ሜጀር ጄነራል አብርሀ በኦጋዴን ጦርነት አትራፊ ናቸው ተባለ በኦጋዴን ደገሀቡር ውስጥ በመንግስት ወታደሮችና በኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ተዋጊዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከሁለቱም ወገን 32 ሰዎች መገደላቸው ሲገለጽ፤ ጦርነቱን የሚያቀጣጥሉት ከአካባቢው ከሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ ትርፍ የሚያጋብሱ የምስራቅ እዝ የጦር አዛዥ ጄኔራል አብርሀ ወልደማሪያም እና የክልሉ ፕሬዚዳንት ናቸው ሲሉ የኦብነግ አመራር አባል አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት ገለጹ። በጅጅጋ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ በ2003 ዓም ብቻ 100 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተዘርፎ ወደ ውጭ ባንኮች መግባቱ ታወቀ
ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጥናቱን ይፋ ያደረገው አለማቀፍ እውቅና ያለው ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የተባለው ተቋም ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2003 ዓም ብቻ ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ 5 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን 400 ሺ ዶላር ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ወደ 100 ቢሊዮን ብር ነው። ገንዘቡ የተዘረፈው በአብዛኛው በሙስ እና በታክስ ማጭበርበር ...
Read More »አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢነት ተነሱ
ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ ሙሀመድ ከሳውዲ አረብያ መንግስት 50 ሺ ብር እና ቅዱስ ቁራን መጽሀፎችን ተቀብለዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ፣ በአቶ ጁነዲን ሳዶ ላይ የሚወሰደው እርምጃ በርትቶ አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የቦርድ ሰብሳቢነት እንዲነሱ ተደርጓል። አቶ ጁነዲን ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትርነታቸው ከተነሱ እንዲሁም በኦህዴድ ውስጥ ተራ አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ከተወሰነ በሁዋላ ነው፣ የአዲስ አበባ ...
Read More »በአዲስ አበባ የሚታየው የመጓጓዣ ችግር እንደቀጠለ ነው
ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በከተማው ውስጥ በሚታየው የትራንስፖርት ችግር ተማሪዎችም ሆነ የመንግስት ሰራተኞች በሰአቱ ትምህርትቤታቸውና ስራ ቦታቸው ለመገኘት አልቻሉም። በተለይ ከጧቱ 1 ሰዓት ተኩል እስከ 2 ሰዓት ተኩል እንዲሁም ከ ሰአት በሁዋላ ከ11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በአራት ኪሎ፣ ሜክሲኮ፣ ሀያሑለት፣ ፒያሳ፣ መርካቶና ቦሌ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የትራንሰፖርት ችግር ይከሰታል። በቅርቡ ግንባታው የሚጀመረው የባቡር መስመር ዝርጋት ችግሩን ...
Read More »የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቶ ሀይለማርያም ከኤርትራ ጋር ስለሚደረገው እግርኳስ ጫወታ የተናገሩትን ቆርጦ አቀረበ
ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስቱ ቴሌቪዥን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኤርትራ ጋር የእግር ኳስ ጨዋታ በአስመራ ለማካሄድ ችግር የለብንም በማለት የተናገሩት መንግስት ቀደም ብሎ ጨዋታው በገለልተኛ አገር እንዲካሄድ ከጠየቀው ጋር የሚጋጭ መሆኑን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወሳል። ኢቲቪ የአቶ ሀይለማርያምን ቃለምልልስ በአማርኛ ተርጉሞ ያቀረበ ሲሆን፣ የእግር ኳስ ጫወታውን በተመለከተ ያለውን ክፍል ቆርጦታል። ኢቲቪ ቃለምልልሱን ቆርጦ ማቅረቡ የኢሳትን ዘገባ ለማስተባበል ተብሎ ይሁን ...
Read More »የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. አባቶች ድርድር ላይ ያወዛገቡት ደብዳቤዎች እየወጡ ነው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በዳላስ ቴክሳስ የተካሄደው ውይይት ለጊዜው ባለመስማማትና ለሌላ ውይይት ቀጠሮ ተይዞ ቢጠናቀቅም፤ የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ የውዝግቡ መነሻ የነበሩት ሰነዶች ለኢሳት ደርሰዋል። በቤተክርስቲያኒቷ አባቶች መካከል አንዱ የልዩነቱ መነሻ የሆነው የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ የጻፉት ደብዳቤ መሆኑ ታውቋል። የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ታምራት ላይኔ ፓትሪያርኩ እንዲነሱ ደብዳቤ መጻፋቸውን አምነው ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ መናገራቸውን ዊኪሊክስ ከሁለት አመት ...
