Amsterdam

በአማራ ክልል ካሉ ትምህርት ቤቶች 87 ከመቶ የሚደርሱት ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቆርቋሪ እያጣ ነው ተብሎአል። መሠረታዊ የግብዓት እጥረት መኖር ፣ የመምህራን ድጋፍ ማነስ፣ የወላጆች ክትትልና ድጋፍ አለመኖር፣የተማሪዎች የመማር ፍላጎትን ከመቀነስ አልፎ 87 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች እንዲሆኑ ምክንያቶች መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መገምገሙን ገለጸ፡፡ ብዙዎቹ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ተማሪዎች ተነሳሽነት ...

Read More »

በቆላድባ አንድ ወታደር የ14 ዓመት ልጃገረድ መድፈሩን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን አሰማ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው የሚታየውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ከተላኩት ወታደሮች መካከል አንዱ የሆነው ለጊዜው ስሙ ያልታወቀው ወታደር፣ እሁድ ሚያዚያ 1 ፣ ከጓደኛው ጋር በመሆን አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ በጉልበት ወስዶ ደፍሯታል። ታዳጊዋ ደም እየፈሰሳት ለአካባቢው ሰዎች መናገሩዋን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ሰቀልት ክፍል ወይም ቀበሌ ዜሮ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነቸው ...

Read More »

በምስራቅ ጉጂ በረሃብና በበሽታ ህጻናት እያለቁ ነው ተባለ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ጉጂ ዞን ቆላ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱንና ይህንን ተከትሎም ወረርሽኝ በመከሰቱ የበርካታ ህጻናት ህይወት እያለፈ ነው ። በተለይ በዞኑ በሚገኙ 6 ወረዳዎች የሚላስ የሚቀመስ የለም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ህጻናት በተቅማጥና ትውከት እያለቁ ነው ይላሉ። በሃራቀሎ፣ ሉባን፣ ሰባ ቦሩ እና ደዋ ቀበሌ የሚኖሩ ነዋሪዎች የሚደርስላቸው ...

Read More »

በደቡብ ክልል የአርበኞች ግንቦት7 አባላት ወረቀቶችን በትነው ማደራቸውን አስታወቁ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪዎች ለኢሳት በላኩት መረጃ በሐዋሳ ፣ በወላይታ ከተማ ፣ በአርባምንጭ ፣ በኮንሶ ፣ በጅንካ እንዲሁም በአቶ ኃ/ማሪያም ደሰላኝ የትውልድ አከባቢ በሆነው አረካ አካባቢ “ ከአሁን በሁዋላ በወያኔ መታለል ይቁም፣ የታጋይ አርበኞቻችን ደም በከንቱ እንደፈሰሰ አይቀርም፣ በወያኔ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝቡን መብት ለማፈን እና አርበኞችን ትግል ለማደናቀፍ ያለመ ቢሆንም የአርበኞች ...

Read More »

መሬታቸውን የተነጠቁ አርሶአደሮች ካሳ ሳይከፈላቸው ለአመታት መቆየታቸውን ገለጹ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዋሽ ሐራ ገበያ – መቀሌ እየተገነባ ካለው የባቡር መስመር ጋር ተያይዞ አርሶአደሮች ያላ አንዳች የካሳ ክፍያ ለዓመታት መቆየታቸውን ተናገሩ፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳን አቋርጦ ወደ መቀሌ ከተማ እየተገነባ ያለው የባቡር መስመር በርካታ አርሶአደሮችን ለችግር ዳርጐ መቆየቱን የቀበሌ ነዋሪዎች ለመንግስት ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በባቡር ሃዲዱ ግንባታ ምክንያት መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ለሁለት ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳደር ተቃውሞ የተነሳበትን የመንገድ አዋጅ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ገለጸ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ታናሽ ወንድም አቶ ገነቱ ደሳለኝ የሚመራው የአዲስአበባ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አወዛጋቢውን የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ በአዲሱ ደንብ በሚያዝ ሪከርድ መሠረት በተደጋጋሚ አጥፍተዋል የተባሉ አሽከርካሪዎች ፈቃዳቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ይገደዳሉ፡፡ ኤጀንሲው ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን በአዲስዘመን ጋዜጣ መጋቢት 28 ቀን ...

Read More »

ወደ ማላዊ የገቡ 56 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሚያዝያ ፩ (አንድ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብተዋል የተባሉ 56 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ የድንበር ፖሊሶች መያዛቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ለጊዜው መነሻቸው ከየት እንደሆነ ያልታወቀው ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በመኪና ተጭነው በሕገወጥ መንገድ ወደ ካሮንጋ ግዛት ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ሃምሳ ስድስቱም ኢትዮዮጵያዊያን ስደተኞች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና የጭነት መኪናው አሽከርካሪ መኪናውን በመተው ከአካባቢው መሰወረኑን ፓሊስ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ይዘው የሚሰሩ ዜጎች መበራከታቸውን መረጃዎች አመለከቱ ። በአገሪቱ የሚታየው የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መበራከት ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን ዜጎች ይናገራሉ።

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃሰት የትምህርት ማስረጃ ይዘው ከሚሰሩት መካከል ደግሞ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች መገኘታቸው በትውልዱ ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ዜጎች ይናገራሉ። በዲግሪ የተመረቁ መምህራን 8ኛ ክፍል ማስተማር አንችልንም ብለው ወደ አንደኛ ደረጃ እንዲመደቡ የጠየቁ መኖራቸውን የክልሉ ሌላው ባለስልጣን ይናገራሉ ። ህክምና ተምረው ሃኪም ያዘዘውን መድሃኒት በትክክል ለመስጠት የማይችሉ ፋርማሲስቶች መኖራቸውንም ባለስልጣኖች ይገልጻሉ ። በኢትዮጵያ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ቤት የማፍረስ ዘመቻው ተባብሶ ቀጥሏል ከ20 ሽህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አካባቢ ያሉ ነባር ባለይዞታ ነዋሪዎች ካለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀሉ ተባብሶ ቀጥሏል። ለዘመናት ተወልደው ያደጉበት መኖሪያ ቤት፣ የሸቀጥ ማከፋፈያ ሱቆች፣ ስጋ ቤቶች፣ ፋርማሲዎች፣ ግሮሰሪዎች፣ የተለያዩ አነስተኛ እና የጅምላ ማከፋፈያ የንግድ ድርጅቶች በዘመቻ እንዲፈርሱ እየተደረገ ነው። በቀበሌ ቤቶች ውስጥ ነዋሪ ለሆኑት ለ6 ወራት የቤት ኪራይ የሚሆን ...

Read More »

በአርባምንጭ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ እየተፈናቀሉ መሆኑን ገልጹ

መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሃንዳዋሎ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ከ1500 በላይ አባዎራዎች ከተማዋ የዛሬ 50 ዓመት ስትቆረቆር ጀምሮ ከነበሩበት ቀየ ለቃችሁ ውጡ በመባላቸው፣ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ከነባር ይዞታቸው ሲነሱ አስፈላጊው ቤትና ቦታ አልተሰጣቸውም። ለምን ብለው የጠየቁ ከ10 ያላነሱ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ዜጎች እየተፈናቀሉ መሬቱ ለካቢኔ አባላቱ እየተሰጠ ...

Read More »