.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ እየጨመረ ነው ተባለ

  ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት ሙስሊሙ ላነሳው ጥያቄ ተገቢውንና ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ የሀይል አማራጭ መጠቀሙ፣ በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰው በደል እየከፋ እንዲሄድ አድርጎታል። የአካባቢው ነዋሪዋች እንደተናገሩት  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ከምሴ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቤት ለቤት በመግባት ከ60 በላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በመያዝ አስረዋል። በተያዙት ወጣቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት እየጨመረ መምጣቱን ...

Read More »

በሀረር ከተማ ከ500 በላይ ሱቆች ይፈርሳሉ መባሉን ተከትሎ አለመረጋጋት መፈጠሩ ተሰማ

ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀረር ከተማ ሸዋ በር እየተባለ በሚጠራው  የገበያ ማእከል የሚገኙ ከ500 ያላነሱ ሱቆች ይፈርሳሉ በመባሉ በዛሬው እለት አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር ዘጋቢዎቻችን ከስፍራው ገልጸዋል። አብዛኞቹ ሱቆች ካለፉት 30 አመታት ጀምሮ በጉራጌ ተወላጆች የተያዙ ሲሆን፣ ክልሉ ነጋዴዎችን በማስወጣት ለአካባቢው ተወላጆች ለመስጠት  እንዳቀደ መነገሩን ተከትሎ ነው አለመረጋጋቱ የተፈጠረው። ተገቢው ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ሱቆችን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ...

Read More »

አንዲት እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች

ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሻሸመኔ ከተማ ሀይማኖት ደሳለኝ የተባለች የቤት እመቤት ከትናንት በስቲያ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተኛችበት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመጥረቢያ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘገበ። የእናትየውና የልጆቹ ምላሶች መቆረጣቸውን፣ አይናቸውም መውጣቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልፀዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት በዛሬው እለት ሟቾቹን የቀበሩ ሲሆን፣ ከቀብር በሁዋላም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። . የቤት ሰራተኛዋ ወንጀሉን በመፈጸም በኩል የመጀመሪያዋ ተጠርጣሪ ሆናለች።

Read More »

የአንድነት ፓርቲ ልሳን “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ በአገሪቱ በየትኛውም ማተሚያ ቤት እንዳትታም ታገደች

ህዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ  ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ህትመቷ ከታገደ በሁዋላ በቅርቡ ዳግም መታተም የጀመረችው ፍኖተ-ነፃነት  ከእንግዲህ በ አገሪቱ በሚገኝ በየትኛውም ማተሚያ ቤት እንዳትታተም  እገዳ ተጥሎባታል። ፓርቲው በወቅቱ አገራዊ ፖለቲካ ዙሪያ ነገ ህዝባዊ ስብሰባ የሚያካሂድ ሲሆን፤ በድርጅቲ ልሳን ላይ ስለተጣለው አዲስ እገዳ አስመልክቶ በስብሰባው ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። በዋናነት የነገው ስብሰባ የተጠራው  በአገሪቱ ...

Read More »

አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እየጎላ መምጣቱ እየተነገረ ነው

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እየጎላ መምጣቱ በሕወሐት ሰዎች ዝንድ ቅሬታ መቀስቀሱና በአንዳንዶችም ዝንድ ቁጣ ማስከተሉ እየተሰማ ነው አቶ በረከትም ከጀርባ ሆነው ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወጥተው የፊት መስመር ላይ በግልፅ መታየት ጀምረዋል። በጠ/ሚ/ር ኋ/ማርያም ደሳለኝ የተመራ የልዑካ ቡድን ወደ ኬንያ ናይሮቢ በተጓዘበት ወቅት የልዑኩ 2ኛ ሰው ...

Read More »

አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ የኢሕአዲግ አባላት ከሆኑት ዲፕሎማቶች ጋር ተወዛገቡ

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠባባቂ ሚኒስትር አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ የኢሕአዲግ አባላት ከሆኑት ዲፕሎማቶች ጋር መወዛገባቸውን የቅርብ ምንጮችን የጠቀሱ ዘገባዎች ይፋ አድርገዋል የውዝግቡ መነሻ የኢሕአዲግ አባላት ያልሆኑ ዲፕሎማቶች ለስራ በመታጨታቸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተጠባባቂ ሚንስትር  አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ ከምክትላቸው ከአቶ ነጋ ፀጋዬ ጋር በመሩት ሥብሰባ ላይ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ደረጃ የኢሕአዲግ አባላት ...

Read More »

አልበሽር ላይ የታቀደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን የሱዳን ባለሥልጣናት ይፋ አደረጉ

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄነራል ኦማር ሐሰን አልበሽር ላይ የታቀደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን የሱዳን ባለሥልጣናት ይፋ አደረጉ ። የሱዳኑ የቀድሞ የፀጥታ  ሃላፊ ሣላህ ጋሆሽን ጨምሮ 13 ሠዎች ከግልበጣው ሙከራ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ታውቋል። የሲዳን  የማስታውቂያ ሚኒስትር አሕመድ ቢላል ኦስማን ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት ግልበጣው የታቀደው ላለፈው ሐሙስ እንደነበር አመልክተዋል ከሳምንት በኋላ ትናንት ...

Read More »

የብፁእ አቡነ ጴጥሮስ ታሪካዊ ሃውልት ተነስቶ ተመልሶ ይተካል የሚለውን ለመቀበል እንደሚቸገር ዲያቆን ዳንኤል ገለጸ

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከፒያሳ ተነስቶ፤ በመርካቶ በኩል አቋርጦ አብነት በታች የሚገኘው የኮካ ኮላ ፋብሪካ ጋር ይደርሳል ተብሎ የታሰበው የመጀመሪያው የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ፣ በአጼ ኃይለ-ስላሴ ዘመነ መንግስት የተተከለውን የብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ለዘመናት ከነበረበት ስፍራ በቅርቡ እንደሚነሳ የአዲስ አበባ መስተዳድር አስታውቋል። ምንም እንኳን አሁን በይፋ ባይገለጽም የደብረ-ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው የአጼ ምኒልክ ...

Read More »

በቤት ውዝግብ የተነሳ በሀረር አንድ አዛውንት ራሳቸውን ሰቅለው ገደሉ

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ድርጊቱ የተፈጸመው ትናንት ህዳር 13 2012 ዓም ነው። በተለምዶ ጀጎል እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ለረጅም ጊዜ በቀበሌ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የጥበቃ ሰራተኛው ባሻ ስዩም ተፈራ ባለፈው ዓመት ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ የቀበሌው ሹማምንት ይጠየቁዋቸዋል። ባሻ ስዩምም ዘመኔን በሙሉ የኖርኩበትን ቤት ትቼ መውደቂያ ሳይኖረኝ አልወጣም በማለት መልስ ሰጥተዋል። የክልሉ ባለስልጣናትም  በቅርቡ ቤታቸውን ብቻ ...

Read More »

በኦማር ሀሰን አልበሽር መንግስት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ ከሸፈ።

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሱዳኑን የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ ሊያደርጉ የነበሩ የቀድሞው የ አገሪቱ የደህንነት ሀላፊ ሳላህ ጎሽ እና  ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቢሲ ዘገበ። የ ዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ሀሙስ ማርፈጃውን    ታንኮችና ታጣቂዎችን የጫኑ የጦር ተሽከርካሪዎች የካርቱምን ጎዳና አጨናንቀዋት ውለዋል። ሱዳናውያን እያሻቀበ የመጣውን የኑሮ ውድነት በመቃወምና አስተዳደራዊ ለውጥ በመፈለግ በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የዜና አውታሩ ...

Read More »