.የኢሳት አማርኛ ዜና

አዲስ የእስልምና ም/ቤት ተቋቋመ

የ ኢትዮ ጵያ ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ሲያስተባብሩ በነበሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ያሸባሪነት ክስ በተመሰረተ ማግስት አዲስ ያእስልምና ም/ቤት መቐቐሙን መንግስታዊ ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል። በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የተመረጡት ያእስልምና ም/ቤት አባላት ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወከሉ መሆናቸውን ከወጣው ዝርዝር መረዳት ተችሎዋል ። በሳዑዲ አረቢያ የ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በዋና ፀሐፊነት እና በቢሮ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሼክ ኪያር መሀመድ አማን በሊቀመንበርነት ...

Read More »

አምነስቲ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቀ

ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ ኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር በመጠየቃቸው አ ፍሶ ያ ሰራቸውን ኢትዮጵያውያን በ አስቸክዋይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለመንግስት ጥሪ አቀረበ ። መንግስት በ አሸባሪነትና የተለያዩ የወንጀል ምክንያት እየፈጠረ ያሰራቸው ሰዎች ያደረጉት ነገር ወይም የጠየቁት ጥያቄ እራሱ ባወጣው በሀገሪቱ ህገመንግስትና በ አለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት ያለውና ህጋዊ በመሆኑ ሊታሰሩም ሊከሰሱም ...

Read More »

የኦህዴድ ክፍፍል ወደ ዞን ባለስልጣናትም ወረደ

ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦህዴድ ክፍፍል ወደ ዞኖች ወርዷል፣ ይህን መንግስት ተቀብለን እንቀጥላለን ወይም አንቀጥልም የሚሉ ሁለት ቡድኖች መፈጠራቸውን አባላቱ ገለጡ ስማቸው እንዳይገለጥ ያስጠነቀቁ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለኢሳት እንደገለጡት በኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረው መከፋፈል ወደ ዞኖች ወርዶ በድርጅቱ ውስጥ ሁለት ቡድኖች እንዲፈጠሩ አድርጓል።   ከፍተኛ ክፍፍል በሚታይበት በሀረሪ ክልል ፣  በአንድ በኩል ይህንን ስርአት ደግፈን መጓዝ አለብን ...

Read More »

በሲዳማ ዞን ቡና አምራች አርሶ አደሮች ተቃውሞ አስነሱ

ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል፣ ሲዳማ ዞን፣ በንታ ወረዳ ቡና አምራች ገበሬዎች ተቃውሞውን ያነሱት የቡና መሸጫ ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ሆኖአል በማለት ነው። በትናንትናው እለት ቡና አምራቾች ለቡና ግዢ የሄዱ ነጋዴዎችን በተለያዩ መሳሪያዎች በማስፈራራት ፣ ሚዛኖቻቸውን በመሰባበርና ንብረታቸውንም በመቀማት አካባቢውን ለቀው አንዲወጡ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሎአል።   የወረዳው ፖሊሶች ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ሞክረው ሳይሳካላቸው ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይግባኝ ወረቀቱን በእስር ቤት ሀላፊዎች ተነጠቀ

ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሽብር ወንጀል ተከሶ 18 ዓመታት የግፍ እስር የተፈረደበት ታዋቂው  ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማቅረብ ተገኝቶ ነበር። እስክንድር  ይግባኝ ለማለት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ቢሆንም፣ የይግባኙን ሰነድና ለፍርድ ቤት ሊያቀርበው ያዘጋጀውን የወረቀት ማስታወሺያዎች የቃሊቲ እስር ቤት ፖሊሶች ስለነጠቁት ሳይችል ቀርቷል። ጋዜጠኛ እስክንድር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለእስር ቤት ፖሊሶች ትእዛዝ ...

Read More »

መከላከያ የባንክ ባለቤት ሊሆን ነው

፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጲያ መግስት ለ2005 የበጀት ጥቅምት አመት ከያዛችው ዋንኛ የሰራ እቅዶች መካከል ወታደራዊ ባንክ ማቋቋም መሆኑን አስታውቆል።ሪፖርተር ከአዲስ አበባ እንደዘገበው መከላኪያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ባንኩን ለማቋቋም እየሰራ ነው። በተያዘውም አመት ተጠናቆ ሰራ ይጀምራል ብሏል።የመከላኪያ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ባቀረበው የስራ ክንውንና ዕቅድ ሪፖርት ላይ ይፋ የሆነው ወታደራዊ ባንክ ግንባታ በዋነኝነት ወታደራዊ  ቁልፍ ስልጣኖችን በእጁ ...

Read More »

እነ አቶ በቀለ ገርባ ጥፋተኛ ተባሉ

ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዩጵያ መንግስት አሸባሪ ሲል ክስ የመሰረተባቸው የመድረክ ስራ አስፈጽሚና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውጭ ቋንቋ መምህር አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች 8 ሰወች በተከሰሱበት አሽባሪነት ክስ ጥፋተኛ ተባሉ። ከሁለት አመት በፊት የፊደራል አቃቢ ህግ አሽባሪ ሲል ክስ የመሰረተባቸው አቶ በቀ ለገርባ እና አቶ አልባማ ሌሊሳ ኦፍዴንና ኦህኮን ሽፋን በማድረግ ለኦነግ እንዲሰሩ ወጣቶችን መልምለው ...

Read More »

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በስቃይ ላይ መሆናቸው ተነገረ

፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዜሮ አንድ ከ 2000 በላይ አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ። የክፍለ ከተማው ፖሊሶች በነቂስ ወተው ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች የፈረሱበትን ዘመቻ ነዋሪውን በማሰርና በመደብደብ ጭምር አስፈጽመዋል። በተለምዶ ሀና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ጥዋት ሶስት ግሬደር ተሰማርቶ ባደረገው የማፍረስ ዘመቻ መስኪድና ቤተክርስትያን ጭምር ፈሮሶል ተብሎል። ኢሳት ...

Read More »

በደጋን ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች ታሰሩ አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ተከቧል

ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ ዞን በደጋን ወረዳ ከሳምንታት በፊት የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ አካባቢው ከትናንትጀምሮ እንደገና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በሁዋላ ከ100 በላይ ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል። ወጣቶችም አካባቢውን ለቀው ወደ ወደ ገጠር በብዛት መሰሰደዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከታሰሩት መካከል በከተማዋ ውስጥ በእድሜ አዛውንት የሆኑት የ90 አመቱ አቶ እንድሪስ ከማል ይገኙበታል። ኢሳት ...

Read More »

ተቃዋሚዎች በዘንድሮ ምርጫ መዳከም አሳይተዋል

ጥቅምት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የአካባቢና የአዲስአበባ ከተማ ምርጫ ተቃዋሚዎች እስካሁን ምንም ዓይነት ዝግጅት አለማድረጋቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ ምርጫ ቦርድ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ምርጫው የሚያካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በምርጫው ዕጩዎቻቸውን ለማስመዝገብ የቀራቸው ጊዜ ሶስት ወራት ብቻ ነው፡፡ ይህም ሆኖ እስካሁን ...

Read More »