Amsterdam

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የአዮዲን እጥረት ተከሰተ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዮዲን እጥረት በዋንኛነት የእንቅርት በሽታ የሚያስከትል ከመሆኑም በተጨማሪ የህጻናት የአእምሮ ዕድገት በመጉዳት በዘላቂነት የአምራች ዜጋ እጦትን ያስከትላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ጨው የሚመረትባቸው አካባቢዎች አፋር ክልል ዶቢ እና አፍዴራ ሐይቆች እንዲሁም በሶማሌ ክልል ኢራካል ሐይቆች በሚገኝ ምርት ነው፡፡ ከሚኒስቴሩ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ወር ጊዜውስጥ ብቻ 300 ሺ ኩንታል ...

Read More »

የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ስራውን እንዲያቆም ተጠየቀ፡፡

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የግንባታ ተቋራጮች እንደተናገሩት ስራቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ሰርተው ለማጠናቀቅ እንዳይችሉ ችግር እየፈጠረባቸው ያለው የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት በመሆኑ ስራውን እንዲያቆም ጠይቀዋል፡፡ ሰሞኑን በክልሉ የግንባታ ባለሙያዎችና በጤና ጥበቃ ቢሮ መካከል በተደረገው የስድስት ወር አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተናገሩት የተቋራጭ ድርጅት ተወካዮች፣ የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ባለሙያዎች ...

Read More »

በነርሶቸ እንዘላልነት የአንድ ወላድ ህይወት አለፈ

የካቲት ፳፰ ( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቀጨኔ ልዩ ስሙ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ህዳሴ በሚባል ጤና ጣቢያ ውስጥ ነርሶች ለወላዷ የምጥ መርፌ ከወጉዋት በሁዋላ ፣ ከወላዱዋ ርቀው ሲጫውቱ ቆይተው ሲመለሱ ህይውቱዋ አልፎ ያገኙዋት ሲሆን፣ በዚህ ድርጊት የተብሳጩት የአካባቢው ነዋሪዎቸ የጤና ጣቢያውን በሮችና መሰኮቶች በድንጋይ ሰባብረዋል። ወላዱዋ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ እንደገባችና ምሽት ...

Read More »

በከንቲባው ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በጎንደር የሚደረገው ፍተሻ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

የካቲት ፳፯ ( ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጎንደር ከተማ ያለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ በጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባባል መኖሪያ ቤት ላይ የቦንብ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ አባላት የአካባቢውን ህዝብ ሲያዋክቡ መሰንበታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ጥቃቱ በግለሰቡ ላይ ያደረሰው ጉዳት ይኑር አይኑር የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ጥቃቱ እንደተሰማ አካባቢው በወታደሮች ታጥሮ የጥቃቱን ...

Read More »

በጂንካ የሙስሊም አመራሮች ታሰሩ

የካቲት ፳፯ ( ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ሦስት የሙስሊም አባቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ እስካሁን ምክንያቱ ባልተገለጸላቸው ሁኔታ በጂንካ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡ አባቶችን ለመያዝ በዞኑ ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ ቤታቸውን የፈተሸው ቡድን ከሃይማኖታዊ ስነስርዓት ውጭ በሆነ ሁኔታ መስገጃቸውን በጫማቸው በመርገጥ ፣ የህጻናት የመማሪያ ደብተሮች ሳይቀር በማገላበጥና የቤት ዕቃዎችን በመበታተን ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፊታችን ማክሰኞ ስድስተኛ ወሩን ይይዛል

የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ በኦሮሚያ፣ አማራ እና ደቡብ ክልሎች የገጠመውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የሚኒስትሮች ም/ቤት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም ያወጣው የአስቸኳዋ ጊዜ አዋጅ የተቀመጠለትን የስድስት ወራት ጊዜ ሊጨርስ አራት ቀናት ብቻ ቢቀሩትም፣ አዋጁን ለማንሳት ፍንጭ አለመታየቱ አዋጁ ሊራዘም ይችላል የሚለውን ግምት እያጠናከረው መጥቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ሀገሪትዋ በወታደራዊ አገዛዝ ...

Read More »

በሶማሊ እና በኦሮምያ ክልሎች ድንበር አካባቢ የሚታየው ውጥረት መቀጠሉን ተከትሎ ነዋሪዎች እየሸሹ ነው

የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያ ወደ ኦሮምያ ክልል በመግባት በህዝብ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ አደጋ ያስከተለ ሲሆን፣ በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የሶማሊ ክልል አርማን እያውለበለቡ መሬቱ የእነሱ እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከልዩ ሃይሉ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመቋቋም የሞከሩ የኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች ፣ ልዩ ሃይሉ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመተባበር ...

Read More »

ኢህአዴግ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ ያስችለኛል ያለውን የገንዘብ ድጎማ ለጎንደር ከተማ ሴቶች አከፋፈለ፡፡

የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጎንደር ብአዴን ጽ/ቤት በተገኝው መረጃ መሰረት በጎንደር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ እና ሴቶችን ያማካለ ሰላም የማምጣት ስትራቴጅ በሚል በታቀደው መሰረት ከመንግስት በጀትና በG.F በጎንደር ከተማ በግሎባል ፈንድ ከተለገሰው ገንዘብ ተቀንሶ በብአዴን ስም የተለገሰ እና በረጅም ጊዜ ተመላሽ የሚሆን ከወለድ ነፃ የገንዘብ ድጋፍ ስራ በ1ኛ ዙር ለተመረጡ 657 ሴቶች ለእያንዳንዳቸው ...

Read More »

ታፍኖ የተወሰደው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ያለበት ቦታ አልታወቀም

የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ወሎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አቶ መኳንንት ካሳሁን ከሃሙስ የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ቦታው በደኅንነቶች ታፍኖ ከተወሰደበት ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ያለበት አድራሻ ባለመታወቁ ወላጅ እናቱን ጨምሮ መላው ቤተሰቡ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። ደሴ ከተማ ውስጥ የሚኖረው አቶ መኳንንት ...

Read More »

በአማራ ክልል የኮሌራ በሽታ በድጋሚ ተከሰተ፡፡

የካቲት ፳፬ ( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት ለበርካታ ዜጎች ሞት ምክንያት የነበረው የኮሌራ ወረርሽኝ በድጋሜ በባህር ዳር አካባቢ አንዳሳ ቀበሌ መከሰቱን ከጤና ጥበቃ ቢሮ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ በበሽታው ከሰላሳ በላይ ሰዎች መለከፋቸውን የሚጠቁመው መረጃ ፣ ታማሚዎችን በባህርዳር ከተማ አዲስ በመሰራት ላይ ባለው ሆስፒታል ለማከም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡በሽታው በቀጣዩ የዝናብ ወቅት ሊቀጥል እንደሚችል የተናገሩት ...

Read More »