.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ ፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ::

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህረሰብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ ፡ እስርና እንግልት እንዲያቆም ለመጠየቅ ያለመ የፊርማ ማሰባሰብ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቀ:: የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ ገብቶል በማለት ያነሱት ተቃውሞ አመት ማስቆጠሩን ያስታወሰው የፊርማ ማሰባሰብ መግለጫ በአሰሳ አርሲና በገርባ በመንግስት ታጣቂዎች 7 ሰዎች መገደላቸውን ፡በረካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ሌሎች መሰደዳቸውን በመግለጽ ...

Read More »

በቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ዕርቅን ለመፍጠር በሚካሄደው ውይይት ላይ ለመገኘት ከአዲስ አበባ የተወከሉት አባቶች አሜሪካ ገቡ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጭ የሚገኙ አባቶችና ከሐገር ቤት የመጡት ልዑካን በትናንትናው ዕለት ዳላስ ቴክሳስ ሲደርሱ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት እንዲያመጡ የተማፅኖ ፊርማዎ እየተሰበሰበ ይገኛል። በውጭ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ መልከ ፀደቅ የሚመራው ልዑካን ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ከካናዳና አውሮፓ ትናንት ዳልስ ገብቷል። ከብፁዕ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊም የጀመሩት ሰላማዊ ትግል ከዳር እንዲደርስ በስደት ላይየኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የመምህራን የትግል አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን አስታወቀ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው በደል በሌላውህብረተሰብ ላይም እየተፈጸመ መሆኑንም ገለጸ:: የመምህራን ማህበሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀውበሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ መንግስት እያደረሰ ያለው ግድያ፡ እስራትና በደልበሌላው የህብረተሰብ ክፍልና ቡድን ላይ ሲደርስ የቆየና እየደረሰ ያለው ግፍአካል በመሆኑ በስደት ያለውን መምህራን የትግል አጋርነት ያስፈልጋል ሌላውምየህብረተሰብ ክፍል የትግሉ አጋር ሊሆን ይገባል ሲል ጥሪ አስተላልፋለሁ:: በተለያዩ ወቅቶች አንድ ላይ ሆነን ባለመነሳታችን የከሸፉትን የትግልእንቅስቃሴዎች ልናስታውስ ይገባል ያለው የመምህራን ማህበሩ መግለጫለስኬት በአንድነት ሆነን ልንነሳና ልንታገል ይገባል ብሏል:: በዘር ምንጫቸውና በቋንቋቸው ተነቅሰው ቤታቸው በብልዶዘር የፈረሰንብረታቸው የተዘረፈና ከኖሩበት ቀዬ የተባረሩ ኢትዮጵያውያኖችን ያወሳውመግለጫው በነጻ ሚድያ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው የአሸባሪነት ክስናየተወሰደው እርምጃንም በማስታወስ በገዢው ፓርቲ ያልተበደለ የህብረተሰብክፍል የለም ካለ በኋላ በጋራ ልንታገለው ይገባል ሲል አስታውቋል:: የመምህር የኔሰው ገብሬን የትግል ቆራጥነትና መስዋዕትነት በመግለጽመስዋዕትነቱ መና አልቀረም ያለው በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ መግለጫ ህዝባዊ አመጽ ደግሞ መስዋዕትነቱም ውጤቱምዘላለማዊ ነው ሲል የጋራ እንነሳ መልዕቱን አጠናቋል::

Read More »

መንግስት የህዝብን ብሶት አልሰማ ብሎአል ሲሉ ፕሮፌሰር በፈቃዱ ደግፌ ተናገሩ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የኢኮኖሚክ ባለሙያ የሆኑት ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት የህዝብን ብሶት አልሰማ በማለቱ አንድ ቀን ያልጠበቀው አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠርበት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ” ህዝቡ የሚሄድበት ቦታ አጥቷል፣ ብሶታል” ያሉት ፕ/ር በፈቃዱ ከአረብ አብዮት የምንማረው ህዝብ መሪ ሳያስፈልገው በብሶቱ ብቻ ሆ ብሎ ሊነሳ የሚችል መሆኑን ነው ሲሉ ገልጸዋል። በኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ...

