ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች ተነስቶ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች ያደረሱትን ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገኖች ለማጣራት ያቀረቡትን ጥያቄ ኢህአዴግ ውድቅ አድርጎታል። ቢቢሲ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጠቅሶ እንደዘገበው በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም ሆነ በመንግስታት የቀረበውን ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ የማቋቋም ሃሳብ በአገዛዙ በኩል ተቀባይነት አላገኘም። አቶ ...
Read More »Amsterdam
አርሶአደሮች በደረሰኝ እየተጭበረበሩ ነው ተባለ
ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት የቁም ከብት በሚሸጡ አርሶአደሮች ላይ ያወጣው ተጨማሪ ክፍያ አርሶአደሮችን ለብዝበዛ እየዳረገ መሆኑን ገዳቱ የደረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ቀደም ብሎ በአንድ የቁም ከብት 3 ብር ይከፈልበት የነበረው ክፍያ ወደ 10 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አርሶአደሮች ቢቃወሙትም ሰሚ አላገኙም። ባለፈው ሳምንት በጉራጌ አካባቢ ገንዘቡን የሚሰበስቡ ሰዎች ከአርሶአደሮች በከብት 15 ብር እየተቀበሉ፣ ደረሰኙ ...
Read More »የስቅለት በዓል በመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች የስቀለት በዓልን አክብረው ውለዋል። በኢትዮጵያ የእምነቱ ተከታዮች እለቱን በስግደት እና ጸሎት አሳልፈዋል። በዚህ አመት የአመት በአል ገበያ የዋጋ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን ወኪላችን ገልጿል። በተለይም በእርድ በሬ፣ ዶሮና ሽንኩርት ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።በደቡብ እና ኦሮምያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ዘይትና ስኳር ሙሉ በሙሉ ከገበያ ...
Read More »በአዲስ አበባ ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደዘገበው ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በተለይም በፒያሳ አካባቢ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት የሚታዩ ሲሆን ፣ ምሽት ላይ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው በሚያመሩበት ጊዜ ፍተሻ ያደርጋሉ። አንዳንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ነዋሪዎችን በሚፈትሹበት ወቅት ‘ አይዟችሁ አትፍሩ ታዘን ነው የምንፈትሸው እንደሚሉ” ወኪላችን ገልጿል። የገዢው ፐርቲ የደህንነት አባላት በአሉን ...
Read More »በኢትዮጵያ በረሃብ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ ተቋም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ወራት ድረስ የሚጥለው የዝናብ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ20 እስከ 30 ቀናት ዘግይቶ እንደሚጀምር እና የዝናቡም መጠን በአማካኝ ከነበረው አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል በወርሃዊ ሪፖርቱ ገልጿል። በድርቅ ክፉኛ ተጠቂ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የዝናብ ስርጭቱ ከ30 እስከ 40 ቀናት ዘግይቶ ይጥላል ...
Read More »የተመድ የልማት ፕሮግራም ኢትዮጵያን በመጨረሻዎች ደሃ አገራት ደረጃ አስቀመጠ
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእየለቱ ብዙ የሚባልለት የኢትዮጵያ ባለሁለት አሃዝ ኢኮኖሚ እድገት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራምን እጅግም አልመሰጠው። ዘንድሮም ድርጅቱ አገሪቱን በአለም እጅግ ድሃ ከሚባሉ አገራት ተራ መድቧታል። ምንም እንኳ ባለፉት 25 ዓመታት መሻሻሎች ቢኖሩም ፣ ኢትዮጵያ በብዙ መስፈርቶች አሁንም እጅግ ዝቅተኛ ሰብአዊ ልማት ( Low Human Development Category) ካላቸው አገራት ተርታ ትመደባለች ያለው ...
Read More »በይርጋለም የታሰሩት የመንግስት ሰራተኞች በእስር እንዲቆዩ ውሳኔ ተላለፈባቸው
ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ይርጋለም ከተማ በአንድ ጊዜ ከ10 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ የሲዳማ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰራተኞች ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ባለመቀበል ለተጨማሪ 10 ቀናት በእስር ቤት እንዲቆዩ ወስኗል። በግለሰቦቹ ላይ የቀረበው ክስ የበሉትን አበል አላወራረዱም የሚል መሆኑን ችሎቱን የተከታተሉ ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ግን በጅምላ የተደረገው እስር ...
Read More »ኢህአዴግ “በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ በጠባብነትና ትምክተኝነት የተነሳ ነው” ሲል ራሱን ሸንግሎ ተሃድሶውን ማጠናቀቁን አስታወቀ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያና አማራ እንዲሁም በአንዳንድ የደቡብ ክልሎች የታዩትን ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተከትሎ አገሪቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስአዋጅ አውጥቶ በወታደራዊ ሃይል እየገዛት ያለው ኢህአዴግ፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ ብሎ ያስቀመጠውን ጥልቅ ትሃድሶ ሲያጠናቅቅ፣ ለተቃውሞው መነሻ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃንን ተጠያቂ አድርጓል። ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶው በድል ተጠናቋል ቢልም ህዝቡ ግን ተሃድሶው የተባለውን ከቁም ነገር አልቆጠረውም። የኢህአዴግ ምክር ቤት ...
Read More »ታጋዮች በበለሳ ወረዳ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሙ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ለኢሳት በላኩት መግለጫ በበለሳ ወረዳ ባጃየ ንኡስ ወረዳ ሚያዚያ 4 ቀን 2009 ዓም ሌሊት ላይ በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ታጋዮቹ ለግማሽ ሰአት ያክል አካባቢውን መቆጣጠራቸውንና ያለምንም ጉዳት ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ጥቃቱን በተመለከተ በገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ መልስ የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ ዘመን በመስተዳድሩ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ...
Read More »ገዢው ፓርቲ ያልተመዘገቡ ናቸው ያላቸውን ከ300 ሺ በላይ የስልክ ሲም ካርዶችን ከአገልግሎት ውጭ አደርጋለሁ አለ
ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልክ የሚታገዙ ወንጀሎችን፣ ማጭበርበርን እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ደንበኞች የሚገለገሉባቸውን ሲም ካርዶች ባለማስመዝገባቸው 349 ሺ 261 ሲምካርዶች ከአገልግሎት ውጭ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት አስታውቋል። የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ሚንስትር ዶ/ር ደብረ ፅዩን ገ/ሚካኤል ፣ ሲም ካርዶቹ ከአገልግሎት ውጭ ከመሆናቸው በፊት ሰነድ የሌላቸውን የሲም ካርድ ባለቤቶች ለመመዝገብ ፣ በአሁኑ ስዓት ማንነታቸው በማይታወቁ ...
Read More »