.የኢሳት አማርኛ ዜና

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአምስት ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸናፊ ሆነች

ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ ሻንጋይ ቻይና ላይ በተደረገው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአምስት ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር 14፡ደቂቃ ከ45ነጥብ 92 ሰከንድ በሆነ ሠዓት በመግባት አሸናፊ ሆነች። በዚሁ ውድድር እንደምታሸንፍ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ባለድል የሆነችው ታዋቂዋ አትሌት መሰረት ደፋር 14ደ ቂቃ፡47 ነጥብ 76 ሰከንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ኬንያዊቷ ...

Read More »

ከአፋር ጋድሌ ጋር በተያያዘ ባለስልጣናትን እና ፖሊሶችን ጨምሮ 14 ሰዎች ታሰሩ

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአፋር ጋድሌ ወታደራዊ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ  14 ሰዎች መታሰራቸውን፣ ከታሰሩት መካከልም፣ የቀበሌው ሊቀመንበር፣ የወረዳ ምክር ቤት አባል፣ አንድ ፖሊስ እና ሽማግሌዎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሎአል። አብዛኞቹ የተያዙት በፌደራል ፖሊሶች ሲሆን በቅርቡ 70 የሚሆኑ የአፋር ወጣቶች አፋር ጋድሌ የሚባለውን  የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኘውን ድርጅቶች መቀላቀላቸውን ተከትሎ ነው። ከታሰሩት መካከል የሩማይቶ ቀበሌ ሊቀመንበር ...

Read More »

አቶ መላኩ ፈንታ በአንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ብቻቸውን መታሰራቸውን ተናገሩ

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሙስና ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት የየኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር    አቶ መላኩ ፋንታ በእስር ቤት ውስጥ ልብቻቸው በአንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ ከመታሰራቸውም በላይ ለአንድ ቀን ብቻ ለ10 ደቂቃ እንዲናፈሱ እንደተፈቀደላቸው ተናግረዋል። ቀኑን ሙሉ በትንሽ ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ነው የምውለው ያሉት አቶ መላኩ ፣ መንግስት ለሚያውቀው በሽታቸው የሚሆን መድሀኒትም ቢሆን ከጊዜ በሁዋላ ...

Read More »

በቤይሩት በቤት ሰራኝነት ተቀጥራ የምታገለግል አንዲት ኢትዮጵያዊ ወጣት፣ አሰሪዋን ሆን ብላ በፈላ ውሃና በእሳት አቃጥላለች በሚል በቁጥጥር ስር መዋሏን ደይሊ ስታር የተሰኘው ድረ ገጽ ዘገበ።

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚሁ የዜና ዘገባ መሰረት በሰሜን ቤይሩት ግዛት ማስቲታ ጀቢል በተሰኘ ስፍራ የምትኖረው የ70 ዓመቷ አረጋዊት ወ/ሮ ሳሚያ፣ ድንቅነሽ የተሰኘች የ24 ዓመት ዕድሜ ያላት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛዋ፣ ከነሃስ በተሰራ ቅርፃ ቅርጽ ጭንቅላቷን ከመታቻት በኋላ የፈላ ውሃ ፊቷ ላይና ደረቷ ላይ በማፍሰስ ጉዳት አድርሳባታለች። አደጋ የደረሰባት ግለሰብ ለህክምና በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል እንደተወሰደች የሚያትተው ይኸው ዘገባ፣ ...

Read More »

ከአዲስ አበባ 430 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ አናለማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር የሚገኙ ጡረተኞች በማኀበር ተደራጅተው ሲሰሩበት ከነበረው መሬት በድንገት መፈናቀላቸውን ገለጹ

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጡረተኞቹ የጎባና የአካባቢው ጡረተኞች ማኀበር በሚል ተደራጅተው በ1991 ዓ.ም፣ 200 ሄክታር መሬት ተረክበው ሲሰሩ እንደነበር በመሃል 75 ነጥብ 25 ሄክታር መሬት መነጠቃቸውን በአሁን ወቅት ደግሞ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው እያለሙ ያሉትን መሬት ሙሉ በሙሉ መነጠቃቸውን ገልጸዋል፡፡ መሬቱ ለ25 ዓመታት ተዋውለን የተረከብነው ነው ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በ30 ሄክታር መሬት ላይ ከ75 ሺ ብር በላይ ለትራክተር ...

