.የኢሳት አማርኛ ዜና

ትናንት በቃሊቲ እና በደሴ እስረኞች ተጎበኙ

ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ወጣቶች ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ በቃሊቲ እና በደሴ እስር ቤቶች ከእስረኞች ቤተሰቦች ውጭ አዳዲስ ተጠያቂዎችም መታየታቸውን አዘጋጆች ገልጸዋል። ወደ ቃሊቲ የተጓዘው ህዝብ እስረኞች የታሰሩበትን ቦታ ባለማወቁ ሲቸገር መታየቱን አዘጋጆች ገልጸዋል። ምንም እንኳ በቃሊቲ የጠበቁትን ያክል ህዝብ ባይገኝም፣ ለመነሻ በቂ መሆኑን አዘጋጆች ገልጸዋል። “ሁሉም ነገር ከዜሮ ነው የሚጀምረው” ያሉት አዘጋጆች ” የእሰረኞች ቤተሰቦች፣ በጠያቂዎች ...

Read More »

መሬት ተደርምሶ ከአራት ያለነሱ ቀን ሰራተኞች ሞቱ

ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ውሀና ፍሳሽ ተቋም ለኮንትራክተሮች ሰጥቶ ለፍሳሽ ማስወገጃ በተቆፈረው ከ 70 ደረጃ ወደ አፍንጮ በር በሚያስወጣው ጠባብ መንገድ ላይ በቁፋሮ ስራ ላይ የነበሩ የቀን ሰራተኞች ከ7 ሜትር ጥልቅት በላይ የሚቆፍሩት መሬት ተደርምሶ አራቱን ሰራተኞች እዛው እንደቀበራቸው የተናገሩት የስራ ባልደረቦቻቸው ሲሆኑ፣ ሁለቱ ሰራተኞች ግን የአካባቢው ወጣቶች ተሰባስበው ለህይወታቸው ሳይሳሱ በገመድ በመጎተት እና የተጫናቸውን ናዳ በቁፋሮ ...

Read More »

ሆርን ሬዲዮ በአረብሳት ላይ ስርጭት ጀመረ

ታህሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሆርን ቲቪ ማኔጅመንት በላከው መግለጫ በአረብሳት ሪዲዮ ላይ የሆርን ቲቪ ራዲዮ ከዛሬ ጀምሮ ይተላለፋል። አድማጮች በባድር 4 ወይም በአረብ ሳት በሚከተሉት ዝርዝሮች ጣቢያውን ሊያገኙት ይችላል ፍሪኮንሲ 11 ሺ 938 ፖላራይዜሽን ፣ ቨርቲካል ሲምቦል ሬት ፡ 27 ነጥብ 5 ኤፍ ሲ ፤ 3/4ኛ ነው።

Read More »

በጅጅጋ በዘራችን ብቻ የንግድ ድርጅቶቻችንን ተቀማን በማለት ነዋሪዎች ገለጹ

ታህሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ተወልደው ያደጉ  በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት በአማራ ክልል በመገኘት የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አክብረው በተመለሱ ማግስት የንግድ ድርጅቶቻችሁን አስረክቡ እንደተባሉ ገልጸዋል። ቀደም ብሎ ታይዋን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የልብስ እና የተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆችን ከፍተው ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት፣ መንግስት ሱቆቻቸውን እንዲያስረክቡ ያደረጋቸው ፣ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች የንግድ ድርጅቶችን ...

Read More »

