.የኢሳት አማርኛ ዜና

የቻይና ጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለመደገፍና በትብብር ለመስራት ይፈልጋል ተባለ

ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ስምዖን በሚስተር ዡ ሾሼን የተመራ የጋዜጠኞች ልዑካን ቡድንን አነጋግረዋል።  የመላው ቻይና ጋዜጠኞች ማህበር ዋና ፀሐፊ ሚስተር ዝሁ ሾቼን የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለመደገፍና የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ቻይና የረጅም ዓመታት የዳበረ ልምድና ተሞክሮ ያላት አገር መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያ ከቻይና ...

Read More »

ከፍተኛ ሙስና ፈጽመዋል የተባሉት ግለሰብ የኦሮምያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

ህዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ77 ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ፍቅሩ አያና ከምክር ቤት አባላቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም፣ ከፍተኛ አመራሮች ስለፈለጉዋቸው ብቻ እንዲሾሙ መደረጉን የኦህዴድ ምንጮች ገልጸዋል። የምክር ቤት አባላት በአቶ ፍቅሩ ላይ ካቀረቡዋቸው የመቃወሚያ ሀሳቦች መካከል ግለሰቡ በሙስና የተዘፈቁ ናቸው፣ በዞናቸው ዳኛ ...

Read More »

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ እንደገና ተቀሰቀሰ

ህዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ ቀርቦበት የነበረው ክስ እንደገነ ተቀሰቀሰ፤ ትላንት ሃሙስ ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ወደ ጋዜጣው ቢሮ የፍርድ ቤት መጥሪያ ይዘው የመጡት የፖሊስ አባላት ጋዜጠኛ ተመስገን ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑ ተነግሯቸው ተመልሰዋል ። ዓርብ ህዳር 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰሃት ...

Read More »

ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የሚኒስትር መ/ቤቶች የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች በደሞዝ ልዩነት ቅሬታ አሰሙ

ህዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ሁላችንም የህዝብ ግንኙነት ሠራተኞች ብንሆንም ጥቂት ሠራተኞች በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤት ስልጠና ስለተሰጣቸው ብቻ ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ ይደረግላቸዋል” በማለት ጋዜጣው ዘግቧል። በኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ለ13 ቀናት የሚሰጠውን ስልጠና የተከታተለ ባለሙያ ደሞዙ ከ2250 ብር ወደ 4150 ብር ከፍ እንደሚል የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ በአንድ ሙያ ላይ ለተሰማሩ ሠራተኞች የዚህን ያህል የደሞዝ ልዩነት መፈጠሩ ከፍተኛ የሞራል ...

Read More »

የሁለቱ ም/ጠቅላይ ሚኒሰትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ ታዋቂ የህግ ባለሙያ ገለጹ

ህዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሩዋንዳ ተቋቁሞ በነበረው የተበባሩት መንግስታት ድርጅት አለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቢ ህግ በመሆን ያገለገሉት እና በህግ የማስተማር ሙያ ላይ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጡት ዶ/ር ያቆብ ሀይለማርያም ለኢሳት እንደተናገሩት የሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም። ዶ/ር ያቆብ ” የህገመንግስቱ አንቀጽ 75 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተክቶ እንደሚሰራ ይደነግጋል  ...

Read More »

የድምጻችን ይሰማ የኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ

ህዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ሰላማዊ ተቃውሞ በመምራታቸው በሽብርተኝነት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የአመራር አባላት ዛሬ ልደታ በሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ለህዳር 27 ቀን 2005 ዓም የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል። የኮሚቴ አባላት ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጋ ለኢሳት እንደገለጡት የዛሬው ችሎት አቃቢ ህግ በጠበቆች በኩል ለቀረበው መቃወሚያ መልስ ለመስጠት ...

Read More »

የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልትን አንስቶ በሙዚየም ለማቆየት ኮሚቴ መቋቋሙ ተነገረ

ህዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ኢህአዴግ ልሳን የሆነው  ሬዲዮ ፋና እንደዘገበው የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት በግንባታው ስለሚነካ በጊዜያዊነት ይነሳና በጥንቃቄ በሙዚየም ይቀመጣል፣ ግንባታው ሲጠናቀቅም ወደ ስፍራው ይመለሳል። የዳግማዊ ምኒልክ ሃውልት ግን ከፕሮጀክቱ ጉድጓድ 15 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ አይነሳም ብሎአል። ይፈርሳል በሚል የሚናፈሰው ወሬም ከእውነት የራቀ  ነው በማለት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ...

Read More »

በመንግስት በተጠራ ሰልፍ የሀርቡ ህዝብ ሳይገኝ ቀረ

ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ የሀርቡ አካባቢ ሙስሊም ነዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የቀረበላቸውን የሰልፍ ጥሪ ባለመቀበል አንወጣም ማለታቸው ተገለጸ። ባለስልጣናቱ ተማሪዎቹን ከትምህርት ቤት በማስወጣት ሰልፍ እንዲያደርጉ ማድረጋቸውም ተዘግቧል። በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የቀረበው የሰልፍ ጥሪ ያልተገኘ ነዋሪ 50 ብር እንደሚቀጣ ቢገለጽም ህዝቡ ለማስጠንቀቂያው ቦታ ባለመስጠት በሰልፉ ሳይገኝ ቀርቷል። ከሬዲዮ ቢላል ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው የፌደራል ፖሊሶችና ያካባቢው ባለስልጣናት በየቤቱ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ ከተናጥል ወደ ማህበረሰባዊ ሊቀየር ይገባል ተባለ

ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ህዝብ በሚደርስበት የኢኮኖሚና የፖለቲካ በደል የሚያሰማውን የተናጥል ቁጣ በጋራ ማሳየት ይገባዋል ሲሉ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ገልጡ። የኢሀዲግ መንግስት ለፓርቲው እንጂ ለህዝብ ደንታ የለውምም ብለዋል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶቱን ቋጥሮ በማጉረምረም ላይ የሚገኝ ነው ፤ ቁጣውም ቢኋን በተናጠል የሚገለጽ ...

Read More »

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የተጠበቁ የስልጣን መሸጋሸጎችን አደረጉ

ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ይፋ ባደረጉት ሹመት 2 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን እና ሁለት ሚኒስትሮችን ብቻ በመሾም አቶ መለስ የመሰረቱትን ካቢኔ ይዘው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።  አስቀድሞ እንደተጠበቀው የኦህዴዱ አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትር በመሆን የአቶ ጁነዲን ሳዶን ቦታ ተክተዋል። የህወሀቱ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ደግሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ...

Read More »