Amsterdam

በመርሃቤቴና በመንዝ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጋዮች ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱ የዞኑ ፖሊስ አመነ

ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን በመርሃ ቤቴና በመንዝ ቀያ ወረዳዎች በመዘዋወር ለነጻነታቸው ሲዋጉ የተሰውት ሁለቱ የነጻነት ታጋዮች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አምኗል። በነበሩ ከመሰለውና ጭንቅል አስጨናቂ የተባሉት የነጻነት ታጋዮች ፣ በገዢው ፓርቲ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ለገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆነው ነበር። ታጋዮቹ በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ጽ/ቤት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ተግባራዊ መሆን አለበት ሲል አሳሰበ

ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ15 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ተከትሎ የተነሳውን ጦርነት ለማስቆም የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት ተከትሎ፣ የተቋቋመው የድንበር ኮሚሽን (EEBC) የሰጠው ውሳኔ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል ብሎአል። የአፍሪካ ቀንድን ችግር በዘላቂነት ይፈታል የተባለውን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ተግባራዊ አለመደረጉ እንደሚያሳስባቸው የገለጹት የህብረቱ ካውንስል ጻሃፊ ወ/ሮ ፌዴሪካ ሞጎሪኒ ፣ ችግሩ ከቀጠናው ባለፈም ...

Read More »

በአዲስ ዘመን የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ ከተማው ገቡ

ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በሊቦ ከምከም ወረዳ አዲስ ዘመን ከተማ ላይ በወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ፣ ተጨማሪ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል ቁጥራቸው ሁለት መቶ የሚሆኑ ወታደሮች ትናንት ምሽት ወደ ከተማዋ በመግባት በድሮው ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት አካባቢዎች መስፈራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ምሽቱን የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ቢገልጹም፣ የተኩሱን መንስኤ ግን ለማወቅ አለመቻላቸውን ...

Read More »

“የመንግስት ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል” ሲል የዋድላ ወረዳ ቤ/ክህነት አስታወቀ

ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቤተ ክርስቲያን የራሱዋ የሆነ መተዳዳሪያ ደንብ ያላት ቢሆንም፣ አገዛዙ በየጊዜው ጣልቃ እየገባ መመሪያዋን ተግባራዊ ማድረግ አለመቻሉዋን የወረዳው ቤ/ክህነት ሃላፊዎች አቤቱታ አሰምተዋል። አመራሮቹ ፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ጠዋት ወደ ቤ/ክርስቲያን እየመጡ “ ስብሰባ አለ፣ መልዕክት አለ፣ ይህን ክፍያ ክፈሉ” እያሉ መእመናንን እያስቸገሩ ነው ያሉ ሲሆን ፣ አሰራሩ ቤ/ክርስቲያኑዋ የሰበሰበቻቸውን ምዕመን ለመበተን የተደረገ አሰራር ...

Read More »

በኦሮምያ የመንግስት ሰራተኞች ለኦህዴድ በግዳጅ የሚከፍሉት ክፍያ እንዲቆም ጠየቁ

ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ አንዳንድ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለኦህዴድ ማጠናከሪያ በሚል ለአመታት ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው የሚቆረጠው ገንዘብ እንዲቆም ጥያቄ አቅርበዋል። በክልሉ ውስጥ የሚኖር የየትኛውም ብሄር ተወላጅ ከደሞዙ 5 በመቶ ለኦህዴድ በግዴታ ይከፍላል። በጅማ ዞን በሚገኙት ሰቃ፣ ደዶ እና ጎማ ወረዳዎች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ከእንግዲህ ክፍያ አንከፍልም በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፣ ከእንግዲህ ደሞዛችን በግድ የሚቆረጥ ከሆነ ...

Read More »

ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ 11 ሚሊዮን ሕዝብ ለርሃብ ተጋላጭ መሆኑን ተመድ አስታወቀ

ሚያዝያ ፫ (ሦስት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ አገራት በተከሰተ ድርቅ 11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ በተባበበሩት መንስግታት ድርጅት የሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ እና የዓለም የምግብ ድርጅት በጋራ አስታውቀዋል። ድርቁ በደቡብ ሱዳን ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎችን ሲያጠቃ፣ ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው። በደቡብ ሱዳን ከድርቁ በተጨማሪ የእርስበርስ ጦርነቱ በነዋሪዎቹ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 ተጨማሪ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈጸሙን የሚገልጸው አርበኞች ግንቦት7 ፣ መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓም ከሱዳን ተነስቶ ወደ ጎንደር በማቅናት ላይ የነበረ የሱዳን ታርጋ ያለው መኪና ላይ በፈጸመው ጥቃት የመኪናውን ከፊል አካል ማቃጠሉን ገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ካለበት አካባቢ ነው። እንዲሁም ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓም አምባጊዮርጊስ አካባቢ የአገዛዙ ሰላይ ...

Read More »

በይርጋለም ከተማ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ ከ15 በላይ የፋይናንስና የማዘጋጃ ሰራተኞች በሙስና በሚል ተሰብስበው ታስረዋል። እርምጃው የተወሰደው በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ነው። የድርጅተ ሰራተኞች እንደገለጹት በሙስና የተዘፈቁት ዋናዎቹ አመራሮች ሆነው እያለ እነሱን ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዛወር፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ተራ ሰራተኞች ይዘው አስረዋል። እስሩን ተከትሎ በሰራተኞች ዘንድ አለመረጋጋት መፈጠሩን ሰራተኞች ተናግረዋል። ...

Read More »

ኦብነግ ከሶማሊ ልዩ ሃይልና ከመከላከያ ጋር መዋጋቱ ተዘገበ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሁለት ቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊት በሚደገፈው የሶማሊ ልዩ ሃይልና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት መካከል በደጋሃቡር አውራጃ፣ በብርቆት ወረዳ ልዩ ስሙ ሊዲለይ በሚባል ስፍራ ላይ በተደረገ ውጊያ 3 አዛዦችን ጨምሮ 17 ወታደሮች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። 21 ቁስለኛ ወታደሮች ደግሞ በአየር ወደ ጅግጅጋ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን እማኞች እንደገለጹለት ...

Read More »

የአረካ ገበያ ተቃጠለ

ሚያዝያ ፪ (ሁለት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ በሆነችው አረካ ከተማ የሚገኘው የገባያ ማእከል በመቃጠሉ ከፍተኛ ንብረት ወድሟል። አብዛኞቹ ሱቆች በአቶ ሃይለማርያም የቅርብ ዘመዶችና በደኢህዴን አባላት የተያዙ እንደነበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ የእሳቱ መንስኤም የአስተዳደር በደልንና ሙስናን ከመወጋት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግምታቸውን ይገልጻሉ። የዚህ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የአስተዳደር በደል የሚፈጸምባቸው ሲሆን፣ በተለይ ወጣቶች ...

Read More »