.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአክሱም ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት በርካታ ተማሪዎች ተጎዱ

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዩኒቨርስቲው በተማሪዎች እና በአስተዳዳሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የተፈነከቱ ሲሆን የዩኒቨርስቲው መኪናዎች ተማሪዎች ባወረዱት የድንጋይ ናዳ ተሰባብረዋል። የመማሪያ ክፍሎች መስታውቶች እና አንዳንድ በግቢው ውስጥ የሚታዮ እቃዎችም ተሰባብረዋል። ተቃውሞው ባለፈው ቅዳሜ ጥር 25 የተነሳው ሁለተኛ ግጭት በምግብ መበከል ሲሆን ዩኒቨርስቲው ከትምህርት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ስራ ብዙ ጊዜ በማዋሉ እና የአስተዳደር ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በታሰሩት የሙስሊም ኮሚቴዎች ላይ የሠራውን ፊልም ነገ ያስመርቃል።

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ራሱን <<የጸረ-ሽብር ግብረ-ሀይል>>ብሎ የሚጠራው ገዥው ፓርቲ ያዋቀረው ወንጃይ  ቡድን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር በታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች  ዚሪያ ያዘጋጀውን ዶክመንተሪ ነገ ማክሰኞ ምሽት እንደሚለቅ ኢቲቪ አስታወቀ። <<ጂሀዳዊ ሀረካት>>በሚል ርዕስ የተቀናበረው ይህ ፊልም <<ቦኮ ሀራም በ ኢትዮጵያ>> በሚል ንኡስ ርዕስ  በሙስሊሞች የተጀመረው እንቅስቃሴ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ያለመ እንደሆነ በስፋት የሚተርክ ነው። የፊልሙ ማጠንጠኛ ...

Read More »

መድረክ የአሰራር ችግር የለበትም ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እና የመድረክ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን የተናገሩት ኢሳት የግንባሩን ማንፌስቶ መጽደቅን አስመልክቶ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው። ዶ/ር ነጋሶ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ ግንባሩ ያካሄደው ጉባኤ የተሳካ ነበር። በቅርቡ አቶ ቡልቻ ሚዴቅሳና ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መድረክን አስመልክቶ የተናገሩት ችግር በአሁኑ ጉበኤ ተነስቶ ተነጋግራችሁበታልን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ዶ/ር ነጋሶ ...

Read More »

በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት አደረጉ

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አርቲስት ታማኝ በየነ እንዲሁም ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በክብር እንግድነት በተገኙበት ጀኔቫ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ለኢሳት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ የሆነው ወጣት ጴጥሮስ አሸናፊ እንደገለጠው ዝግጅቱ ከታሰበው በላይ በስኬት መካሄዱን ገልጿል ( ) አርቲስት ታማኝ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ለኢሳት የሚያደርገውን ድጋፍ በስዊዘርላንድ ጀምሯል። ከአውሮፓ አገራት መካከል በስዊድን ...

Read More »

በገንዘብዎ ሳይሆን በጊዜዎ የሚገዙት ሎተሪ በኢሳት !

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን / ኢሳት / በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን፣ በድህረ ገጽ፣ በፌስ ቡክና በትዊተር የሚዲያ ዘርፎቹ  በወር ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ጎብኚ ያለው ነው። ይህ ከፍተኛ አድማጭና ተመልካች ያለው የሚዲያ ተቋም በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ተቀባይነት ጠብቆ ለመቆየት፤  ስራውን እያሳደገና ወደ ኢትዮጵያ የሚያድርገውንም የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ስርጭት አስተማማኝ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። በሚያስተላልፈው ፕሮግራምም የተለያየ የህብረተሰብ ክፍልን ፍላጎት ለማሟላት በየጊዜው ያልተቋረጠ ፕሮግራሞችን የማስፋፋት ስራም እያከናወነ ...

Read More »

መድረክ ለረጅም ጊዜ ሲያጓትተው የነበረውን ማንፌስቶ አጸደቀ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ ክርክር በታየበት የመድረክ ጉባኤ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት ማንፌስቶውንና መተዳደሪያ ደንቡን አጽድቀዋል። ባለ 25 ገጹ ማንፌስቶ ላለፉት ስድስት ወራት ሲዘጋጅ  የቆየ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ በፈጀ ክርክር ጸድቋል:፡፡ ላለፉት 4 አመታት ሲንከባለል የቆየውና የድርጅቶች የልዩነት ምንጭ ተደርጎ ይታይ የነበረው መተዳደሪያ ደንብም እንዲሁ ጸድቋል። “በጣም ደስ የሚል ኢትዮጵያዊ መድረክ ነበር፣ ቋንቋው፣ ...

Read More »

ኦህዴድ ለሶስት ቡድኖች መከፋፈሉ ታወቀ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት በአብዛኛው የኦሮሚያ ዞኖች በተለይም በምስራቅ ኦሮሚያና በአርሲ ዞኖች የሚገኙ የድርጅቱ አባላት ለ3 ተከፍለው እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው። የክፍፍሉ መንስኤዎች በድርጅቱ እምነት ማጣት፣ ሙስናና የግል ጥቅምን ማሳደድ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አመራሮቹ እርስ በርስ እየተባሉ ይገኛሉ ያሉት ምንጮች፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የድርጅቱ ህልውና ሊያከትም እንደሚችል ጠቁመዋል። በዞን ደረጃ የሚታየው መከፋፋል ...

Read More »

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ በትናንትናው እለት በደህንነት ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት 2ቱ ጓደኞቻቸው የት እንዳሉ ዩኒቨርስቲው እንዲያሳውቃቸው ጠይቀዋል። የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ከተማሪዎች ለቀረበው ጥያቄ ” ተማሪዎቹ በደህንነት ሀይሎች ተፈልገው የተወሰዱ በመሆኑ እኛ ምንም ማድረግ አንችልንም፣ ለወደፊቱም የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘው ከመጡ  አሳልፈን እንሰጣለን” በማለት መልስ መስጠታቸው ታውቋል። በሰላማዊ ...

Read More »

”የመለስ ወራሾች አገሪቷን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየከተቷት ነው” ሲል ጋዜጠኛተመስገን ደሳለኝ ገለጸ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ተመስገን ይህን ያለው፤  <<የመለስ ራዕይ በ አዲስ ታይምስ መጽሔት ተተገበረ>>በሚል  ርዕስ የአዲስ ታይምስን መዘጋት አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ማስታወሻ ነው። “ምንም ጥርጥር የለውም መለስ ዜናዊ ፍፁም አምባገነን ነበር፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ከአንድ ክፍለ ጦር በላይ የተለየ ሀሳብን እና ነፃ ሚዲያን  ይፈራ ነበር>> በማለት አስተያዬቱን መስጠት የጀመረው ተመስገን፤ << ወራሾቹም ...

Read More »

ሕዝቡ በምርጫ እንዳይሳተፍ ጥሪ ቀረበ

ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግ ሊያካሂደው ባሰበው የአካባቢ ምርጫ እንዳይሳተፍ 39ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ። ፓርቲዎቹ ህዝባዊ ጥሪውን ያቀረቡት ”ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ  አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ  ባወጡት መግለጫ ነው። የ ኢህአዴግ ምክር ቤት ጸሀፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ፓርቲዎቹ በምርጫ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን አስመልክቶ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ፦<<እነሱ ...

Read More »