.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰ ነው ተባለ

ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፓርላማ የሰጠው ተጨማሪ የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ሕገመንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 75 ለአንድ ጠ/ሚኒስትር ብቻ ዕውቅና እንደሚሰጥ ያስታወሱት ባለሙያዎቹ በዚሁ አንቀጽ 75(1)ለ ላይ የተመለከተው ጠ/ሚኒስትሩ በማይኖርበት ጊዜ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ተክቶት ይሰራል የሚለው ንኡስ አንቀጽ አንድ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ብቻ  እንደሚኖር የሚያሳይ ነው ይላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል ...

Read More »

በአየር መንገድ ውስጥ በጉልበት ስራ ላይ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች በኢህዴግ ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ሊተኩ ነው

ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የ816 ሚሊዮን ብር የልማት ድጋፍ አገኘች

ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የድጋፍ ስምምነቱን የፈረሙት  የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሱፊያን አህመድና የአውሮፓ ኅብረት የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተርና የአፍሪካ ካሪቢያን ፓስፊክ አስተባባሪ ፍራንሲስካ ሞስካ ናቸው። ድጋፉ የወጪ ምርቶችና በተመረጡ ኢንቨስትመንት መስኮች  በቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣ ጨርቃጨርቅ ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያና መድኃኒት ፋብሪካዎችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ፣ በልምድና ክህሎት እንዲሁም የገበያ ልማትን በማጠናከር ተወዳዳሪነታቸውን ለማጠናከር እንዲሁም  በቢዝነስ ፣በሥራ ...

Read More »

የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው የስልጣን ብወዛ መቀጠሉ ተዘገበ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህም መሰረት የአዳማ ከተማ ወይንም የናዝሪት ከተማ ከንቲባ ተነስተው በምትካቸው ሌላ ሰው መሾሙን ጉለሌ ፖስት የተባለው ድረ ገጽ ዘግቧል። እርምጃው የኦህዴድን መካከለኛ አመራር የመጥረግ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። ከሩብ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት አዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጉታ ላንቼሮ በድንገት ተነስተው በምትካቻቸው የኳሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ባካር ሻሊ እንደተኰቸውም ተመልክቷል። ባለፉት ሶስት ወራት በሙስናና ...

Read More »

ሆላንድ ካር በኪሳራ ለመዘጋት የበቃው በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ባለመገኘቱ መሆኑ ተነገረ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ መኪና በመገጣጠም የመጀመሪያው በመኋን ሲሰራ የቆየው ሆላንድ ካር በኪሳራ ለመዘጋት የበቃው በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ባለመገኘቱ መሆኑን የኩባንያውን ባለቤት የጠቀሱ ዘገባዎች አመልክተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ሳምንታዊው የቢዝነስ ጋዜጣ ካፒታል እንደዘገበው ለኩባንያው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። የኋላንድ ካር ባለድርሻና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ ለካፒታል ጋዜጣ ...

Read More »

በጉዲፈቻ ወደ ዴንማርክ የመጣች ህጻን ለከፍተኛ የስነ አዕምሮ ችግር መዳረጎን ከዴንማርክ የደረሰን ዘገባ አመለከተ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዛሬአራት አመት ከወላጅ እናቷና አባቷ ተረክበው ህጻኗን ከወንድሟ ጋር የወሰዳት የዴንማር ሰዎች ህጻኗ ለቤተሰቦቿ ያላትን ናፍቆት በየአጋጣሚው በመግለጽ እናቷ ጋር እየዲወስዷት በመጠየቅና ያልተለመደ በሀሪእያሳየች ደስታ በማጣቷ ለህጻናት ማሳደጊያ እንደሰጧት የኢሳት ምንጮች ከዴንማርክ ገልጣለች:: ከዴንማርክ የደረሰን ይሀው መረጃ እንደሚያመለክተው የህጻኗ ማእሾ ታሪክ በዴንማርክ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ቤተሰቦቿን ያነጋገረና የህጻኗን ወደ ሀገር ቤት ...

Read More »

በናዝሬት በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 4 ከንቲባዎች ተቀያየሩ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በተደረገ ግምገማ ላለፉት አራት ወራት በስልጣን ላይ ቆይተው የነበሩት የናዝሬት ወይም የአዳማ ዋና ከንቲባ እና ከእኝሁ ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አላቻው የተባሉት የከተማዋ የኦህዴድ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርጓል። ገምጋሚዎቹ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት የነበሩ ሲሆን ግምገማውም በመልካም አስተዳዳር፣ በከተሞች እድገት፣ በኪራይ ሰብሳቢነትና በልማት ሰራዊት አደረጃጃት ላይ ያተኮረ ነበር። የከተማው ከንቲባ የነበሩት ...

Read More »

መንግስት በመላ አገሪቱ ሙስሊሞችን እያስገደደ ለተቃውሞ ሰልፍ ሊያስወጣ ነው

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙና መንግስት በሙስሊሙ ላይ በሚፈጽመው ኢሰብአዊ  ድርጊት የተነሳ ተቃውሞ ያስነሳሉ በተባሉ አካባቢዎች በሙሉ ፣ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ይደረጋሉ። አብዛኛው ህዝብ ተገዶ እንዲወጣ፣ የድርጅት አባላት ከፍተኛ ተልእኮ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሎአል። በዛሬው እለትም በቅርቡ የመንግስት ታጣቂዎች 4 ሰዎችን በገደሉበት ገርባ እና ደጋን መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተደርገዋል። የሰልፉ ...

Read More »

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ላለመውሰድ ወሰኑ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ2005 ዓ.ም ለሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማና የአካባቢ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፓርቲዎች ጋር ለመነጋገር በአዳማ ከተማ ምርጫ ቦርድ በጠራው ስብሰባ ፒቲሽን የተፈራረሙት የ34 ፓርቲዎች ህብረት፤ የምርጫ ችግሮች ሳይፈቱ  የመወዳደሪያ ምልክታቸውን እንደማይወስዱ በአንድ ድምጽ መወሰናቸው ታወቀ፡፡ 34ቱ ፓርቲዎች  የምርጫ ምልክት ላለመውሰድ የወሰኑት ፤ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በመላው  ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ...

Read More »

የብር ዋጋ እየወደቀ ነው ተባለ

ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ በ17 በመቶ ጨምሮ በ16.35 ብር እንዲመነዘር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መወሰኑ ይፋ ከተደረገበት መስከረም 2003 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት፣ የብር ምንዛሪ አቅም እየቀነሰ ከ10 በመቶ በላይ ወርዷል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው። በኅዳር 2004 ዓ.ም. የየዕለቱ የውጭ ምንዛሪ ዋጋን በሚያመለክተው መረጃ መሠረት የአንድ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 17 ብር ...

Read More »