Amsterdam

ገዥው ፓርቲ በፈጠረው ጫና ላለፉት አስር ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን ስርጪት ዳግም ተጀመረ።

የካቲት ፲፭ ( አሥራ አምስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ሀሳቦችን እንዳይሰማ ካለው ሥጋት በመነሳት እንደተለመደው ሁሉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሠስ የኢሳት ቴሌቪዥን ከአየር ላይ እንዲወርድ አድርጎ ቢሰነብትም ኢሳት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዳግም ወደ አየር ተመልሷል። ቀደም ሲል ኢሳትን ሲከታትተሉ የነበሩ አድማጮች የዲሽ ሰሀን አቅጣጫ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በፍሪኩዌንሲ Tel Star 12 Frequency 12738 Horizontal ...

Read More »

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተፈናቀሉት የኦሮሞ አርሶአደሮች ውስጥ 70 በመቶው ከመፈናቀላቸው በፊት ከነበረው በባሰ የኑሮ ጉስቁልና ውስጥ እንደሚገኙ ታወቀ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የአዲስ አበባ መስተዳድር ባስጠናው ጥናት በአዲስ አበባና ዙሪያ ከተሞች ከተፈናቀሉ የኦሮሞ አርሶደሮች መካከል በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባሉት 6 በመቶ ብቻ ሲሆኑ፣ 70 በመቶ ያህሉ ግን ከመፈናቀላቸው በፊት ከነበራቸው የኑሮ ደረጃ ባሽቆለቆለ ኑሮ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። በኦሮምያ ለተነሳው ተቃውሞ መነሻ ከነበሩት ምክንያቶች መካከል ...

Read More »

በጎንደር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን “እናንሳው አናንሳው” በሚል የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ሙከራ ቢደርገም የህዝቡ መልስ ባለስልጣኖችን አስደንግጧል

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በተለያዩ የጎንደር ቀበሌዎች በተካሄዱ የህዝብ ስብሰባዎች፣ የአገዛዙ ካድሬዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳት በኩል የህዝቡ አስተያየት ምንድነው በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ህዝቡ ግን በቀጥታ ከመናገር ይልቅ በጽሁፍ ፣ “ እናንትን አንቀበላችሁም፣ አናውቃችሁም፣ ከህዝብ ውጭ ሆናችሁዋል” የሚል መልስ በብዛት መስጠቱ ካድሬዎችን አስደንግጧል። አንዳንድ ሰዎች “ አዋጁን ስታውጁ እኛን አላማከራችሁንም፣ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በረሃብ ለተጠቁ ኢትዮጵያኖች 8.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አፋጣኝ እርዳታ ለገሰ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እርዳታው በምስራቅ እና ደቡባዊ ኢትዮጵያ በድርቅ ተጎጂ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ይውላል ተብሏል። ከ 5.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ውስጥ 785 ሽህ የሚሆኑት ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡ መሆናቸውን ተመድ በሪፖርቱ ጠቅሷል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ አስተባባሪ ኮሚቴ ሃላፊ ስቴፋን ኦብሪን ፣ በድርቁ ምክንያት በተለይ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ለከፍተኛ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሰማአታት ሃውልት ላይ የህወሃት አርማ መተከሉ ትችት አስከተለ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፋሽሽት ኢጣሊያ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊያን የሚታሰቡበት የካቲት 12 ቀን በተቀዛቀዘ ሁኔታ እንዲከበር ከመደረጉም በላይ በሃውልቱ መታሰቢያ ላይ የህወሃት አርማ እንዲውለበለብ መደረጉ የከተማዋን ነዋሪዎች በእጅጉ አበሳጭቷል። በድርጊቱ የተበሳጩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፣ “ድርጊቱ ነውር ነው” በማለት አስተያየታቸውን እየሰጡ ሲሆን፣ “ህወሃት ሆን ብሎ የጀግኖችን ሰማአታት ቀን ከራሱ ታጋዮች ጋር እኩል ለማድረግ ያደረገው ...