በማረቃ ወረዳ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ተገደለ

ታህሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ማንነቱ ያልታወቀው ግለሰብ የተገደለው በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በሁዋላ ነው። ግለሰቡን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ በስም አልታወቀም። ይሁን እንጅ የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ የሚል ምክንያት መስጠቱን ለማወቅ ተችልኦል። የተርጫ ዞን የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር አለማየሁ ጦፉ ግድያ መፈጸሙን ባይሸሽጉም ፣ ዝርዝሩን ከስብሰባ እንደወጡ እንደሚሰጡ ቢገልጹም ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ላለፈው አንድ አመት የጁመዓን ጸሎት ተከትሎ  ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ተቃውሞ  ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። ኢትዮጵያውያኑ መንግስት ድምጻችን ይስማን፣ የታሰሩ መሪዎች ይለቀቁ፣ መንግስት የለም ወይ በማለት ድምጻቸውን አስምተዋል። ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ በተካሄደበት በዚህ ተቃውሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር መስጊድና በውጭ በመሆን ድምጻቸውን አሰምተዋል። በሴቶች መስገጂያ በኩል የጸጥታ ሀይሎች 11 የሚሆኑ ሴቶችን ይዘው ማሰራቸው ...

Read More »

ፌዴራል ፖሊስ አገሪቱን በስለላ ካሜራዎች ለማጥለቅለቅ አቅዷል

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፌዴራል ፖሊስ ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስአበባ ተክሎ ሥራ ላይ ያዋላቸው የስለላ ካሜራዎች (cctv ካሜራዎች) ውጤታማ በመሆናቸው ወደክልሎች ለማስፋፋት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ የፖሊስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስአበባ ዋናዋና መንገዶች ላይ ካሜራዎችን በመግጠም የመቆጣጠሪያ ክፍል በማቋቋም በመንገዶቹ ላይ የሚሰሩ ሕገወጥ ድርጊቶችንና የትራፊክ አደጋዎችን በአነስተኛ የፖሊስ ኃይል ያለብዙ ወጪና ድካም ...

Read More »

በመቀሌ ከተማ ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞርና መንገድ ዳር በመዘርጋት ሽጠው የሚተዳደሩ ወገኖች ስራቸውን እንዲያቆሙ ታዘዙ

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች”ህፃናትና ኣዛውንቶች ከታሕሳስ 5/2005ዓ/ም ጀምረው ስራቸውን እንዲያቆሙ የከተማው ኣስተዳደር ከፖሊስና ሚሊሻ ሓይሎች ጋር በመቀናጀት ኣስቁመዋቸዋል$ እነዚህ ወገኖች ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞር”መንገድ ዳር ተቀምጦው በመሸጥ የዕለት ገቢያቸው ንየሚያገኙ ሲሆኑ የከተማው ኣስተዳደር ጋዜጣና መፅሄት እንዳያዞሩና ኣንድ ቦታ ላይ ተቀምጠውም እንዳይሸጡ  ያዘዘ ሲሆን፣  ያላቸው መጽሄት እና ጋዜጣ ሽጠው እንዲጨርሱ የኣምስት ቀን ዕድል ሰጧቸዋል ...

Read More »

በማረሚያቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመነ

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መንግስታዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መኖራቸውን በይፋ አመነ፡፡ ኮሚሽኑ በባህርዳር ከተማ የተከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ተከትሎ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ላይ የቀረበ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በሕገመንግስቱ የተደነገጉና አገሪቱ ተቀብላ ያጸደቀቻቸውን ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች በሚቃረን መልኩ በአንዳንድ ማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በታራሚዎች ላይ እየተፈጸሙ መሆኑን ይፋ ...

Read More »

የጋምቤላ ጭፍጨፋ 9ኛ አመት ታስቦ ዋለ

  426 የአኝዋክ ብሄረሰብ ተወላጆች የተገደሉበት 9ኛው አመት የጋምቤላ ጭፍጨፋ ዛሬ በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል። በተለይም የአኝዋክ ብሄረሰብ ተወላጆች በብዛት በሚገኙበት የሜኒሶታ ግዛት መታሰቢያው በሀዘን ድባብ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር ማኝ ኛንግ ለኢሳት ገልጸዋል። ከ9 አመት በፊት፤ በታህሳስ 1996 ዓ.ም. በአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት እንደተገደሉ የሚጠረጠሩ ስምንት የመሀል አገር ሰዎችን ወይም ደገኞችን ሞት ለመበቀል በሚል ሰበብ፤ የመንግስት ወታደሮች የተማሩ አኝዋክ ብሄረሰብ ተወላጆችን ...

Read More »