የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የውስጥ ሽኩቻ መበራከት የተነሳ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት እንደተሳነው የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው። በህወሀት ውስጥ ሁለት ቡድኖች ድርጅቱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ መጀመራቸው ከተዘገባ ከወራት በሁዋላ ችግሩ ከመቃለል ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን አንድ የቀድሞ የህወሀት ነባር ታጋይ ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል። ነባር ታጋዩ፤ በአቶ ስብሀት ነጋ በኩል ባሉ ሰዎች ወደ ድርጅቱ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ታክሲ ውስጥ በ 1 ብር ከ 35 ሳንቲም ሳቢያ በተፈጠረ ጭቅጭቅ ረዳቱ በጥይት ተመታ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከትናንት በስቲያ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ኪዱ ገብረሥላሴ በተባለ የታክሲ ተሳፋሪና በረዳቱ መካከል በተፈጠረ የ1.35 ብር አለመግባባት ምክንያት ረዳቱ በጥይት ተመታ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ ድርጊቱ የተፈጸመው ቦሌ መድኃኔዓለም ከሚገኘው ካልዲስ ካፌ ፊት ለፊት ሲሆን፣ ተጠርጣሪው አቶ ኪዱ ገብረ ሥላሴ ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ ነጋ ንጉሡ የተባለው የታክሲው ረዳትም፤ ሃያት ሆስፒታል ለሕክምና ተወስዷል፡፡ ...
Read More »ፋሽስት ግራዚያኒን ለመቃወም ለሁለተኛ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተጠራ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ የኢጣልያ መንግስት ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ያስገነባው ሙዚየምና የመናፈሻ ስፍራን ለመቃወም በድጋሚ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተጠራ። እንደ ሰንደቅ ዘገባ የተቃውሞ ሰልፉን የጠሩት ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ ባለ ራዕይ የወጣቶች ማኅበር እና ሰማያዊ ፓርቲ ናቸው። ቀደም ሲል ሦስት በጎፈቃድ አባላት ያሉበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ...
Read More »ሁለት የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድራቸውን አቋርጠው ጠፉ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሀአሬጽ የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ እንደዘገበው ሁለቱ አትሌቶች የማራቶን ሩጫቸውን በማቋረጥ ነው ባለፈው አርብ ፣ ማርች 1፣ 2013 የጠፉት። ሜላት መኮንን እና ማህሌት ዘለቀ የተባሉ የ24 እና 25 አመት እድሜ ያላቸው አትሌቶች የጠፉት በደቡብ ቴላቪቭ ሲሆን፤ የ እስራኤል ፖሊስ አትሌቶቹ ሆን ብለው እንደጠፉ ገልጿል። ሁለቱም አትሌቶች ፓስፖርታቸውን እና ሌሎች እቃዎቻቸውን ሁሉ በመተው በሩጫ ...
Read More »ኢህአዴግ በርካታ የመረጃ ሰዎችን በሆቴል ቤት ሰራተኝነት ስም ቀጥሮ አሰማራ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ሻሂ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ውስጥ የ ኢህአዴግ መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወጣት ሴቶችን በማሰልጠን እና አንድ ለአምስት በመጠርነፍ መረጃ እንዲያቀርቡ እያሰማራ እንደሚገኝ ታውቋል። መንግስት ከሻሂ ቤቶችና ሆቴሎች ስራ አስኪያጆች ጋር በሚስጢር በመነጋገር ደሞዝ የሚከፍላቸውን አስተናጋጆች አሰማርቶ ከህዝቡ መረጃ እየሰበሰበ ነው። ቀደም ሲል መንግስት ሰዎችን በማስረግ ብቻ ...
Read More »ታዛቢዎች የቤተክህነቱ ” ጅሀዳዊ ሀረካት” ያሉት መጽሀፍ እየተሰራጨ ነው
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደት የሚገኙነትን አራተኛው ፓትርያርክ ጨምሮ በውጪ አገር ያሉ አባቶችን ስሕተት፣ ጥፋትና ዕርቀ ሰላሙን ማፍረስ የሚያትት እንዲሁም ፓትርያርኩ ከሥልጣን የወረዱት ተገደው ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ መሆኑን የሚያትት ባለ 52 ገጽ አነስተኛ መጽሐፍ ታትሞ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ደጀሰላም ዘግቧል። ይኸው በአቡነ ማቲያስ ዕለተ ሲመት ጀምሮ መሰራጨት የጀመረው መጽሐፍ በብዙዎች አባባል የቤተ ክህነቱ “ጂሐዳዊ ሐረካት” የተሰኘ ...
Read More »ወታደሮች በኦጋዴን የውሀ ጉድጋዶችን በመያዝ ህዝቡን እያሰቃዩት ነው ተባለ
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሰራዊቱ እና የሶማሊ ልዩ ምልሻ በጋራ ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የውሀ ጉድጓዶችን ተቆጣጥረው ህዝቡን ገንዘብ በማስከፈል እያሰቃዩት ነው። ድርጅቱ ለአለማቀፍ ድርጅቶች ባሰማው የድረሱልን ጥሪ ሰራዊቱ በአንድ ሰው እና በእንስሳ ቁጥር ልክ ገንዘብ እያስከፈለ ነው። አንድ ቤተሰብ ወደ ውሀ በወሰዳቸው ግመሎች፣ ፍየሎችና በጎች ልክ ለውሀው እንደሚከፍል ...
Read More »በኬንያ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ እየመሩ ነው
የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ ተቀናቃኛቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን በሰፊ ልዩነት እየመሩ ነው። እስካሁን በተደረገው ቆጠራ ሚስተር ኬንያታ 53 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው 42 በመቶ አግኝተዋል። የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን ሀላፊ እንደተናገሩት ውጤቱ ጊዜያዊ በመሆኑ፣ ህዝቡ በትእግስት እንዲጠብቅ መክረዋል። እስካሁን አንድ ሶስተኛው ድምጽ የተቆጠረ ሲሆን ኡሁሩ ኬንያታ በሰፊ ድምጽ እየመሩ ...
Read More »33 የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የመግባቢያ ሰነድ ፈረሙ
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲዎቹ የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት ባለፈው ቅዳሜ ነው። በፊርማ ስነስርአቱ ላይ የፓርቲዎቹ ጥምረት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ ” የተፈረመው ሰነድ የመጀመሪያ የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን ገልጠው፣ የኢህአዴግ የ21 አመታት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ኢትዮጵያን ለረሀብ፣ ለድህነት፣ ለስደት፣ ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ ለኢፍትሀዊነት፣ ለሙስና ዳርጓታል ብለዋል። የአዲሱ ስብስብ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በበኩላቸው በዚህ ታሪካዊ የአድዋ ቀን ...
Read More »የሰብዓዊ መብት ሊጉ የዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ፖለቲካዊና ዘረኝነት ላይ ያነጣጠረ ነው አለ።
የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የምሥራቅ አፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ሊግ በቅርቡ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ 10 የኦሮሞ ተወላጆች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ መደረጋቸውን አጥብቆ አወገዘ። የሰብዓዊ መብት ሊጉ ከትምርታቸው የታገዱትን ተማሪዎች ፎቶ አስደግፎ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገዱት የመጀመሪያ ሴሚስተር ፈተናቸውን አጠናቅቀው የሁለት ሳምንት እረፍት ወስደው ከተመለሱ በሁዋላ ነው። ሊጉ ከውስጥ የደረሱትን መረጃዎች ...
Read More »