Read More »

ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተፈናቃዮች አለመረጋጋታቸውን ተናገሩ

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሚያዝያ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈናቀሉ በኋላ በድርድር ወደ ተፈናቀሉበት ቤንሻንጉል ጉሙዝ  እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ  ተወላጆች ዳግም የመፈናቀል ስጋት አንዣቦብናል አሉ፡፡ የት ተወልድን እንዳደግን፣ የቀድሞ ሠፈራችንና ቀበሌያችንን በመመዝገብ ሂደት ላይ ያለው የዞኑ አስተዳድር ሚስጥራዊና ድብቅ የማፈናቀል ዘመቻውን ሊቀጥል እንደሚችል በተወሰነ መልኩ መገንዘብ ችለናል ያሉት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የሴባ ቀበሌ ኗሪ በሁኔታው ሁሉም ...

Read More »

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ከአንድ መቶ በላይ ተማሪዎች ተይዘው ታሰሩ

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሶስት ቀናት በፊት የተነሳው የተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ቀጥሎ የፌደራል ፖሊሶች አድማውን መርተዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን   ከ100 በላይ ተማሪዎች ወስደው በጋሞጎፋ ዞን ፖሊስ መመሪያ ግቢ ውስጥ ማጎራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የተለያዩ የትምህርትና አስተዳዳራዊ በደሎችን ያነሱት ተማሪዎች ትናንት ቀኑን ሙሉ በፖሊሶች ተከበው መዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። በዛሬው እለትም ተማሪዎቹ ትምህርት ያልጀመሩ ሲሆን፣ የታሰሩ ጓደኞቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ...

Read More »

የአብያታ ሐይቅ ህልውና ላይ አደጋ ተጋርጧል

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የመስኖ እርሻና የሶዳ አሽ ሥራዎች ለአብያታ ሐይቅ ህልውና አደጋ መሆናቸውን ምሁራን  ናቸው ያስጠነቀቁት በአንድ ወቅት በዝዋይ በሚገኙ የአበባ እርሻዎች ሳቢያ ለብክለትና ለከፍተኛ የውኃ መጠን መቀነስ ችግር ተዳርጎ የቆየው አብያታ ሐይቅ፣ በአሁኑ ወቅት በመስኖ እርሻዎችና ሶዳ አሽ በሚያመርተው ፋብሪካ ሳቢያ ለከፍተኛ አደጋ  ተጋልጧል። ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ከአንድ ትውልድ በላይ ላይዘልቅ እንደሚችል  ያስጠነቀቁት ...

Read More »

አርቲስት አበበች ደራራ አረፈች

ግንቦት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስታገለገል የቆየችው አበበች ደራራ ባደረባት ህመም ሳቢያ በእስራኤል ግንቦት 8 ፣ 20005 ዓም አርፋለች። ድምጸ መረዋዋ አበበች ደራራ ለበርካታ አመታት ከሽታዋ ጋር ስትታገል መቆየቷን በቅርብ የሚያውቁዋት ሰዎች ተናግረዋል። የአበበች ደራራ የቀብር ስነስርአት በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ መፈጸሙን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ኢሳት ለአርቲስ አበበች ደራራ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።

Read More »

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የተጀመረው ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋሞ ካምፓስ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ያዋለ ሲሆን “ተማሪዎች መብታችን ይከበር፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ጥያቄያችን ይመለሰ፣ ተምሮ  ለኮብል ስቶን ” የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ግቢውን የተቆጣጠሩት ሲሆን ተማሪዎች እርስ በርስ እንዳይገናኙ አድረገዋል። ተማሪዎች የምግብ መበላሸትን  ሰበብ አድርገው አድማውን ቢጀምሩም፣ ሌሎች ከትምህርት ...

Read More »