Read More »

ለደቡብ ሱዳን ሰላም መስፈን ከጎረቤት አገራት ውጭ ያሉ አገሮች ሙከራ ማድረግ እንዳለባቸው የአሜሪካው አምባሳደር ተናገሩ

የካቲት ፲፬ ( አሥራ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ ልዑክ የሆኑት አምባሳደር ዶናል ቡዝ በለንደን ሻተም ሃውስ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአካባቢው አገራት የራሳችውን ጥቅም ለማስከበር ሲሉ የደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት እያወሳሰቡት ነው ብለዋል። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አገራት በሂደቱ ላይ በቀጥታ ተጽእኖ የሚያደርጉ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ የውይይቱን አቅጣጫ ሁሉ እስከማስቀየር ይደርሳሉ ። አንዳንዶች ሸምጋይ ...

Read More »

በዝርፊያ ወንጀል የሚጠረጠሩ የቀድሞ የልማት ባንክና የንግድ ባንክ ባለስልጣናት ከአገር መኮብለላቸው ታወቀ

የካቲት ፲፫ ( አሥራ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአብዛኛው የቀድሞ የህወሃት የጦር መኮንኖችና አባላት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከልማት ባንክና ከንግድ ባንክ እንዲበደሩ በማድረግ በጋምቤላ ሰፋፊ መሬቶችን እንዲገዙ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸው የሚነገርላቸው የልማት ባንክ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረን ጨምሮ ሌሎች የልማት ባንክ እና የንግድ ባንክ የስራ ሃላፊዎች ከአገር መውጣታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ድርጊቱ ግለሰቦቹንና ከእነሱ ጀርባ ያሉትን ባለስልጣናት ሆን ...

Read More »

ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች የአዲስ አበባ ፋርማሲዎችን አጥለቅልቀዋል

የካቲት ፲፫ ( አሥራ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መገኛ ምንጫቸው በትክክል የማይታወቁና በኮንትሮባንድ ጭምር እንደሚገቡ የሚነገርላቸው የተለያዩ መድሃኒቶች በአዲስአበባ በሚገኙ በአንዳንድ ሕጋዊ መድሃኒት መሸጫ ፋርማሲዎች፣ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎች እየተቸበቸቡ ነው፡፡ መድሃኒቶቹ በተለያዩ መጠቅለያዎች ተጀቡነው ድንበር አቋርጠው የሚገቡ መሆናቸውን፣ ከመንግሥት ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በአንዳንድ ምግባረ ብልሹ ሠራተኞች እየተመዘበሩ በፌስታልና በመሳሰሉ ጥንቃቄ በጎደላቸው መያዣዎች ወደፋርማሲዎቹ እንደሚሸጋገሩ ፍንጭ መኖሩን ከጤና ቢሮው ...

Read More »

በአስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ምክንያት 100 ሺህ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ አለመምጣታቸው ተዘገበ

የካቲት ፲፫ ( አሥራ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት የተለያዩ አገራት ማንኛውንም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የጉዞ እቀባ መጣላቸውን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቁጥራቸው ከ100 ሺህ በላይ አገር ጎብኚ ቱሪስቶች መቅረታቸውን የጁሚያ ትራቭል ጥናትን በመጥቀስ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ከሁለት ዓመት በፊት 900 ሺህ ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ...

Read More »

ብኢኮ ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላን ለማስራት ከ235 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለሁለት አገራት ኩባንያዎች ክፍያ ፈጸመ ።

የካቲት ፲ ( አሥር )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውና አብዛኛውን የመከላከያን ግዢ በኮንትራት ወስዶ የሚሰራው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላኖችን በአገር ውስጥ ለማሰራት ከ235 ሚሊዮን 500 ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይም 4 ቢሊዮን 710 ሚሊዮን ብር መክፈሉን ከድርጅቱ የተገኙ የሂሳብ መዝገብ ሰነዶች አመለከቱ። ብኢኮ በፈንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ብቻ ከ1 ...

Read More »