መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ጥቃት ይደርስብናል በሚል ተሸሽገው የቆዩ 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሰዎቹ የተያዙት ከዚህ በሁዋላ ምንም እንደማይደርስባቸው በአገር ሽማግሌዎች ማረጋገጫ ከተሰጣቸው በሁዋላ ነው። በአሁኑ ሰአት የአካባቢው ህዝብ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች፣ በርካታ ሰዎች አካባቢውን ጥለው እየሸሹ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ...
Read More »Amsterdam
በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የሲቪል ሰርቪስ የምዘና ሂደት መከነ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደኢህዴግ ከፍተኛ ካድሬ በሆኑት አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ለመተግበር እየሞከረ ያለው የመሠረታዊ የሥራ ሒደት (BPR) እና የውጤት ተኮር ሥርዓት (Balanced Score Card/BSC) ምዘና መምከኑን ምንጮች ገልጹ። የምዘና ዕቅዱ በሰራተኞች ተቀባይነት አጥቶ ቢከሽፍም፣ የኢህአዴግ አገዛዝ ግን ዕቅዱን ለማስፈጸም በሚል ዛሬም ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ነው። የሚኒስቴሩ ምንጮች ...
Read More »የአባይ ግድብ በእንቦጭ አረም ሊጠቃ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ተነገረ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ክልል አቀፍ የእምቦጭ አረም አስወጋጅ ዩኒት አስተባባሪ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት ወ/ሮ በፍታ ጥሩነህ ሰሞኑን ለመንግስት ሚዲያዎች እንደተናገሩት የአረሙ ስጋት በጣም ሠፊ በመሆኑ ተስፋ የተጣለበት ይህ ትልቅ ግድብ በእንቦጭ አረም ሊጠቃ እንደሚችል ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡ ዩኒት አስተባባሪዋ ስለመጤ አረሙ ሲያስረዱ የውሀን ተፈጥሯዊትነት በማዛባት እንዲደርቅ የሚያደርገው ...
Read More »አንድ የአሜሪካ የፓርላማ አባል ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ እንዲቋረጥ ጠየቁ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሎራዶ 6th ዲስትሪክት ተወካይ የሆኑት ማይክ ኮፍማን ለአገራቸው ምክር ቤት የውጭ እርዳታ አስተባባሪ ክፍል በጻፉት ደብዳቤ የኢህአዴግ መንግስት የሚፈጽመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እስኪቆም ድረስ በመጪው አመት ሊሰጥ የታሰበው የእርዳታ ገንዘብ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል። “ዛሬ ይህንን ደብዳቤ እንድጽፍ ያደረገኝ እኔን የመረጡኝ አብዛኛዎቹ ኢትዮ-አሜሪካዊያንን ባቀረቡልኝ ጥያቄ መሰረት ነው። “ ያሉት የፓርላማ አባሉ፣ በስልጣን ላይ ...
Read More »በድንበር አካባቢ ያለው ጸጥታ አለመረጋጋቱን ሚኒስትሩ አስታወቁ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሚቀጥሉት አራት ወራት እንዲራዘም ለተወካዮች ምክርቤት ጥያቄ አቅርበው የተፈቀዳላቸው የወታደራዊ እዙ ( ኮማንድ ፖስት) ዋና ጸሃፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣ አዋጁ እንዲራዘም ያስፈለገው ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ጸረ ሰላም ሃይሎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ በአማራ ክልል በትግራይና አማራ ፣ በኦሮምያ እና በሶማሊ እንዲሁም በቤንሻንጉልና በአማራ ድንበሮች አካባቢ ጦርነቶች እየተደረጉ ...
Read More »ባህርዳር ውስጥ በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ላይ አንድን ወጣት ገጭቶ የገደለው ባለስልጣን ከተለቀቀ በሁዋላ መልሶ ታሰረ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃይለኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ሲያሸከረክር የነበረው የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ ተሻገር በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ወይም “ዜብራ ክሮስ” ላይ ጋሻው የተባለውን ወጣት ገጭቶ ከገደለው በሁዋላ፣ በእለቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢወሰድም በማግስቱ የተለቀቀ ሲሆን፣ ኢሳት ዜናውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ግን ተመልሶ እንዲታሰር መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል። ድርጊቱ የከተማው ህዝብ ...
Read More »ከውጭ አገራት በተለያዩ መንገዶች የገባ 50 ቢሊዮን ብር ባንክ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ የውጭ አገር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለኢትዮጵያውያን ለልማት እያሉ በብሄራዊ ባንክ በኩል ከሚያስተላልፉት ገንዘብ ውስጥ 50 ቢሊዮን ብር ጥቅም ላይ ሳይውል ተቀምጦ እንደሚገኝ የብሄራዊ ባንክ ምንጮቻችን ገልጸዋል። የውጭ አገር ዜጎች ለልማት እያሉ የሚያስገቡት ገንዘብ፣ በድርጅቶቹ ደካማ እቅድ አፈጻጸም ወይም በሌሎች ምክንያቶች ጥቅም ላይ ሳይውል ተከማችቶ እንደሚገኝ የሚገልጹት ምንጮች፣ የባንኩ ሃላፊዎችና ...
Read More »በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ወርልድ ቪዥን ገለጸ
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ አለመጣሉን ተከትሎ በተፈጠረ ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን ወርልድ ቪዥን አስታውቋል። የአየር ትንበያዎች በመጪዎቹ ወራቶች ካሁኑ በከፋ ሁኔታ የዝናብ እጥረቱ ተባባሶ እንደሚቀጥልና ከቀድሞው 45 በመቶ ከመቶ በታች የሆነ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል ያመለክታሉ። ከምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ...
Read More »ረሃብና ጦርነትን የሸሹ በሽዎች የሚቆጠሩ ሶማሊያዊያን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየፈለሱ ነው።
መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብዙ ኪሎሜትሮችን በእግር በመጓዝ ሕጻናትን የያዙ እናቶች፣ ነፍሰጡሮች እና አቅመ ደካማ ሶማሊያዊያን አገራቸውን እና መኖሪያ ቀያቸውን በመተው ኢትዮጵያ ውስጥ ወደሚገኘው ዳሎ አዶ መጠለያ ጣቢያ እየጎረፉ ነው። ሶማሊያውያን በርሃብ የተጎዱ ልጆቻቸውን ማጥባት የተሳናቸው ሲሆን፣ አገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት ረሃብ እና ጦርነትን ሸሽተው መሆኑን ተናግረዋል።
Read More »ሼክ አላሙዲን የህዝብ የልማት ድርጅቶችን የገዙበትን ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ አልከፈሉም ተባለ
መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስትን ድርጅቶችን ወደ ግል በማዞር ሒደት አገዛዙ ለግል ባለሃብቶች ከሸጣቸው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ እንዳልተከፈለና አብዛኛውን እዳ የተሸከሙት ባለሀብቱ ሼክ ሙሃመድ ሁሴን አላሙዲን መሆናቸው ተገልጿል። መንግሥታዊው አዲስዘመን ጋዜጣ በረቡዕ መጋቢት 20 ቀን ዕትሙ እንደዘገበው ከመንግሥት ወደግል ከተዛወሩ 29 ድርጅቶች በጠቅላላው ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ ክፍያ ያልተፈጸመበት ሲሆን፣ ከዚህ ...
Read More »