደፈጣ ውጊያ መገደላቸው ታወቀ
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመሩት የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በጉርሱምና ቦምባሴ አካባቢ ያደረጉትን ወረራ ተከትሎ ፣ በደፈጣ ውጊያ ከ20 ያለነሱ የልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውን የደህንነት ምንጮች ገለጹ። እርምጃውን የወሰዱት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሲሆኑ፣ 12 የጦር መሳሪያዎችን እና በአማካኝ እስከ 44 የሚደርሱ ካርታ ጥይቶች ተወስደዋል። የሶማሊ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በ7 የኦሮምያ ...
Read More »በጅጅጋ በመከላከያ በአል ላይ የአየር ላይ ትርኢት ለማሳየት የነበረው እቅድ ተሰረዘ
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጅጅጋ በተከበረው የመከላከያ ቀን ላይ በአየር ሃይል ሄሊኮፕተሮች የአየር የበረራ ትርኢት ለማሳየት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በአብራሪዎች ችሎታና የአይሮፕላኖች ቴክኒካዊ ብቃት ጉድለት ምክንያት እንደታሰበው ሳኪያሄድ ቀርቷል። በአሉ አስቀድሞ በደብረዘይት ከተማ በሚገኘው የአየር ሃይል ዋና አዛዠ በሆነዉ ሰፈር ለማክበር ታስቦ የነበር ሲሆን፣ ዘግይቶ በመጣ ትዕዛዝ በዓሉ በጂጂጋ እንዲከበር መወሰኑን የመከላከያ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ...
Read More »በአማራ ክልል ህዝቡ በደን ኢንተርፕራይዝ ላይ ተቃውሞ ማሰማቱን ተከትሎ ድርጅቱ ሊዘጋ ነው
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ደን ኢንተራፕራይዝ በህዝብ ተቀባይነት ማግኘት ባለመቻሉ እና በኪሳራ ውስጥ በመግባቱ የክልሉ መንግስት በክልሉ 14 ቦታዎች ካቋቋመ በኋላ ሊዘጋው እንደሆነ ታውቋል፡፡ በርካታ አነስተኛ የጣውላ ማሽኖችን ከአንዶነዥያ በማስመጣት ወጣቶችን የስራ ዕድል በመንጠቅ እና ግዙፍ ደኖችን በማውደም በርካታ ጣውላዎች ማምረት ቢችልም ፣ ላለፉት አምስት አመታት ያመረታቸው ጣውላዎች አገልግሎት ላይ መዋል ባለመቻላቸው ለብልሽት ...
Read More »በኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ አስታወቀ::
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሚያካሂደው 34ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈፀሙትን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶት አትኩሮት በመስጠት እንዲያወግዝ ሲል የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ ጥሪውን አቅርቧል። በኢትዮጵያ የአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ በተለይ በወጣት የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ግድያ፣ እስራት፣ ከአገር ማሳደድ፣ አካላዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የተለያዩ ...
Read More »የግልገል ጊቤ ሦስት ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ላይ አደጋ ጋርጧል ተባለ
የካቲት ፯ ( ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የገነባችውን ግድብና እያካሄደች ያለውን ልማት ተከትሎ የኬንያ ቱርካና ሀይቅ የውሃ መጠን መቀነሱ በግማሽ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ህይወት ላይ አደጋ መጋረጡት ዓለማቀፉ የስብ አዊመብት ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ በዩናይትድ ስቴትስ የእርሻ ዲፓርትመንት ለሕዝብ ክፍት የሆኑ የዳታ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ...
Read More »ነዋሪዎች በላያቸው ላይ ቤቶች እንደፈረሱባቸው ተናገሩ።
የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሰኞ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አፍራሽ ግብረሃይል ከ500 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን አፍርሷል። ታዛቢዎች እንደሚናገሩት አፍራሽ ግብረሃይሉ በድንገት በመሄድ በወሰደው እርምጃ 2 ከወለዱ ሳምንት ባልሞላቸው እናቶች ላይ ቤታቸውን በላያቸው ላይ አፍርሰዋል። እርጉዞች ፣ ህናጻትና አሮጊቶች በተወሰደው እርምጃ ሲያነቡ አርፍደዋል። እቃቸውን እንኳ በወጉ እንዳያወጡ በመደረጋቸው ብዙዎች ለአመታት ደክመው የገዙዋቸውን እቃዎች ሳይቀር ...
Read More »በስልጣን ላይ ያሉ ተሿሚ አመራሮች ምንም ዓይነት የፖለቲካ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው ሲሉ አሰልጣኞች ተናገሩ፡፡
የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች በጥልቅ ተሃድሶ በመሰልጠን ሀገሪቱ ከወደቀችበት አዘቅት ነጻ ያወጣሉ ተብሎ የታመነባቸው አመራሮች ምንም ዓይነት የፖለቲካ ዕውቀት የሌላቸው መሆኑን አንድ አሰልጣኝ በተለይ ለኢሳት ተናገሩ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት አመራሮችን በማሰልጠን የተሳተፉት ግለሰብ እንደተናገሩት አመራሮች ለስልጠና ከመግባታቸው በፊት በተሰጣቸው የሀገሪቱን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በሚዳስሰው የመግቢያ ፈተና አብዛኛው ሰልጣኝ የግንዛቤ ችግር አለበት። በአሁኑ ሰዓት ...
Read More »አለማቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ እጁን በፍጥነት አለመዘርጋቱ ጭንቀት ፈጥሯል
የካቲት ፮ ( ስድስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ወር መጀመሪያ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ጭምር በአባልነት የሚገኙበት የድርቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኮምቴ ለቀጣዩ አንድ ዓመት ለድርቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ይፋ ቢያደርግም የዓለም አቀፉ ማህበረሰቡ ምላሽ እጅግ የተቀዛቀዘ መሆኑ አገዛዙን አሳስቦታል። ከብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ወቅት የመኽር ዝናብ ማለትም በያዝነው ዓመት ከጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት እስከ ታህሳስ ...
Read More »