Read More »

የለገጣፎ/ለገዳዲ ነዋሪዎች አዲሱን ከንቲባ አንቀበልም አሉ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከመሬት ዝርፊያ ጋር በተያያዘ የከተማው ነዋሪዎች ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ በቅርቡ ከንቲባውን አቶ መገርሳ ገለታን ጨምሮ 5 የካቢኔ አባላትን ከስልጣን ያወረደው መንግስት፣ ከአካባቢው ህዝብ ያልተመረጠ አዲስ ከንቲባ በመሾም ለህዝቡ ለማስተዋወቅ የጠራው ስብስባ በተቃውሞ እንዲበተን ተደርጓል። ህዳር 21 ቀን 2005 ዓም ከፍተኛ የኦህዴድ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቀነአ ኩማ የለገጣፎ ለገዳዲን ህዝብ በመሰብሰብ አዲስ ...

Read More »

ነጋዴዎች አዲስ ራእይ መጽሄትን እንዲገዙ እየተገደዱ ነው

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነጋዴዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ፣ አንድ ነጋዴ በ100 ብር ቢያንስ ሁለት የአዲስ ራእይ መጽሄትን መግዛት ግድ ይለዋል። ይህን መጽሄት ለመግዛት ፈቃደኛ ካልሆ ጸረ ልማትና ጸረ ህገመንግስት ተደርጎ ይቆጠራል። መጽሀፉን የሚሸጡት የኢህአዴግ አባላት ሲሆኑ ፣ አንድ አባል በነፍስ ወከፍ እስከ 50 አዲስ ራእይ መጽሄቶችን መሸጥ ይጠበቅበታል። ኢሳት ከመንግስት በኩል ማረጋጋጥ ባይቻልም ስለመለስ ዜናዊ ማንነት ...

Read More »

በጅማ ዩኒቨርስቲ በተነሳው ተቃውሞ የታሰሩት ተማሪዎች ቁጥር ከ100 በላይ መድረሱን የፖሊስ ምንጮች ገለጹ

ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ፖሊሶች ለኢሳት እንደገለጡት በእስር ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ቁጥር 115 ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት ትናንት ተለቀዋል። 2 ተማሪዎች ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ጠቁመዋል። መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ መሆኑን የገለጡት ፖሊሶች፣ ትምህርት አንጀምርም ያሉትን ተማሪዎች ከሙስሊም እንቅስቃሴና ከተቃዋሚዎች ጋር በማያያዝ ለመክሰስ መታቀዱን ገልጸዋል። ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ...

Read More »

መድረክ በቅርቡ የተደረገውን የ3ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል አወገዘ

ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራሊስት አንድነት መድረክ በቅርቡ የተደረገውን  የ3ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል አወገዘ። መድረክ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ ሹመት የህገመንግስቱን ሁለት አንቀጸች የጣሰ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡ 34ቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህገመንግስቱ ተጥሶ 3 ም ክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች መሾማቸውን በማውገዝ ጉዳዩን ወደ ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት መፍረስ ተቃወመ

ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ማንኛውም ልማት ወጪን ቆጣቢ ሆኖ መሰራት እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም በዋጋ ሊተመኑ የማኢችሉ ቅርሶችን በማጥፋት ግን ወጪን ለመቀነስ ማሰብ የእብደት አስተሳሰብ ነው ብሎአል። የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌታሁን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ  ኢህአዴግ ከፍ ብሎ ለመታየት ባለው ፍላጎት የተነሳ ከዚህ በፊት የተሰሩትን ስራዎች ሁሉ ለማሳነስ እንደሚሞክር ገልጠው፣ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ...

Read More »

በጥንቁር አንበሳ የካንሰር ተጠቂው ቁጥር ከሆስፒታሉ አቅም በላይ ሆኗል ተባለ

ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በካንሰር በሽታ ተጠቅተው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሄዱ ህሙማን ለኢሳት እንደገለጹት ሆስፒታሉ ለካንሰር ህመምተኞች ያዘጋጀው አልጋ እና ህክምና የሚሰጡት ባለሙያዎች ቁጥር ከበሽተኛው ቁጥር ጋር ሊጣጣም ባለማቻሉ በሽተኞች ተገቢውን ህክምና ለማግኘት አልቻሉም። በጥቁር አንበሳ ለካንሰር በሽተኞች ተብሎ የተዘጋጀው አልጋ ቁጥር አነስተኛ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በየአመቱ ከ200 ሺ በላይ አዳዲስ የካንሰር ተጠቂዎች እንዳሉ መረጃዎች ...

Read More »