Read More »በጅጅጋ የሆቴል ባለቤቶች አሻበሪዎችን ታስድራላችሁ በሚል እየተቀጡ ነው
ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጅጅጋ ወኪል የሆቴል ባለንብረቶችን አነጋግሮ እንደዘገበው በክልሉ የተቋቋመው እና በከፍተኛ ደረጃ የሚፈራው ልዩ ሚሊሺያ የሆቴሎች ባለቤቶችን እያስገደዱ ገንዘብ ይዘርፋሉ። ሚሊሻዎቹ የሆቴል ባለቤቶችን የሚዘርፉት የኦጋዴን አማጽያንን ያለበቂ ፍተሻና ምዘገባ በሆቴላችሁ ታሳድራላችሁ ፣ በቂ የፍተሻ ሰራተኞችን አልመደባችሁም በማለት ነው። “በመጀመሪያ ሚሊሺያዎች፣ ፖሊሶችና ባለስልጣናቱ ሆቴሎች ውስጥ ገብተው ይቀመጣሉ፣ ከዚያም ይሀው መሳሪያ ይዘን ገብተናል ፣ ፍተሻችሁ ጠንካራ አይደለም ...
Read More »በዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ኢህአዴግ ስልጠና ሊሰጥ ነው
ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጡት በመጪው ሳምንት በሚጀመረው በዚህ የስልጠና መርሀግብር የሁለተኛ ደረጃ ፣ የመሰናዶ፣ የኮሌጅ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይሳተፋሉ። በመርሀ ግብሩ መሰረት ከነዚሁ የትምህርት ተቋማት የሚመረጡ ቁልፍ ተማሪዎች በቅድሚያ ስልጠና ከተሰጣቸው በሁዋላ፣ እነዚሁ ሰልጣኞች ተመልሰው በመሄድ ለተቀረው ተማሪ ስልጠና ይሰጣሉ። ስልጠናው የሚቆየው ለአንድ ሳምንት ሲሆን፣ የሚሰለጥኑበት ሁኔታም በአብዛኛው ኢህአዴግ ባለፉት 8 አመታት ስላስገኛው ድሎች፣ ...
Read More »የአዲስ አበባ ወጣቶች የቃሊቲ ጉብኝት ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ተባለ
ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው እሁድ ታህሳስ 7፣ 2005 ዓም አለአግባብ የታሰሩ የሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ መሪዎችን በቃሊቲ ተገኝተው ለመጠየቅ የወጠኑት እቅድ ጥሩ ምላሽ እያገኘ መምጣቱን አዘጋጆች ገልጸዋል። ማንኛውም የህገመንግስቱን የእምነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንዳለበት የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ወደ ቃሊቲ በመሄድ ድጋፉን እንዲያደርግ እንጠይቃለን የሚል መግለጫ ካወጡ በሁዋላ ጥሪው በማህበራዊ ድረገጾች ...
Read More »ከጅቡቲ ደረቅ ጭነት የጫኑ ከ100 በላይ መኪኖች አዋሽ አርባ ላይ ቆመዋል ተባለ
ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲሱ መልቲ ሞዳል ሲስተም መሰረት እቃዎችን ከጅቡቲ በመጫን ወደ መሀል አገር የገቡ ከ100 በላይ መኪኖች ውሳኔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ላለፉት 10 ቀናት አዋሽ አርባ ላይ መቆማቸውን ሾፌሮች ተናግረዋል። ጭነቱ የመንግስት መሆኑን የተናገሩት ሾፌሮች በሞጆ ደረቅ ወደብና በአዲስ አበባ ደረቅ ወደብ መራገፍ ቢኖርበትም ውሳኔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ እስካሁን ሊራገፍ አልቻለም። የመኪኖቹ ባለንብረቶች ለመንግስት ባለስልጣናት ችግሩን ...
Read More »