.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዲስ አበባ ከሚገኙ 26 የትራፊክ መብራቶች አገልግሎት የሚሰጠው አንዱ ብቻ ነው

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከሚገኙ 26 የትራፊክ መብራቶች  ከአንዱ በስተቀር ሌሎቹ አለመሥራታቸው ፤  የትራፊክ መጨናነቅና የአደጋ መንስኤ መሆኑ ተዘገበ። እንደ አድማስ ዘገባ የመብራቶቹ አለመሥራት ከዚህም ባሻገር  በትራፊክ ፖሊሶች ላይ ከአቅም በላይ የሆነ የስራ ጫና ፈጥሯል፡፡    == አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠሩት የከተማዋ የትራፊክ መብራቶች ሲበላሹ ጥገና ስለማይደረግላቸው ለበለጠ ብልሽት እየተዳረጉ ከጥቅም ውጪ እንደሆኑ ...

Read More »

ከደሀው ህዝብ በግብር ስም የሚሰበሰው ገንዘብ ለልማት እንዲውል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ ጠየቁ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከአመት በፊት የጀመሩትን ተቃውሞ በመቀጠል በአርብ የጁማ ጸሎት ላይ መንግስት ከደሀው ህዝብ በግብርና በተለያዩ መዋጮች ስም የሰበሰበውን ከ313 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ አህባሽ የተባለውን ሀይማኖት ለማስፋፋት ማዋሉን አጥብቀው በመቃወም ገንዘቡ ለልማት እንዲውል ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የታሰሩት ይፈቱ፣ በአገራችን ሰላም አጣን፣ ኢቲቪ አሸባሪ፣ መንግስት ...

Read More »

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ በሙስና መጨማለቁን አንድ ጥናት አመለከተ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የመንገደኞች የይለፍ ማረጋገጫ አሰጣጥ እና የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ የአሰራር ሥርዓት በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨማለቀ መሆኑን ከፌዴራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የተገኘ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ በመምሪያው በይለፍ ማረጋገጫ አሰራር ስርዓት ላይ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ተብለው በጥናቱ ከቀረቡት ሁኔታዎች ውስጥ የመረጃ አያያዝና ...

Read More »

የመለስ ፋውንዴሽን ሰድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ግቢ ውስጥ ሊሰራ ነው

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀደም ብሎ ለወ/ሮ አዜብና ቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ቤት ግንባታ ተመርጦ የነበረው የስድስት ኪሎው የስብሰባ ማእከል ግቢ፣ አሁን ለመለስ ፋውንዴሽን ህንጻ ማሰሪያ ሊውል መሆኑን ምንጮች ገለጹ። ወ/ሮ አዜብ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ባለፈው ሀሙስ ስፍራውን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችም ከህንጻ ግንባታው ጋር በተያያዘ ሊፈርሱ ይችላሉ፡፡ በከፍተኛ ጥበቃ በስፍራው ላይ የተገኙት ወ/ሮ ...

Read More »

አዋሽ ወንዝ በጥቂት ወራት ውስጥ የሚሊዮኖችን ህይወት ለአደጋ አጋልጦ ከጥቅም ውጭ ሊሆን ይችላል ተባለ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉበርግ ትናንት ይዞት በወጣው አስደንጋጭ ዘገባ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው የበሰቃ ሀይቅ በመስኖ ስራዎች እና በተፈጥሮ እንቅስቃሴ ምክንያት ጨዋማነቱ በ15 እጥፍ በመጨመሩ በሰኔ ወር ዝናብ ከዘነበና  ሀይቁ ወደ አዋሽ ወንዝ መፍሰስ ከጀመረ ፣ ወንዙን ለመጨረሻ ጊዜ ከጥቅም ውጭ ያደርገዋል ሲል ጠቅሷል።. ስራ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ የአፈር መሸርሸርና በመሬት የውስጥ እንቅስቃሴ ምክንያት ጨዋማነቱ ...

Read More »

በአፋር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ልዩ ወረዳ መጠየቃቸውን የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ተቃወመ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዞን ሁለት ዋና ከተማ በሆነው አብአላ   የሚኖሩ 15 ሺ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ራሳችንን በራሳችን ለማስተዳደር ልዩ ወረዳ ይሰጠን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ አይደለም ሲሉ የአፋር ሰብአዊ  መብቶች ሃለፊ አቶ ገአስ አህመድ ገልጸዋል። አቶ ጋአስ በዱብቲ ከተማ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጆች ቢኖርም አንድም ቀን የወረዳ ጥያቄ አለማንሳታቸውን ገልጸው፣ ከመቀሌ በ45 ኪሎሜትር ...

Read More »

የግራዚያኒ ሀውልት እንዲሰራ ፈቃድ የሰጡት ከንቲባ እየተመረመሩ ነው

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሮም ደቡባዊ ግዛት የምትገኘው ቲቮሊ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ኢርኮሊ ቪሊ  የህዝብን ገንዘብ በአለም በወንጀለኛነቱ ለተፈረጀው ሮዶልፎ ግራዚያኒ ሀውልት ማሰሪያ በመጠቀማቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አንሳ የተባለው ድረገጽ ዘግቧል። ሀውልት እንዲቆም የተወሰነው አንድ ማንነቱ ላልታወቀ ወታደር ቢሆንም ፣ ከንቲባው ግን በኢትዮጵያ እና በሊቢያ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎችን ላካሄደው ግራዚያኒ እንዲሆን ማድረጉ ለምርመራ መጋበዙን ድረገጹ ጠቅሷል። ድረገጹ ...

Read More »

የፌደራል መንግስቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ላይ ስህተት መፈጸሙን ተናገሩ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለሳምንታት የመላውን ኢትዮጵያውያን ትኩረት በመሳብ መነጋገሪያ ሆነ የቆየው በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመው መፈናቀል በተመለከተ የፌደራል መንግስቱ ከረጅም ጊዜ ዝምታ በሁዋላ ትናንት በጠቅላይ ሚኒሰትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት አቋሙን ግልጽ አድርጓል። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው መፈናቀል በሙስና በተዘፈቁ የአካባቢው ባለስልጣናት መፈጸሙን ገልጸዋል። መንግስታቸው ማጣሪያ በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል። ...

Read More »

በቤቶች ጉዳይ አቶ ሀይለማርያም የሰጡት መልስ የፓርላማ አባላቱን አስቆጣ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትላንት የመንግስታቸውን የ2005 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከፓርላማ አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የ40 በ 60 የተባለው የቤቶች ልማት ፕሮጀክትን አስመልክቶ የሰጡት ምላሽ ባልተለመደ መልክ የኢህአዴግ የፓርላማ አባላትን ጉምጉምታ አስከተለ፡፡ 40 በ 60 የሚባለው የቤት ልማት ፕሮግራም ሕዝቡ በአንድ በኩል ቆጥቦ የቤት ባለቤት እንደሚሆን እየተነገረ በሌላ በኩል ...

Read More »

አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ መብት አፈና አወገዘ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሪድ ላንድስ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በ53ኛው የአፍሪካ የሰዎች እና የህዝቦች መብት ጉባኤ ላይ ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፕሬስ አፈና በዝርዝር አቅርቧል። አለማቀፍ ተሸላሚውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የተለያዩ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን፣ የኢንተርኔት ስርጭት እንዳይስፋፋ መደረጉን፣ መንግስት ከህዝቡ የሚሰበስበውን ገንዘብ የተለያዩ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማፈኛነት እንደሚያውለው፣ ሽብርተኝነት በመዋጋት ስም የሚወጡት ህጎች ፕሬሱን ...

Read More »